ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የ106 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ለቻይና ኩባንያ ሰጠ
– በበጀት ዓመቱ በ3.7 ቢሊዮን ብር 45 ፕሮጀክቶችን እጀምራለሁ አለ
በታምሩ ጽጌ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ከሲኤምሲ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ ድረስ ተዘርግቶ የነበረውን ከባድ የውኃ ማስተላለፊያ መስመር ለመቀየር፣ 70 ሺሕ ሜትር ኪዩብ ውኃ ማምረት የሚያስችሉ ጥልቅ ጉድጓዶችን ለማስቆፈር፣ ለቻይናው ሲጂሲ ኦቨርሲስ ኩባንያ ከ106 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለመክፈል ስምምነት መፈራረሙን አስታወቀ፡፡