ዶክተር እሌኒ ከያራ ያገኙትን ሽልማት ለበጐ አድራጐት ድርጅት ማቋቋሚያ ሊያውሉት ነው

በዳዊት ታዬ

የኢትዮጵያ የምርት ገበያ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር እሌኒ ገብረ መድህን በግብርና ግብዓት አምራችነቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚታወቀው ያራ ፋውንዴሽን የዘንድሮ ተሸላሚ በመሆን የተበረከተላቸውን 30 ሺሕ ዶላር ለታዳጊ ሴቶች በጐ አድራጐት ድርጅት ማቋቋሚያ እንደሚያውሉት ገለጹ፡፡