የኢትዮጵያ ሕዝብ የዘመንና የሥልጣን መሸጋገሪያ የግዴታ ስጦታ ከመንግሥት እየጠበቀ ነው

የዘንድሮ የዘመን መለወጫ በዓል ለየት ያለ ሆኗል፡፡ አሮጌው ዓመት አልፎ አዲስ ዓመት መምጣቱ የተለመደና ቤተሰብ መሰባሰቡ፣ እንኳን አደረሰህ መባባሉ፣ በጋራ መብላቱና መጫወቱ ባይቀርም፣ ዋናው አጀንዳ የዶሮ፣ የበግ፣ የመጠጥ፣ የጭፈራና የዘመን መቀያየር ሳይሆን፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕልፈት ምክንያት የተከሰተው የአመራር መተካካት እንዴት ይከናወናል የሚል ሕዝባዊ ጥያቄ ያንዣበበት በዓል ነው፡፡