ሸራተን አዲስ ሆቴል የ19 ሠራተኞቹን የጥቅማ ጥቅም ክፍያ አቋረጠ
በታምሩ ጽጌ
የሸራተን አዲስ ሆቴል ባንኩዌት በተባለው የሥራ ዘርፍ በምግብና መጠጥ አቅራቢነት ላይ ይሠሩ ለነበሩ 19 ሠራተኞች የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሆቴሉ እንዲያገኙ ፍርድ የሰጠባቸውን 11 ውሳኔዎች በመቃወም፣ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ያቀረበው ይግባኝ ‹‹ያስቀርባል›› በመባሉ ሊከፈላቸው የነበረውን የጥቅማ ጥቅም ክፍያ ማቋረጡን አስታወቀ፡፡