የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት በቅርቡ በክብር ወደ ቦታው ይመለሳል ተባለ ::

የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት በቅርቡ በክብር ወደ ቦታው ይመለሳል ተባለ::

በአዲስ አበባ የቀላል ባቡር መስመር ዝርጋታ ሳቢያ ከቦታው የተነሳው የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት በቅርቡ በክብር ወደ ቦታው እንደሚመለስ በቅርስ ጥበቃና ጥናት ባለሥልጣን ከፍተኛ የቅርስ ተመራማሪ የሆኑት አቶ ኃይሉ ዘለቀ ለሸገር ተናግረዋል፡፡
እስካሁን ሐውልቱ ወደ ቦታው ያልተመለሰው የባቡሩ ንዝረት ሐውልቱን ይጎዳዋል ወይ የሚለውን በባለሞያ በማስጠናት ላይ በመሆኑና አሁን ግን ንዝረቱ ለሐውልቱ ስጋት እንደማይሆን በመረጋገጡ ሐውልቱ በቅርቡ በክብር ወደ ቦታው ይመለሳል ብለዋል።