በገመና ቁጥር ፪ ድራማ ላይ የተጠየቀው እግድ ውድቅ ተደረገ

– ኢሬቴድ ያስተላለፈውን ማስታወቂያና የድራማውን ቅጅ እንዲያቀርብ ታዘዘ

በዕለተ እሑድ ለአንድ ዓመት ሲተላለፍ የነበረውና አድናቆትን ያተረፈው የገመና ቁጥር ፩ ተከታይ ገመና ቁጥር ፪ ድራማ ላይ ቀርቦ የነበረው የእግድ ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ፡፡