አጭር ማስታወሻ ለእስክንድር ፍሥሓ ታደሰ ፈለቀ
ውድ እስክንድር፦ በቅድሚያ እንኳን ለዘመነ ማቴዎስ አደረሰኽ። በመቀጠልም ስለኑሮኽ ልጠይቅኽ፦ (ኑሮ ካሉት ቃሊቲም… ነውና) እንዴት አለኽ? ውድ ባለቤትኽስ? ልጅኽስ? እኔ አምላከ-ኢትዮጵያ ይመስገን ከመላ ቤተሰቤ ጋራ ደኅና ነኝ። ከዚህ የሚቀጥለውን እንዳንድ ታናሽ ወንድም ማስታወሻ ውሰድልኝ። ስላንተ ላንተ ማውሳት ከንቱ ድካም ይኾናል። ስለዚህ አልሞክረውም። ይልቅ የማውቅኽ በዝና ብቻ ሳይኾን አንድ ቀን ተያይተን እንደነበረ ልጠቁምኽ እወዳለኹ። ሥድስት ኪሎ […]