ከሊቢያ ወደብ ተነስታ የሜድትራኒያንን ባህር በማቋረጥ ወደ ጣሊያን በማምራት ላይ የነበረች መርከብ በመስጠሟ ከ900 ሰዎች በላይ ሳይሞቱ አልቀረም። በመርከቧ ከተሳፈሩ ሰዎች መካከል 28 ስደተኞች ብቻ ተርፈዋል።

እራሱን «እስላማዊ መንግስት» እያለ የሚጠራው አሸባሪ ቡድን 30 ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን ሊቢያ ውስጥ ዛሬ በአሰቃቂ ኹኔታ መግደሉን የሚያሳይ ቪዲዮ ማሰራጨቱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ።

Islamischer Staat Video Christen Libyen 29 ደቂቃ የሚፈጀው ቪዲዮ «ከጠላቲቱ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የመስቀሉ ተከታዮች» የሚል ርእስ እንደያዘ እና ፊታቸውን በጭምብል የሸፈኑ ታጣቂዎች በሁለት ምድብ ኢትዮጵያውያኑን በተርታ ይዘው እንደሚያሳይ ተገልጿል። ሽጉጥ የያዘ አንድ ታጣቂ፤ ክርስቲያኖች እምነታቸውን ወደ እስልምና እስካልቀየሩ ድረስ ቡድኑ እንደሚዋጋቸው በእንግሊዘኛ ቋንቋ ዝቷልም ተብሏል። በመቀጠል ቪዲዮው ውስጥ 12 ሰዎች ያሉበት ቡድን አንገታቸው በካራ ሲቆረጥ፤ ሌሎች ቢያንስ 16 ሰዎች ደግሞ በጥይት ሲገደሉ እንደሚያሳይ የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ የመንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ሬድዋን ሁሴን በ«እስላማዊ መንግስት» የተገደሉት 30 ሰዎች ማንነት ማጣራት አለመቻላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ቃል አቀባዩ አክለው ሲናገሩ «ቪዲዮውን ተመልክተነዋል፤ ሆኖም የተገደሉት ሰዎች ኢትዮጵያውያን ስለመሆናቸው ካይሮ የሚገኘው ኤምባሲያችን ማረጋገጥ አልቻለም» ማለታቸውን የዜና ምንጩ አክሎ ተናግሯል። ቃል አቀባዩ «እንዲያም ሆኖ ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ይኽን አሰቃቂ ድርጊት ያወግዛል» ብለዋል። ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ሊቢያ ውስጥ ኤምባሲ ባይኖራትም ከሊቢያ ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንን ለመርዳት ዝግጁ ናት ማለታቸውም ተዘግቧል። ቀደም ሲል ይኽ እራሱን «እስላማዊ መንግስት» እያለ የሚጠራው አሸባሪ ቡድን 21 የግብጽ ኮፕት ክርስቲያኖችን አንገት የሊቢያ ባሕር ዳርቻ ላይ በስለት መቁረጡ ይታወሳል።

ባለፈዉ መጋቢት 28 በተደረገዉ ምርጫ የመላዉ ለዉጥ አራማጆች ኮንግረስ (APC) ዕጩ የቀድሞዉ ጄኔራል መሐመዱ ቡኸሪ አሽንፈዋል።ከቡኻሪ ማሸነፍ እኩል በሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት ጉድላክ ጆናታን ሽንፈታቸዉን አምነዉ መቀበላቸዉ በናጄሪያ በብዙ የአፍሪቃ ሐገራትም ብዙ ያልተለመደ ዓይነት ዴሞክራሲያዊ የሥልጣን ሽሽግር ነዉ የሆነዉ።

ናይጄሪያ በ1960 እጎአ ከብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ዲሞክራሲያዉ ይትበሐል በምርጫ መሪዎችዋን ለመሾም የተለያዩ ሙከራዎች ተደርገዉባት ነበር።ይሁንና እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር እስከ 1999 ድረስ የተመረጠ የሲቢል አስተዳደር ተደላድሎ ሥልጣን ይዞባት አያዉቅም።

ብዙ ጊዜ በጦር ጄኔራሎች መፈንቅለ መንግሥት፤ አልፎ፤ አልፎ በርስ በርስ ጦርነትና ግጭት ሥትታበጥ አርባ ዓመት ያሕል ያስቆጠረችዉ ምዕራብ አፍሪቃዊት ሐገር አነሰም በዛ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማስተናገድ የጀመረችዉ እጎአ በ1999 ነዉ።ከ1999 እስካሁን ድረስ የሚገዛት ግን ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (PDP) የተሰኘዉ ነዉ።

ባለፈዉ መጋቢት 28 በተደረገዉ ምርጫ ግን አራት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያጣመረዉ የመላዉ ለዉጥ አራማጆች ኮንግረስ (APC) ዕጩ የቀድሞዉ ጄኔራል መሐመዱ ቡኸሪ አሽንፈዋል።ከቡኻሪ ማሸነፍ እኩል በሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት ጉድላክ ጆናታን ሽንፈታቸዉን አምነዉ መቀበላቸዉ በናጄሪያ በብዙ የአፍሪቃ ሐገራትም ብዙ ያልተለመደ ዓይነት ዴሞክራሲያዊ የሥልጣን ሽሽግር ነዉ የሆነዉ።

እርግጥ ነዉ ከቀዝቃዛዉ ጦርነት ፍፃሜ በሕዋላ ለወትሮዉ በመፈንቅለ መንግሥት፤ በነፍጥ ትግል ወይም በዉርስ መሪዎች ሲፈራረቁባቸዉ የነበሩት ብዙ የአፍሪቃ ሐገራት ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እናስተናግዳለን ማለታቸዉ አልቀረም።ይሁንና በትክክለኛ ምርጫ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር የተደረገባቸዉ ፤ ደቡብ አፍሪቃ፤ቦትስዋና፤ሞዛምቢክ፤ ጋና፤ ታንዛኒያ እያልን የምንቆጥራቸዉ የአንድ ዕጅ ጣቶችን እንኳ የማይሞሉ ሐገራት ናቸዉ።

ያሁኑ የናጄሪያ ምርጫ ሒደትና ዉጤት ለአፍሪቃዉያን ምን ያስተምራል ነዉ?የሚለዉ ጥያቄ የዉይይታችን አብይ ጭብጥ ነዉ።

ሰው ለምን በአይሮፕላን መብረርን ይፈራል? በእንግሊዝኛ «አቪፎቢያ» ወይም «ኤይሮፎቢያ» የሚባለው ለምን ያድርበታል? ከሚነቀሳቀስበት የብስ ራቅ ባለና አንዳች ሊቆጣጠረው ፣ ሊይዘው- ሊጨብጠው በማይችልበት ሁኔታ ስለሚገኝ? ሰው በሠራው የሥነ ቴክኒክ

በምዕራብ አፍሪቃ ባለፈው ዓመት የተከሰተውን የኤቦላ ወረርሽኝ ለመታገል ዓ/አቀፉ ማህበረሰብ የወሰደው ርምጃ ንዑስና አዝጋሚ ነበር ሲሉ የርዳታ ድርጅቶች ወቀሳ ሰንዝረዋል። ተላላፊ በሽታ በሚከሰትበት ጊዜ ተመሳሳይ ዝግመት እንዳይታይም፣ የጀርመን መንግሥት አስቸኳይ የህክምና ርዳታ የሚሰጥ ሁሌ ዝግጁ የሚሆን የጦር ግብረ ኃይል ለማቋቋም አቅዷል።

ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም በነዚህ እጩዎች ላይ የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ ከእጩነት ቢያገላቸውም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስዶ እንዲወዳደሩ እንደተበየነለት ሰማያዊ ፓርቲ አስታውቋል ።

የኬንያ መንግስት የዳዳብ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያን ሊዘጋ መሆኑን የጀርመን የዜና ወኪል ዘገበ። በጣቢያው የሚገኙ ከ500 ሺ በላይ የሶማሊያ ስደተኞች የአሸባብ ታጣቂ ቡድን ወደ ማይገኝባቸው የሶማሊያ ግዛቶች እንዲመለሱ ይደረጋል ተብሏል። የኬንያ መንግስት ከዚህ ውሳኔ የደረሰው በጋሪሳ ከተፈጸመው ጥቃት በኃላ መሆኑን የዜና ወኪሉ ጨምሮ ዘግቧል።

በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በተመላሽነት ለመመዝገብ ፓስፖርት ወይም መታወቂያ ያስፈልጋል ተባለ። ኢትዮጵያ በየመን የሚገኙ ዜጎቿን ለመመለስ የምታደርገው ጥረት ግን አዝጋሚ ነው ተብሏል።

የጀርመን የመጀመሪያው መራኄ መንግሥት የኦቶ ፎን ቢስማርክ 200ኛ ዓመት የልደት በዓል ባለፈው ሳምንት ታስቧል ። ከ200 ዓመት በኋላ አሁንም ጀርመናውያን ስለ ቢስማርክ የሚሰጡት አስተያየት በሁለት የተከፈለ ነው ። ቢስማርክ ማንናቸው ?

የዓለም የጤና ቀን በየዓመቱ በጎርጎሪዮሳዊዉ የዘመን ቀመር ሚያዝያ ሰባት ቀን ይታሰባል። የዓለም የጤና ድርጅት የዘንድሮዉን የዓለም የጤና ቀን ያሰበዉ «የሚመገቡት ምግብ ምን ያህል ለጤና ተስማሚ ነዉ» በሚል መሪ ቃል ላይ ተመስርቶ ነዉ።

በስፔን ላሊጋ ክሪያስቲያኖ ሮናልዶ በ8 ደቂቃ ሐትሪክ በመሥራት ለቡድኑ 5 ግቦችን አስቆጥሯል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ሊሰናበቱ እንደሆነ ተገለጠ። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዳጉ ማራቶን የሩጫ ውድድር በወንድም በሴትም አሸናፊ ሆነዋል።

የሲሚንቶ ዋጋ በስልሳ በመቶ ገደማ መጨመሩን ከሀገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን የተገኘዉ ዘገባ ያመለክታል። እንደዘገባዉ ለዋጋዉ መጨመር እንደምክንያት የቀረበዉ በጅቡቲ ወደብ ላይ የተከማቹ እቃዎችን ለማመላለስ እቃ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ወደዚያ በመሠማራታቸዉ ሳይሆን አይቀርም።

ኑክሌርን ለኢራን ያስተዋወቀችዉ ዩናይትድ ስቴትስ ናት።በ1950ዎቹ «አቶሚክ ለሠላም» በሚል መርሕ ዩናይትድ ስቴትስ ለኢራን የሐይል ማመንጪያ ተቋም ማስገባት ጀምራ ነበር።የኑክሌር ተቋም ግንባታዉን ያቋረጠችዉ ደግሞ ማንም ሳይሆን እራስዋ ኢራን ነበረች

በእርስ በርስ ግጭት የጦርነት ቀጣና የሆነችዉ የመን ይዞታ ወደሰብዓዊ ቀዉስ እያመራ መሆኑን የተመድ አመለከተ። የመንግሥታቱ ድርጅት የሕፃናት መርጃ UNICEF እንደገለፀዉ በጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩት ከቤት ንብረታቸዉ ለመፈናቀል ሲዳረጉ፤ አጋጣሚዉ ለበሽታና ለምግብ እጥረት አጋልጧቸዋል።

አንዳንድ የመስኩ ባለሞያዎች በስምምነቱ ኢትዮጵያ ኃይል ከማመንጨት በተጨማሪ በሌሎችም መስኮች ከግድቡ ተጠቃሚ ልትሆን የምትችልበትን እድል አልተጠቀመችም ሲሉ ይተቻሉ ። መንግሥት በበኩሉ ስምምነቱ ብሔራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ ወደ ኋላ የሚል አይደለም በማለት ይከራከራል ።

የናይጀሪያ ህዝብ ባለፈው የሳምንት መጨረሻ በተካሄደ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የቀድሞው ወታደራዊ መንግሥት መሪ መሀማዱ ቡሀሪን ሀገሪቱን ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት እንዲመሩ አዲሱ ፕሬዚደንት አድርገው መርጠዋል።

ዋና ጽ/ቤቱ በፓሪስ ፈረንሳይ የሚገኘው በኢንዱስትሪ የበለጸጉ መንግሥታት የሚገኙበት የኤኮኖሚ ትብብርና ዕድገት ድርጅት (OECD) ከሰሞኑ ስዊድን በሚገኙ ስደተኞችላይ ያተኮረ መግለጫ አውጥቷል።

የመን ውስጥ ጠንካራ ሆኖ በተገኘው የሁቲ አማጽያን ድርጅት ላይ ፣ በስዑዲ ዐረቢያ መሪነት የአየር ኃይል ድብደባው እንደቀጠለ ነው። ጥቃቱ በማየሉም ሁቲ አምጽያንና ተባባሪዎቻቸው ከአድን የወደብ ከተማ ማዕከል አፈግፍገዋል።

ከትናንት ወዲያ ዕሮብ (እኢአ ሚያዚያ 1 ቀን) ፤ ምዕራባዊያን « April fools day » በማለት የሚጠሩት እና ሌሎችን ውሸት በመናገር፤ የሚያስደነግጡበት እና የሚያስጨንቁበት ዕለት ነበር። ይህ ቀን ለምን ይከበራል? የውሸት ለከቱስ የት ድረስ ነው?

በምሥራቃዊ ኬንያ በጋሪሳ ከተማ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ጥዋት የጦር መሳሪያ ባነገቱ ሰዎች ጥቃት እንደደረሰበት ተነገረ። በጥቃቱ ቢያንስ 70 ሰዎች መገደላቸውን፣ ወደ 80 የሚጠጉ ደግሞ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው ወደ ሀኪም ቤቶች መወሰዳቸውን ያካባቢው ፖሊስ አስታውቋል።

በሶማልያ የፖለቲካው ውዝግብ ገና መላ አልተገኘለትም፣ ኧል ሸባብ በበኩሉ ከዕለት ወደ ዕለት የሽብር ተግባሩን አጠናክሮ እንደቀጠለ ነው። ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ መፍትኄ ነው ብሎ ያተኮረው በአብራሪ የለሽ የጦር አይሮፕላኖች (Drones)ጭምር በሚታገዘው

በዓለም ከ7000 በላይ ቋንቋዎች በመግባቢያነት እንደሚያገለግሉ ይነገራል። በዓለም ላይ ከሚገኙ ቋንቋዎች 6 በመቶው የሚሆኑትን 94 በመቶ የዓለም ህዝብ በመግባቢያነት ይጠቀምባቸዋል። የቀሪዎቹ 94 በመቶ ቋንቋዎች ተናጋሪ ግን ከዓለም ህዝብ 6 በመቶ ብቻ መሆኑን ኢትኖሎግ የተሰኘው የዓለም ቋንቋዎች የጥናት ዘገባ ይፋ አድርጓል።

እስራኤል በሕገ ወጥ መንገድ ወደግዛቷ የገቡ አፍሪቃዉያን ስደተኞችን «አስተማማኝ» ወዳለቻቸዉ ሶስተኛ ሃገራት ለማሻገር መወሰኗን አመለከተች። የሀገር ዉስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣዉ መግለጫ መሠረትም ይህን አማራጭ የማይቀበሉ እስራት ይጠብቃቸዋል።

ቀድሞው የግብፅ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከሥልጣን ከተወገዱ ከ አራት ዓመት ወዲህ ግብፅ እንደገና በውጭ አመራር ረገድ ስሟ ይጠራ ጀምሯል። አሁን በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በተለይም በየመን ብርቱ ውዝግብ ካጋጠመ ወዲህ፤ ግብፅ በዐረቡ ዓለም ፤ ፀጥታ የማስከበር ግንባር ቀደም ኀላፊነት ያለባት ሀገር ሆና በምዕራቡ ዓለም ዘንድ መታየት ጀምራለች።

እስከትናንት የመጨረሻ ቀነ ገደብ ተሰጥቶት የነበረዉ የኢራን የኒኩሊየር መርሃግብር ድርድር ዛሬም እንደገና መቀጠሉ እየተነገረ ነዉ። ዘገባዎች እንደሚሉት ከስድስቱ ሃገራት የሶስቱ ተደራዳሪዎች አልተገኙም።

ኢትዮጵያ፤ግብጽና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የተፈራረሙት ስምምነት የመወደሱን ያክል ዛሬም ድረስ እያወያየና እያከራከረ ነው ። የግብጽ ጋዜጦች የስምምነቱን መፈረም በደስታ የመቀበላቸውን ያህል ትችቶችም እየሰነዘሩ ነው።

በዓለም ዙሪያ የተፈጥሮ ሀብት ፤ በሰፊውና በመጠኑ የታደሉ ሃገራት ጥቂቶች አ,ይደሉም፣ ከሞላ ጎደል ምንም የሌላቸውም አሉ። በማስተዋል በሚነደፍ የአጭር ጊዜና የረጅም ጊዜ እቅድ ፣ የተፈጥሮ ሃብትን ለህዝብ ጠቀሜታ እንዲውል የሚያደርጉ መንግሥታት የመኖራቸውን

ብዙ የፖለቲካ ተንታኞች እንደተስማሙበት የቅዳሜዉ ምርጫ ቡኸሪን ለሥልጣን ማብቃቱ ከማሰገረሙ ይልቅ ጆናታን ሽንፈታቸዉን መቀበላቸዉ የዚያችን ሐገር ፖለቲከኞች ብስለት፤ አርቆ አሳቢነት፤ለሐገርና ለሕዝብ ተቆርቋሪነትን መስካሪ ነዉ።

ባለፈዉ ሰኞ ከአዉሮፕላን የተጣለ ቦምብ መዝራቅ በተሰኘዉ መጠለያ ጣቢያ የተጠለሉ አርባ ስደተኞች ወይም ተፈናቃዮችን መግደሉ፤ ጦርነቱ ከተሳታፊዎቹ አልፎ የስደተኞችን ሕወት እያስገበረ መሆንኑ አረጋጧል።በጥቃቱ ከተገደሉት በተጨማሪ ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች ቆስለዋል።ከሟች ቁስለኞቹ መካካል ኢትዮጵያዉን እንደሚገኙበት አንዳድ ዘገቦች ጠቁመዉ ነበር።

በአሁኑ ጊዜ ህገ ወጥ በሚባል መንገድ በአደገኛ ጉዞ አውሮፓ የሚደርሱ ስደተኞች በሙሉ አውሮፓን እንደጠበቋት ሆና አያገኟትም ።ከሞት ተርፈው ምድሪቱን ለመርገጥ ከበቁት መካከል ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጠው አስከፊ ህይወት የሚገፉ ጥቂት የሚባሉ አይደሉም ።

በናይጀሪያ ባለፈው የሳምንት መጨረሻ በተካሄደው ፕሬዚደንታዊ እና ምክር ቤታዊ ምርጫ የተቃዋሚዉ ወገን መሪ ጄኔራል ሙሃማዱ ቡሃሪ ማሸነፋቸዉ ተገለጸ። ስልጣን ላይ የነበሩት ፕሬዝደንት ጉድላክ ጆነተን ተቀናቃኛቸዉን በስልክ እንኳን ደስ ያልዎት ማለታቸዉ ተዘግቧል። ።

ለመድሃኒትነት የሚዉሉ በርካታ የእፅዋት ዓይነቶች መኖራቸዉ ይታወቃል። ከተክሎች የተቀመሙ መድሃኒቶችን መጠቀምም የተለመደ ነዉ። ለመድሃኒት የሚሆኑትን ተክሎች መንከባከቡ ግን ይጎድላል።

በሣዑዲ ዐረቢያ መራሹ የአየር ጥቃት የመን ውስጥ የተከፈተው ዘመቻ ስድስተኛ ቀኑን ባስቆጠረበት በዛሬው ቀን ከ40 በላይ ስደተኞች መገደላቸውን 65 መቁሰላቸውን የየመኑ ወኪላችን ገለጠ። የዓለም አቀፍ ስድተኞች ድርጅት (IOM) በማነጋገር ያገኘሁት ነው ባለው መረጃ መሠረት ከሟቾቹ መካከል ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል ።

በናይጀሪያ ባለፈው የሳምንት መጨረሻ የተካሄደው ፕሬዚደንታዊ እና ምክር ቤታዊ ምርጫ ውጤት አሁንም ገና እየተጠበቀ ነው። ለፕሬዚደንታዊው ምርጫ በዕጩነት ከቀረቡት 14 ተወዳዳሪዎች መካከል ጠንካራው ፉክክር የተካሄደው በፕሬዚደንት ጉድላክ ጆናታን እና በተቃውሞው ቡድን መሪ መሀማዱ ቡሀሪ መካከል ነው።