የዋጋ ግሽበቱ 25 በመቶ ደርሷል

በነጠላ አሀዝ ደረጃ ወርዶ በቁጥጥር ሥር ውሏል ተብሎ የነበረው የዋጋ ግሽበት በበጀት ዓመቱ መባቻ ላይ የተደረገውን የምንዛሪ ለውጥ ተከትሎ የጀመረውን የሽቅብ ጉዞ በመቀጠል፣ ባለፈው መጋቢት ወር 25 በመቶ መድረሱን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ይፋ አደረገ፡፡