የሚሌኒየም ቦንድ ገበያው ደርቷል

በውድነህ ዘነበ

በዓባይ ወንዝ ላይ ለሚገነባው የሚሌኒየም ግድብ የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን የተጀመረው የሚሌኒየም ቦንድ ሽያጭ በአገር ውስጥና በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ትኩረት እየሳበ ሲሆን፣ ግዢውን ለመፈጸም በርካታ ሰዎች የኢትዮጵያ ልማት ባንክንና የኢትዮጵያ ንግድ ባንኮችን እያጨናነቁ ነው፡፡