ኧረ የፍትሕ ያለህ!
በሦስት ምስክሮች ምክንያት አይጥ ዝሆን ነሽ ተብሎ ተፈረደባት››
ዝሆኖች እንዲታሰሩና ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተላለፈ፡፡ በደረሳቸው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሠረትም ፖሊሶች ዝሆኖችን ማሰር ጀመሩ፡፡ ዝሆኖች ሲታሰሩ በዝሆኖች እግር ሥር ተደናግጣ ስትሽሎኮሎክ የነበረችው አይጥም፣ ከዝሆኖቹ ጋር አብራ ታሰረች፡፡ ከዝሆኖቹ ጋርም ፍርድ ቤት ቀረበች፡፡ በዝሆኖች ላይ የተመሠረተው የዓቃቤ ሕግ ክስ ሲነበብ አይጥ ተቃውሞ አቀረበች፡፡ ይህ ክስ በዝሆኖች ላይ የቀረበ ክስ ስለሆነና እኔ አይጥ ስለሆንኩ አይመለከተኝምና መለቀቅ አለብኝ አለች፡፡