ቤን አኩር ቱኑዝያዊው የዲሞክራሲ ተሸላሚ

ቱኒዝያዊው የህግ ባለሞያ ያድ ቤን አኩር እዚህ ቦን ውስጥ አለም ዓቀፍ የዲሞክራሲ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ። ቤን አኩር እጎአ ከጥር 2011ቱ የቱኒዝያ ህዝባዊ አብዮት በኋላ የመጨረሻው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ እንዲካሄድ ያበቃው የቱኒዝያ የተሃድሶ ኮሚሽን ሃላፊ ነበሩ ።