የግንቦት 7 ፍርደኞች ንብረት ቤተሰቦቻቸውንና ዓቃቤ ሕግን እያከራከረ ነው

የፌዴራል ከፍተኛ ዓቃቤ ሕግ በመሠረተባቸው የወንጀል ክስ ጥፋተኛ ተብለው በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ከተወሰነባቸው የግንቦት 7 ተከሳሾች መካከል፣ የብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞና የአቶ አሳምነው ጽጌ ንብረት ቤተሰቦቻቸውንና ዓቃቤ ሕግን እያከራከረ ነው፡፡