ኢሕአዴግ በአዲሱ ዓመት የፖለቲካ ምኅዳሩን እንዲያሰፋ ተቃዋሚዎች ጠየቁ

በኃይሌ ሙሉ

በፖለቲካ ምኅዳር መጥበብ ምክንያት ለኅብረተሰቡ አጀንዳቸውን ማቅረብ ያልቻሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወደ አክራሪነት እንዳይቀየሩና በመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ ላይ ጉዳት እንዳይከሰት ከተፈለገ፣ መንግሥት ከአዲሱ ዓመት ጀምሮ የፖለቲካ ምኅዳሩን ማስፋት አንዳለበት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ገለጹ፡፡