ደን ምንጠራው፣ ታላቁ ግድብና መሬት ወረራው
ባህር ዳር ከተማ ከመደረሱ በፊት ከእንጅባራ ከተማ በስተግራ 100 ኪሎ ሜትር ላይ የቤኒሻንጉል ክልል ትልቁ ዞን የሆነው መተከል ይገኛል፡፡ ለዘመናት ተረስቶ የቆየው ይህ ዞን አሁን ሁለት ሰፋፊ ፕሮጀክቶችን በማስተናገድ ላይ ይገኛል፡፡የመጀመርያው በዓባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው ታላቁ የሚሌኒየም ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ግድብ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ለኢንቨስተሮች የተሰጡት ሰፋፊ መሬቶች የሚታረሱበት ፕሮጀክት ነው፡፡ የዓባይ ግድብ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያውያን መነቃቃትን በመፍጠር የቦንድ ሽያጩ እየተፋፋመ ይገኛል፡፡ የግብርና ልማቱ ግን በአስደንጋጭ ሁኔታ ውስጥ ነው የሚለውን የውድነህ ዘነበ ዘገባ፣ የሁለቱን ፕሮጀክቶች አንድነትና ልዩነት እያመሳከረ ይተነትናል፡፡