የስፖርት ዘገባ፤ መጋቢት 21 ቀን፣ 2007 ዓ.ም
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከበርሊን ማራቶን እስከ ቻይና አገር አቋራጭ የሩጫ ፉክክር ብሎም የካርልስባድ ካሊፎርኒያ ውድድር አመርቂ ድሎችን ተቀዳጅተዋል። በዩሮ 2016 የእግር ኳስ የማጣሪያ ፍልሚያ ጆርጂያ ጀርመንን ለግማሽ ሠዓት ያህል ተገዳድራለች፤ ከመሸነፍ ግን አልዳነችም። ትንሺቱ ጅብራልታር እንደለመደችው የግብ ጎተራ ሆናለች።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከበርሊን ማራቶን እስከ ቻይና አገር አቋራጭ የሩጫ ፉክክር ብሎም የካርልስባድ ካሊፎርኒያ ውድድር አመርቂ ድሎችን ተቀዳጅተዋል። በዩሮ 2016 የእግር ኳስ የማጣሪያ ፍልሚያ ጆርጂያ ጀርመንን ለግማሽ ሠዓት ያህል ተገዳድራለች፤ ከመሸነፍ ግን አልዳነችም። ትንሺቱ ጅብራልታር እንደለመደችው የግብ ጎተራ ሆናለች።
ሰማያዊ ፓርቲ፣ ትናንት በ 15 የተለያዩ ከተሞች ሊያካሂድ ያሰበውን ሰላማዊ ሰልፍ ከ 4 ከተሞች በስተቀር በፖሊስ መደናቀፉን የፓርቲው ሊቀመንበር ገለጡ። አዲስ አበባ የተጠራዉ ሰልፍ በታቀደዉ መንገድ መሄድ ባለ መቻሉ ተቃዉሞ ሰልፉ ከጽ/ቤቱ ብዙም ሳይርቅ መደረጉ ተመልክቶአል
በሳዑዲ አረቢያ መሪነት በየመን የሁቲ አማጽያን ላይ የሚካሄደው የአየር ጥቃት ለአምስተኛ ቀን ቀጥሏል። ዛሬ ለሊት ሁለት የጦር አውሮፕላኖች በየመን ቤተ-መንግስት አቅራቢያ ድብደባ መፈጸማቸውን ሬውተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።
በዩናይትድ ስቴትስ ከአፍሪቃዉ ቀንድ የመጡ ሶስት ግለሰቦች በጫት ንግድ በወንጀለኝነት ተከሰዉ የሶስት ዓመት እስራት ተፈረደባቸዉ። ጫት ለብዙ ወንጀሎች የሚያጋልጥ እጽ መሆኑም ተመልክቶአል።
ራሷን የቻለች ሀገር ከሆነች ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረችዉ ኤርትራ ከምዕራቡ ዓለም መንግሥታት ጋ ያላት ግንኙነት የቀዘቀዘ መሆኑ የሚታይ ነዉ። ምሥራቅ አፍሪቃዊቱ ትንሽ ሀገር በአቅራቢያዋ ከሚገኙ ሃገራት ጋ ያላት ግንኙነትም የሞቀ የሚባል አይደለም።
በመካከለኛዉ ምሥራቅ ዉጥረት እያየለ በመጣበት በአሁኑ ወቅት የአረብ ሊግ የዓለም ዜና ጥምር ጦር ለመመሥረት እንደሚፈልግ ተገለፀ። የሚቋቋመዉ ጥምር ወታደራዊ ጦር ሃገራቱ አካባቢ እየጨመረ የመጣዉን ሥጋት እና ደህንነት ያስጠብቃል ተብሎአል።
በመካከለኛዉ ምሥራቅ ዉጥረት እያየለ በመጣበት በአሁኑ ወቅት የአረብ ሊጋዉ ጥምር ጦር ለመመሥረት እንደሚፈልግ ተገለፀ። የሚቋቋመዉ ጥምር ወታደራዊ ጦር ሃገራቱ አካባቢ እየጨመረ የመጣዉን ሥጋት እና ደህንነት ያስጠብቃል ተብሎአል።
ሊካሄድ ከታሰበ ከ6 ሳምንታት በኋላ ዛሬ ናይጄሪያ ውስጥ ጥብቅ ቁጥጥር በተሞላበት ሁናቴ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተካሄደ። አሁን በሥልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን ዳግም ለመመረጥ እጩ ሆነው ቀርበዋል።
የተመድ የፀጥታ ጥ/ም/ቤት በዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ ውስጥ የተሠማራውን እና በምህፃሩ « ሞኑስክ» ተብሎ የሚታወቀውን የተመድ ሰላም አስከባሪ ጓድ ተልዕኮ በአንድ ዓመት አራዝሞዋል፣ ይሁንና፣ አሁን በሀገሪቱ የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ቁጥር በ2000 እንዲቀንስ 15 ሀገራት የሚጠቃለሉበት ምክር ቤት የተመድ ፀ/ጥ/ም/ቤት በአንድ ድምፅ ወስኖዋል።
ኬንያ እና ሶማልያን በሚያዋስነው ረጅም እና ጥበቃው ልል በሆነው ድንበር በኩል ብዙ ህዝብ፣ ስደተኞች እና ሚሊሺያ ሳይቀሩ በየጊዜው ወደ ኬንያ ይገባሉ። ይህ ካለ ቁጥጥር የሚደረገው ዝውውር ግን በቅርቡ ሊያበቃ እንደሚችል ተገልጿል።
በጎርጎሮሲያዊ የዘመን አቆጣጠር ወር በገባ ዘወትር በመጨረሻው ዓርብ ዕለት፤ E-within የሚባለው ድርጅት አንድ የንባብ ምሽት በአዲስ አበባ ከተማ ያዘጋጃል። «የመጽሐፍት ማዕድ» በሚል መጠሪያው የሚታወቀው ይህ ምሽት፤ ለሁሉም መጽሐፍ አፍቃሪያን ክፍት ነው።
ሳውዲ ዓረቢያ ግብፅ ሱዳን ጨምሮ አስር ሀገራት የየመን ፕሬዚደንት አቤድ ራቦ ማንሱር ሀዲን በመፃረር የሚዋጉትን የሁቲ ዓማፅያን ማጥቃት ከጀመሩ አንድ ቀን አልፏል።
ዛሬ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በተካሄደዉ የፓርቲዎች ክርክር ሰማያዊ ፓርቲ እንዳልሳተፍ ተደረኩ ሲል አማረረ።
ዛሬ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በተካሄደዉ የፓርቲዎች ክርክር ሰማያዊ ፓርቲ እንዳልሳተፍ ተደረኩ ሲል አማረረ። የኢትዮጵያ ብሮድካስቲግ ኮርፖሬሽን በበኩሉ የክርክር መድረኮቹ በእጣ መደልደላቸዉን ገልጾአል።
በደቡብ ፈረንሳይ በሚገኘዉ ተራራማማ አካባቢ ሰሞኑን የተከሰከሰዉ የጀርመን አዉሮፕላን በቴክኒክ ጉድለት ወይም በሌላ ምክንያቶች ሳይሆን ረዳት አብራሪዉ ሆን ብሎ የፈፀመዉ የጥፋት ርምጃ መሆኑ ተሰምቷል።
ዛሬ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በተካሄደዉ የፓርቲዎች ክርክር ሰማያዊ ፓርቲ እንዳልሳተፍ ተደረኩ ሲል አማረረ። የኢትዮጵያ ብሮድካስቲግ ኮርፖሬሽን በበኩሉ የክርክር መድረኮቹ በእጣ መደልደላቸዉን ገልጾአል።
«የዘፈኑን ዕድሜ ስነግራችሁ ሸመገለ እንዳትሉኝ እንጂ « ተማር ልጄ» የተዘፈነዉ የዛሬ ሰላሳ አምስት ዓመት ነዉ። ያዘለዉ መልክት እዉነተኛ አባት ለልጁ የሚሰጠዉ ምክር ነዉ። የሰዉ ልጅ ካልተማረ ዋጋ የለዉም። ስለሆነም አባቶች የሚሰጡንን ምክር በዚህ ዘፈን ለመጭዉ ትዉልድ የዘራሁት ነዉ ብዬ ነዉ የማምነዉ» አለማየሁ እሸቴ
ሰሜናዊውን የመን ቀደም ሲል ፤ ከዚያም ካለፈው መስከረም አንስቶ መዲናይቱን ሰንዓን የተቆጣጠሩት ሁቲ አማጽያን፣ መላይቱን ሀገር ለመቆጣጠር ወደ ደቡብ በመዝመት የአደንን የወደብ ከተማ ለመያዝ በተጠጉበት ወቅት፤
ከኤርትራ በአደገኛ ሁኔታ ወደአዉሮጳ በገፍ የሚነጉዱትን ስደተኞች ለሀገሪቱ የልማት እርዳታ በመስጠት ለመርዳት ጥረት የሚደረግ ስለመሆኑ የዜና አዉታሮች የአዉሮጳ ኮሚሽንን ባለስልጣናት ጠቅሰዉ ሰሞኑን ዘግበዋል። ሮይተርስ
የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታኅ ኧል ሲሲ በኢትዮጵያ ያደረጉትን የ 3 ቀናት ጉባዔ ፈጽመው ተመልሰዋል። ኧል ሲሲ ወደ ኢትዮጵያ ከመሻገራቸው በፊት ካርቱም ላይ ፤ ከኢትዮጵያና ከሱዳን መሪዎች ጋር፤ የዐባይን ውሃ
የደቡብ ሱዳን ምክር ቤት የፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪርን የስልጣን ዘመን ለተጨማሪ ሶስት ዓመታት አራዝሟል። ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪርን እስከ ጎርጎሮሳውያኑ 2018 በፕሬዝዳንትነት መንበረ ስልጣኑ ላይ የሚያቆየው ውሳኔ በዋና ከተማዋ ጁባ በሚገኙ ተቃዋሚዎች ዘንድም ተቀባይነት አላገኘም። የፖለቲካ ተንታኞች ግን ጉዳዩ አዲስ አይደለም እያሉ ነው።
የጀርመናውያኑ አየር መስመር «ጀርመንዊንግስ፣ ኤ 320 ኤርባስ » አይሮፕላን፣ ትናንት በደቡብ ፈረንሳይ በአልፕስ ተራራ በምትገኘው የባርሰሎኔት አካባቢ በተከሰከሰበት አሳዛኝ አደጋ 150 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በአደጋው ከሞቱት 72 ጀርመናውያን እና 51 ስጳኛውያን ሌላ፣ የብሪታንያ፣ ዴንማርክ፣
በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደታወቁት እንደ E-BAY እና AMAZON ትልቁ የቻይና የ ONLINE ንግድ ድርጅት «አሊባባ» ባለቤት የሆኑት የጠነጠኑት ቻይናዊው ሀብታም ፤ ጃክ ማ ፤ ቀደም ባሉት ዘመናት የተከሠቱት የኢንዱስቴትሪ አብዮቶች፤ ሰዎች
አንድ «ጀርመንዊንግስ» የተባለው የጀርመናውያኑ አየር መስመር ሉፍትሀንዛ ቅርንጫፍ አየር መንገድ አይሮፕላን ዛሬ በደቡብ ፈረንሳይ መከስከሱን የፈረንሳይ ፖሊስ እና የበረራ ተቆጣጣሪ ባለስልጣናት አስታወቁ።
በጀርመን እና በግሪክ የገንዘብ ሚኒስትሮች መካከል ንግግሩ ከሯል። ጉዳዩ በሁለት ሚኒስትሮች ብቻ የሚፈታ አይደለም። አዲሱ የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲስ ሲፕራስ ሰኞ ወደ ጀርመን መጥተው ከጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ጋር ስለ ግሪክ የኢኮኖሚ ቀውስ ተወያይተዋል። የሚያስማማ ሀሳብ ላይ ግን አልደረሱም።
ኢትዮጵያ ፣ግብፅ እና ሱዳን የአባይ ወንዝን ውኃ በጋራ መጠቀም ስለሚችሉበት መንገድ የጋራ ነጥብ ላይ ደርሰው ትናንት ሰኞ ከአንድ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተሰምቷል።
የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታሕ ኧል ሲሲ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና ከፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመጋ ጋር በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ተገናኝተው ዛሬ በሰፊው መወያየታቸዉ ተሰምቷል።
«ዉኃና ዘላቂ ልማት» ከአንድ ቀን በፊት በመላዉ ዓለም የታሰበዉ የዘንድሮዉ የዓለም የዉኃ ቀን መሪ ቃል ነዉ። ለጤና፤ ለአካባቢ ልማት፤ ለኢንዱስትሪ ባጠቃላይ ለዕለት ከዕለት ኑሮ ወሳኝ መሆኑን በተለያዩ መድረኮች ለማሳየትም ተሞክሯል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ትናንት መጋቢት 13 ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ አገሪቱ የርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ልትገባ ትችላለች ሲል በድጋሚ አስጠንቅቋል። የሑቲ አማጽያን በበኩላቸው ወደ ደቡብ የመን የሚያደርጉትን ግስጋሴ ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒኬሽን 4G የተባለዉን አዲስ ቴክኖሎጂ ለግዙፍ ድርጅቶችን ለዓለማቀፍ ተቋማት በአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎት መጀመሩን ይፋ አደረገ።
ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች በሮም ማራቶን በወንድም በሴትም አሸናፊ ሆነዋል። በጀርመን ቡንደስ ሊጋ የዘንድሮ ውድድር ባየር ሙይንሽን በሜዳው ለመጀመሪያ ጊዜ ሽንፈት ገጥሞታል። በስፔን ላሊጋ ባርሴሎና ዋነኛ ተፎካካሪው ሪያል ማድሪድን አሸንፏል። የሊቨርፑሉ ሽቴፋን ዤራርድ ከሜዳ በቀይ ካርድ ተሰናብቷል።
የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲስ ሲፕራስ ከጥቂት ሰዓታቶች በፊት ጀርመን መዲና በርሊን ላይ ይፋዊ ጉብኝታቸዉን ጀምረዋል።
የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲስ ሲፕራስ ከጥቂት ሰዓታቶች በፊት ጀርመን መዲና በርሊን ላይ ይፋዊ ጉብኝታቸዉን ጀምረዋል።
ዱካውን በአፍጋኒስታንና ፓኪስታን አሳርፎ ሰሜንና ምዕራብ አፍሪቃ መድረስ ችሏል። ከናይጄሪያው ሌላኛው አሸባሪ ድርጅት ቦኮሃራም ጋር መወዳጀቱ፣ በሊቢያ መንሰራፋቱ ይነገርለታል። አሸባሪው ቡድን በሊቢያ የግብፅ ኦርቶዶክሶችን አንገት ለካራ መዳረጉ የቅርብ ትዝታነቱ ገና ሳይዘነጋ፤ በደም የታጠበ እጁን በንዑሷ ቱኒዝያ ለተጨማሪ ጥፋት መዘርጋቱ አልቀረም።
ዘመናዊቷ እሥራኤል፣ እ ጎ አ ግንቦት 14 ቀን 1948 ዓ ም ፤ መንግሥት ከመሠረተችበት ጊዜ አንስቶ ፣ ከፍልስጤማውያንና ከዐረብ መንግሥታት ጋር ተደጋጋሚ ጦርነቶች ተካሂደው እንደነበረ የሚታወስ ነው።የኦስሎውን ስምምነት ጨምሮ በጠቅላላ ከ 14 የማያንሱ
ከ 20 ዓመታት በላይ በሶማሊያ የተረጋጋ መንግሥት አይስተዋልም። ስለሆነም በሀገሪቱ ይፋና መደበኛ የሆነ የባንክ አሰራር ስርዓት የለም። ለአመታት በዘለቀው የርስ በዕርስ ጦርነት ምክንያት በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ከሀገራቸው ተሰደዋል።
የኢትዮጵያ መጪውን ምርጫ ምክንያት በማድረግ ፊት ለፊት ቀርበው ስለተከራከሩት አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ፤
ባለፈው እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ ቁጥራቸው በሺ የሚቆጠሩ ሴቶች ሮጠዋል። ከነዚህም ውስጥ 700 የሚሆኑት የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ናቸው። የሴቶችን ተሳትፎ እና መብት ለማበረታታት በየዓመቱ ስለሚካሄደው የሩጫ ውድድር በዛሬው የወጣቶች ዓለም እንመለከታለን።
ከተለያዩ የአዉሮጳ ሃገራት የተዉጣጡ ኢትዮጵያዉያን በዛሬዉ ዕለት ጄኔቭ ስዊትዘርላንድ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።
የጀርመኗ ፍራንክፉርት ከተማ ትናት በዓመጽ ስትናጥ ነበር። መኪናዎች እና ጎማዎች አደባባዮች ላይ ሲነዱ፣ ቁሳቁሶች ሲወረወሩ የተቃውሞ ሰልፉ የተኪያሄደበት የከተማው ክፍልም በጥቁር ጢስ ተውጦ ታይቷል። የግጭቱ መንስዔ ደግሞ በፍራንክፉርት ከተማ አዲስ የአውሮጳ ማዕከላዊ ባንክ መከፈት ነው።
በቱኒዝያ መዲና ቱኒስ ውስጥ ትናንት በደረሰው የሽብር ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 23 መድረሱ ተዘገበ። ከሟቾቹ መካከል ኻያው አገር ጎብኚ የውጭ ዜጎች ናቸው ተብሏል።
የኢትዮጵያ ጦር በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ከአሸባብ ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን የእስልምና ሃይማኖት መምህር ፍለጋ ወደ ሰሜን ሶማሊያ ገብቶ እንደ ነበር ተሰማ። ጦሩ ከገባበት አካባቢ ወዲያው ለቆ መውጣቱ ተዘግቧል።
በምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት /ኢጋድ/ አማካኝነት ሲካሄድ የከረመው የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ሃይሎች ድርድር አለመሳካቱን ተከትሎ በአገሪቱ ሁለት ግዛቶች ተቀስቅሶ የነበረው ግጭት ወደ ሌሎች አራት ግዛቶች መስፋፋቱን የአገሪቱ ባለስልጣናት አረጋግጠዋል። ግጭቱ በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች ነዋሪዎች ቀያቸውን ጥለው እየተሰደዱ ነው።
«በቆዳ ቀለማችን ለየት ብንልም ልባችን ኢትዮጵያዊ ነዉ ፤ ኢትዮጵያን፤ ኢትዮጵያዉያንን በኔና በቤተሰቤ ስም በጣም ማመስገን እፈልጋለሁ» ትዉልደ አርመኑን ኢትዮጵያዊ ሙዚቀኛ ቫሄ ቲልብያን የዛሬ ወር ኢትዮጵያን፤ አፍሪቃን ብሎም አርሜንያን ወክሎ በግዙፉ የአዉሮጳ ሃገራት የሙዚቃ ዉድድር ላይ ሙዚቃ እንዲያቀርብ ተመርጦአል።
2,8 ሚሊዮን ዓመት ያስቆጠረ የቅድመ ሰው መንገጭላ ከ አምስት ጥርሶች ጋር ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘት፤ በሳይንስ ምልከታ መሠረት ፣ ከቅድመ ሰው እስከዛሬው ዘመን ሰው ዝግመታዊው እርከናዊ ለውጥ ፣ ምን ዓይነት ትርጉም እንደተሰጠው ባለፈዉ ሳምንት ዝግጅት ዳስሰን እንደነበረ ይታወስ ይሆናል።
የአዉሮጳ ፓርላማ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚቴ ትናንት በኤርትራ ጉዳይ ላይ ተወያየ። ኮሚቴዉ በዉይይቱ በኤርትራ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ያለዉን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የሕዝቡንም ችግር መርምሯል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የሚመሩት የሊኩድ ፓርቲ በትናንቱ ዕለት የተካሄደው ምክር ቤታዊ ምርጫ አሸናፊ ሆነ። ከ120 የምክር ቤት፣ ክኔሴት መንበሮች ሊኩድ 30 ዎቹን ፣ ዋነኛው ተፎካካሪያቸው ይትዝሀቅ ሄርሶግ የመሩት የተቃውሞ የመሀል ግራው የጽዮናውያኑ አንድነት ትብብር 24 ፣ የዐረባውያኑ ፓርቲዎች የመሠረቱት
በዓለም አቀፉ የኃይል ተቋም (International Energy Agency) መሠረት 75 በመቶ ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሪክ ኃይል አያገኙም። ይህ የኃይል ድህነት በገጠራማ አካባቢዎች ይበረታል። አቶ ዮሴፍ ብርሃነ የኤተርኑም ኢነርጂ ቬንቸርስ (Eternum Energy Ventures )የተባለ ኩባንያ መስራች እና ባለቤት ናቸው።
በእሥራኤል 120 መቀመጫዎች ላሉት 20ኛው የክኔሴት ማለትም የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ምርጫ በመኪያሄድ ላይ ነው። 5.8 ሚሊዮን ነዋሪዎች ለመምረጥ መመዝገባቸው ተጠቅሷል። የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት እኩለ ሌሊት ላይ የሚገለጥ መሆኑም ተነግሯል።