‹‹በኢትዮጵያ ዓመፅ ቢነሳ ባለቤቱ ሕዝቡ እንጂ ፓርቲዎች አይደሉም››

አንድነት ፓርቲ

– መድረክ ዛሬ በመቀሌ ለጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ እንዳይቀሰቅስ መከልከሉን ገለጸ

በየማነ ናግሽ

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሰሞኑን ‹‹ሽብርና አመፅን ከሚቀሰቅሱ መካከል›› ያሉዋቸውን የአንድነት የፓርቲ አባላት ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ፣ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ፣ በኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመፅ የሚቀሰቀስ ከሆነ የእንቅስቃሴው ባለቤት ራሱ ሕዝቡ እንጂ ፓርቲዎች አይደሉም አለ፡፡