ከመለስ በኋላስ?

(ተመስገን ደሳለኝ – አዲስ አበባ)

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዕሁድ ዕለት ስርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟል። ለሁለት ሳምንት ያህልም ለእልፍ አእላፍት አንገብጋቢ ጉዳዮቻችን ግርዶሽ ሆኖብን የነበረው ብሔራዊ  ዘንም አብሮ አብቅቷል። ለቤተሰቦቻቸው እና ለዘመዶቻቸው መፅናናትን ከልብ እመኛለሁ። ስለዚህም ከቀብር መልስ ባሉ  ገራዊ ጉዳዮች ላይ መነጋገር መ መር አለብን ብዬ አስባለሁ።