የሸራተን አዲስ የመጀመሪያዎቹ ተነሺዎች ቤታችንን ልንነጠቅ ነው አሉ
በታምሩ ጽጌ
ሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ሸራተን አዲስን ከመገንባታቸው በፊት በነፃ ቤት ሠርተው እንደሰጧቸውና ይዞታውም የእነሱ እንደሆነ በወቅቱ እንደነገሯቸው የሚገልጹት ሆቴሉ ከተሠራበት ቦታ ላይ ተነስተው ወደ ሲኤምሲ የተዛወሩ በርካታ ነዋሪዎች፣ የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቱ የራሱ መሆኑን በመግለጽ ሊነጥቃቸው መሆኑን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡