‹የኤርትራ መንግሥት ከሽብር ተግባር አለመታቀቡን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አሳውቀናል›› አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ
በየማነ ናግሽ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በኒው ዮርክ ያደረጉትን ጉብኝት በማስመልከት ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ የኤርትራ መንግሥት ከሽብር ተግባሩ ለመታቀብ ባለመቻሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማሳወቁን ገለጹ፡፡