በኢትዮጵያ የረሃብተኛው ቁጥር ወደ 11.3 ሚሊዮን አሻቅቧል::ወገን በጠኔ እየረገፈ ቀባሪ እየጠፋ ነው::
የወያኔው አገዛዝ ቅድመ ጥንቃቄ ያላደረገበት በተኮፈሱ ፖሊሲዎች እና በተቆለሉ ቁጥሮች ተተብትቦ በሃስት ፕሮፓጋንዳ በሚቦዝንበት በዚህ ወቅት የረሃብ አደጋውን ሞቅ ቀዝቀዝ እያደረገ ሰበቡን በተፈጥሮ ላይ በመላከክ የሕዝብን ሃሳብ ወደ ሌላ በመውሰድ አጀንዳው ለማጠፍ በሚታታርበት በዚህ ወቅት የረሃብተኛው ቀጥር ወደ 11.3 ሚሊዮን መድረሱ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው::

በተለያዩ አከባቢዎች ለእርዳታ ስራ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን የሰበሰቡት መረጃ እንደሚጠቁመው የረሃብተኛው ቁጥር ባለፈው ጊዜ የወያኔ ባለስልጣንት እንደተናገሩት 8.2 ሚሊዮን ብቻ ሳይሆን የተሰበሰቡ ዳታዎች እንደሚያሳየው ከ11 ሚሊዮን በላይ መሆናቸውን እየተናገሩ ነው::ይህ የድርቅ እና ረሃብ ችግር እንደሚከሰት ከሰኔ 2015 በፊት ተጠቁሞ የነበረ ሲሆን በተለይ በአፋር በትግራይ እና ኦሮሚያ ክልል የምግብ እጥረት በመኖሩ ተብለው በውጭ እርዳታ ድርጅቶች በኩል የተመዘገቡ ዜጎች አስቸኳይ እርዳታ እንዳያገኙ ወያኔ ከፍተኛ ጋሬጣ ሆኖ እንደነበር ተጠቁሟል::
ቻይልድ ፈንድ አውስትራሊያ የተባለው የእርዳታ ድርጅት ይፋ እንዳደረገው፣ ከህዳር እስከ ግንቦት 2007 ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ 140,000 የሚጠጉ የምግብ እጥረት ያለባቸውን ሕፃናት በአስቸኳይ ለመመገብ ፕሮግራም መመዝገባቸው አውስቶ ሕጻናቱ በአብዛኛው ከትግራይ፣ ከኦሮሚያ፣ ከአፋር፣ ከደቡብ፣ ከሶማሌና ከአማራ ክልል እንደነበሩ ድርጅቱ በሪፖርቱ አስቀምጧል::ይህ የሚያመለክተው ረሃቡ እንደሚከሰት የታወቀው ዜጎች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚፈልጉ የታወቀው ከህዳር 2007 ጀምሮ መሆኑ በቀ መረጃ እያለ ነገሩን በመሸፋፈን ለመደበቅ እና ለማድበስበስ የሞከረው ወያኔ ለአሁኑ ከባድ ችግር ዜጎችን መዳረጉ ማረጋገጫ ነው::አሁንም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዳለው ረሃቡን እየደበቁ በፍጥነት መከላከል ካልተቻለ በሚቀጥለው 2 ወር ውስጥ ብቻ ወደ 15 ሚሊዮን ያድጋል::ቅድሚያ ለፖለቲካ ፍጆታ ሳይሆን በረሃብ ለተጎዱ ወገኖች ይሁን::#ምንሊክሳልሳዊ