አነጋሪው የኢትዮጵያ የሥልጣን ሽግግር

በአፍሪቃ ጉዳዮች ላይ ልዩ ልዩ ዘገባዎችን የሚያቀርበው አፍሪካ ኮንፊደንሽያል በመባል የሚታወቀው ለንደን ብሪታኒያ የሚታተመው መፅሄትና ድረ ገፅ አዘጋጅ ፓትሪክ ስሚዝ ለዶቼቬለ በሰጠው ቃል ምልልስ በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት ሰለማዊ የሥልጣን ሽግግር መኖር አለመኖሩም ግልፅ አይደለም ብሏል ።