ሰሜን ጐንደር ውስጥ በ774 ሺሕ ብር ሙስና የተጠረጠሩ ኃላፊዎች ታሠሩ
– በ668 ሺሕ ብር የተሰጠ ኮንትራትም በ115 ሺሕ ብር እንዲሠራ ተደረገ
በታምሩ ጽጌ
ከተቆረቆረች 400ኛ ዓመቷን ባለፈው ዓመት በጥር ወር 2002 ዓ.ም. ያከበረችውና በሰሜን ጐንደር ዞን ውስጥ የምትገኘው የዳባት ወረዳ ከተማ የውኃ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ የቴክኒክ ቁጥጥር ባለሙያና አንድ ባለሀብት ከ774 ሺሕ ብር በላይ ከተገዛ ንብረት ጋር በተያያዘ በሙስና ተጠርጥረው ከታሰሩ በኋላ ክስ ተመሠረተባቸው፡፡