መንግሥት የሕዝብን የልብ ትርታ ያዳምጥ!

የአመራር የጥበብ መጀመርያ የሕዝብን የልብ ትርታ ማዳመጥ ነው፡፡ ችግርን ለይተው ካላወቁ ትክክለኛ መፍትሔ ለማስቀመጥና ለመስጠት ያስቸግራል፡፡ ችግርን ለይቶ ለማወቅ ደግሞ ሕዝብን ማዳመጥ ያስፈልጋል፡፡ የሚፈታው ችግር የሕዝብ ችግር ነውና፡፡