መንግሥት የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር የጉብኝት ጥያቄን እያጤነው ነው

የኢትዮጵያ መንግሥት የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሳም ሻሪፍ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ያቀረቡትን ጥያቄ እያጤነው እንደሆነ አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ግብፅ በይፋ የጉብኝት ጥያቄዋን ለኢትዮጵያ ብታቀርብም፣ ጥያቄዋ እየታየ ነው፡፡