ነገሩ፣ ለዘመናት ከምናውቀው እውቀት የተለየ በመሆኑ ግራ ማጋባቱ አይቀርም፡፡ እስካሁን ለሕፃናት ዕድገትና ጥንካሬ ጥሩ ነው በማለት ሕፃናትን ስንመግብ የኖርነው ወተት፤ በተቃራኒው ለሕፃናት ዕድገት ጥሩ አይደለም፤ ያቀጭጫቸዋል ቢባሉ ምን ይላሉ? የሚገርም ነው!ሰሞኑን በሂልተን ሆቴል ሲካሄድ በቆየው 4ኛ የአፍሪካ የምግብና የኑትሪሽን ፎረም …

የአዲስ አበባና አካባቢዋ ወተት ከፍተኛ መርዛማ ኬሚካል አለው ተባለ Read more »

በባቲ ከተማ የሚገኝ አንድ የአእምሮ በሽተኛ የሆነ ልጅ ከወራት በፊት “አርዳችሃለሁ እገድላችሃለሁ” እያለ ይናገራል። በፌስቡክም ላይ ይፅፋል። እንኳን ዘንቦብሽ እንዲሉ ከፌድራል ቀጥታ ባቲ ድረስ የሄዱ ፖሊሶች ና ደህንነቶች ይህን ልጅ ለመያዝ ባቲ ከተማ ላይ ይደርሳሉ። የአካባቢው ነዋሪዎችም ልጁ የአእምሮ ችግር …

የወያኔ ዳኞች የአእምሮ በሽተኛ የሆነውን ልጅ የአይሲስ ወታደር ነኝ ብሏል ብለው ሊፈርዱበት ነው Read more »

በባህርዳር የባጃጅ ሾፌሮች አድማ መቱ የባህርዳር ከተማ የባጃጅ ሾፌሮች የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፁ፡፡ በከተማው ባጃጆች ከአንድ መስመር ውጭ እንዳይሰሩ ከመከልከላቸው ባሻገር ኮንትራት ጭናችኋል በሚልና በሌሎችም ሰበቦች በየቀኑ ከፍተኛ ቅጣት ስለሚጣልባቸውና ቅጣቱ ከሚያገኙት ገቢ በላይ በመሆኑ የስራ ማቆም …

በባህርዳር የባጃጅ ሾፌሮች አድማ መቱ Read more »

የሳተላይት ሥርጭቱ መካከለኛው ምሥራቅን፣ ደቡብ አውሮፓንና ሰሜን አፍሪቃን ያካልላል (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፮ ቁጥር ፰፻፳፬፤ ጥቅምት ፳ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በሀገር ውስጥና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ አገልጋዮችዋ እና ምእመናንዋ ድምፅዋን የምታሰማበትና መረጃ የምትሰጥበት የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን አገልግሎት እንድትጀምር ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ፡፡ ከጥቅምት 12 ጀምሮ የዓመቱን የመጀመሪያ የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ በማካሔድ …

ግድያ ለመፈፀም ዝቷል- አቃቤ ህግ
    በፌስቡክ፤ “አይኤስ ነኝ” ከሚል መልእክት ጋር የግድያ ዛቻ በማስተላለፍ የሽብር ወንጀል ፈፅሟል ተብሎ የተከሰሰው ወጣት ላይ፤ የአቃቤ ህግ ከትናንት በስቲያ ምስክሮችን አቀረበ፡፡ አቃቤ ህግ ያቀረበው ክስ፣ ሰይድ መሃመድ፣ በሚያዚያ ወር 2007 ዓ.ም፤ “አይኤስ ነኝ” በማለት በፌስቡክ እንደጻፈ ይገልጻል፡፡ የአይኤስ ወታደር ነኝ … በቅርቡ በረመዳን ወር የሚታረዱትን ለመያዝ ወደ ባቲ እመጣለሁ” የሚል የዛቻ መልዕክት በግል በፌስቡክ ገፁ ላይ ለጥፏል ብሏል – አቃቤ ህግ፡፡
1ኛ የአቃቤ ህግ ምስክር፤ ከላይ የተጠቀሰው መልዕክት ላይ ሰዎች አስተያየት በሰጡበት ወቅት ይህንን መልዕክት በፌስቡክ መመልከቱን  የገለፀ የአቃቤ ህግ ምስክር፤ ከአካባቢዬ ወጣቶች ጋር በመመካከር ለፖሊስ ጠቁሜያለሁ ብሏል፡፡
የባቲ ከተማ ፖሊስ መሆናቸውን የገልፁ ሌላ የአቃቤ ህግ ምስክር በበኩላቸው፣ ጥቆማ ከደረሰን በኋላ ተጠራጣሪውን በቁጥጥር ስር አውለናል ብለዋል፡፡ በተጠርጣሪው የፌስቡክ ገፅ ላይም፤ “አይኤስ ማለት እንደኔ አይነት ነው፡፡ በረመዳን ወር ለእርድ ወደ ባቲ እመጣለሁ” የሚል መልዕክት አይቻለሁ ብለዋል፡፡
በወቅቱ “ለምን ይሄን አደረግህ” ብዬ ጠይቄዋለሁ፤ እሱም፤ “እኔ ጓደኞቼን ለማስፈራራት ነው  እንጂ አይኤስ አይደለሁም” ሲል መልሶልኛል ብለዋል – እኚሁ የአቃቤ ህግ ምስክር፡፡ በሚያዚያ ወር፤ አይኤስ የተሰኘው አሸባሪ ቡድን፣ በሊቢያ በርካታ ኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን በሚያዝያ ወር፣ አይ ኤስ የተሰኘው አሸባሪ ቡድን በሊቢያ በርካታ ኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ ለማውገዝ፤ ወደ ሰላማዊ ሰልፍ ለመሄድ እየተዘጋጀሁ እንደነበር አስታውሳለሁ፤ ተጠርጣሪው የተያዘውም በዚያኑ እለት ነው በማለት ምስክሩ ተናግረዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ነው፤ ተጠርጣሪው ለምርመራ ወደ አዲስ አበባ የመጣው ተብሏል፡፡
የአቃቤ ህግ 3ኛ ምስክር የአዲስ አበባ ነዋሪ እንደሆኑ ጠቅሰው፤ ተጠርጣሪው የፌስቡክ ገፁ የራሱ መሆኑን አምኖ ሲፈርም እኔ በታዛቢነት ፈርሜያለሁ ብለዋል፡፡ በፌስቡክ አካውንቱ ላይ የተፃፈውንም መልዕክት እንደተመለከቱ ተናግረዋል፡፡
ፍ/ቤቱም የምስክሮቹን ቃል ካደመጠ በኋላ በመቅረፀ ድምፅ የተቀረፀው ምስክርነት ወደ ፅሁፍ ተገልብጦ የመዝገቡ አካል እንዲሆን ትዕዛዝ ያስተላለፈ ሲሆን ምስክርነቱን መርምሮ ብይን ለመስጠትም ለህዳር 30 ቀን 2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
 ተከሳሹ ወጣት፤ የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ እስከማገኝ ድረስ በንፁህነት የመታየት መብቴን እንዳላጣ፣ የፍርድ ሂደቱ፤ ተመልካችና ጋዜጠኛ ሳይኖር፤ በዝግ ይታይልኝ ሲል ጠይቋል በጠበቃው አማካኝነት፡
፡ ፍ/ቤቱ ግን፤ ክሱ መታየት የጀመረውና የተነበበው ተመልካቾች ባሉበት በግልፅ ችሎት መሆኑን በመጥቀስ፣ አቤቱታውን ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ በተከሳሹ የፌስቡክ ገፅ ላይ የተለጠፈው መልእክት፤ “እኔ አይኤስ አይኤስ ነኝ፣ የስራ ድርሻዬም ሰውን እጅና እግሩን አንጋልዬ መያዝ ነው፤ ደሞዝ የሚከፈለኝ በያዝኩት ሰው ልክ ነው፣ የአይኤስ ወታደር ነኝ፤ በቅርቡ ወደ ባቲ ለእርድ እመጣለሁ” የሚል ነው ብሏል – አቃቤ ህግ፡፡ ተከሳሹ በበኩሉ፤ “የፃፍኩት ለቀልድ ነው” ማለቱ ተገልጿል፡፡

መምህር ግርማ የታሰሩት 800ሺህ ብር በማታለል ተጠርጥረው ነው ተጠርጣሪው አስተባብለዋል

      ታዋቂው መምህር ግርማ ወንድሙ የታሰሩት እምነትን መነሻ በማድረግ፣ በተፅዕኖ መኖሪያ ቤት በማሸጥና ገንዘብ አታሎ በመውሰድ ወንጀል ተጠርጥረው መሆኑን ፖሊስ ለፍ/ቤት ያስረዳ ሲሆን ተጠርጣሪው ግን አስተባብለዋል፡፡
ባለፈው ረቡዕ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ዘንድ በአጥማቂነት የሚታወቁት መምህር ግርማ ወንድሙ፤ በተጠረጠሩበት ወንጀል ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ያስፈልገኛል በማለቱ ፍ/ቤቱ 7 ቀን ሰጥቷል፡፡
በተጠርጣሪው ላይ እየተጣራ ያለው የፖሊስ የምርመራ መዝገብ፤ መስከረም 2006 ዓ.ም አቶ በላይነህ ከበደ የተባሉ ግለሰብን ሃይማኖትና እምነትን መነሻ በማድረግ በየካ ክፍለ ከተማ ወሰን ግሮሰሪ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ላይ ከሚገኝ መኖሪያ ቤቱ እስከ ጥር 30 ቀን 2006 ዓ.ም ሸጦ ካልወጡ አስከሬናቸው መውጣቱ የማይቀር መሆኑን በመንገር ግለሰቡ ቦታውን እንዲሸጡ አድርገዋል ይላል፡፡
ግለሰቡም ከባለቤታቸው ጋር በመሆን እንደተባሉት ቤቱን በ800ሺህ ብር ይሸጣሉ፡፡
 ቤቱ በተጠቀሰው ዝቅተኛ ዋጋ እንዲሸጥ ተጠርጣሪው መምህር ግርማ አስተዋጽኦ ነበራቸው ይላል የፖሊስ የምርመራ መዝገብ፡፡ ግለሰቡ ቤታቸውን ከሸጡ በኋላ ተጠርጣሪው “በራዕይ ያየሁት ቦታ “ቦሌ” አለ፤ እሱን ነው መግዛት ያለብህ፣ ቤቱ የተሸጠበትን 800ሺህ ብር አምጣና እንዲበረከትልህ ልፀልይበት” ብለው ወሰዱት፡፡ የግል ተበዳይ ገንዘባቸውን ለማስመለስ ያደረጉት ጥረት እንዳልሠመረላቸውና ከሀገር ወጥተዋል እንደተባሉ የፖሊስ ምርመራ መዝገብ ያብራራል፡፡
 የግል ተበዳይ ጉዳዩ ውሎ ሲያድር ማታለል መሆኑን በመረዳታቸው በመጋቢት 2007 ዓ.ም ወር ገደማ ለፖሊስ ያመለከቱ ሲሆን ፖሊስ ከሄዱበት ሀገር እስኪመለሱ የተበዳዩን ቃልና የምስክሮችን ቃል ሲቀበል መቆየቱን ያትታል፡፡
መምህሩ በበኩላቸው፤ ከሣሽ የተባለውን ግለሰብ ጥቁር ይሁን ቀይ አንድም ቀን አይተውት እንደማያውቁ በመግለጽ ከጀርባዬ የተሴረብኝ ሴራ አለ ሲሉ ለፍ/ቤቱ ተናግረዋል፡፡
 ጉዳዩን የያዘው የፖሊስ የምርመራ ቡድን ከትናንት በስቲያ ተጠርጣሪውን በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ወ/ችሎት ያቀረባቸው ሲሆን ግለሰቡ በተጠረጠሩበት የማታለል ወንጀል ቀሪ የምርመራ ስራ ስላለኝ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ብሎ ፍ/ቤቱን ቢጠይቅም ፍ/ቤቱ የ7 ቀን ጊዜ በመፍቀድ ጉዳዩን ለጥቅምት 25 ቀጥሯል፡፡
ተጠርጣሪው ፖሊስ የተጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የተቃወሙና የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው የጠየቁ ቢሆንም ፖሊስ በዋስ ቢለቀቁ መረጃ ያሸሹብኛል በማለቱ ፍ/ቤቱ የመምህር ግርማን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አድርጓል፡፡

ጌታቸው ሽፈራው • ‹‹ስለ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ መናገር ቀርቶ ስሙንም ማንሳት በጣም ያሳፍረኛል›› • ‹‹ጀኔራል መርዕድ ንጉሴ የውጊያ መሰናዶዎቼን ለጠላት አሳልገው ሰጥተዋል • የሀገር ደህንነት መስሪያ ቤት ፈላሻዎችን በህገ ወጥ መንገድ ሲያስተላልፍ ነበር • ፕሮፌሰር መስፍንና ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ ተጠያቂ ከተደረጉት …

ሌ/ኮ መንግስቱ ኃይለማሪያም በ‹‹ኑዛዜያቸው›› በርካቶችን ለኢትዮጵያ ውድቀት ተጠያቂ አደረጉ:: Read more »

አሜሪካ ስመጣ ሦስት ቦታ ያለው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ይማርከኛል፡፡ ላስቬጋስ  ኪዳነ ምሕረትና ቅዱስ ሚካኤል፣ ዴንቨር መድኃኔዓለምና ሚነሶታ ቅድስት ሥላሴ፡፡ ሃይማኖታቸውን የተረዱ፣ ለአገልግሎት የተጉና ምራቃቸውን የዋጡ ክርስቲያኖች ያሉበት ቦታ፡፡ ወደነዚህ ቦታዎች ስመጣ ከማስተምረው የምማረው ይበልጣል፡፡ በአስቸጋሪው የአሜሪካ ኑሮና ፈተና ውስጥ የቤተ …

ላስቬጋስ – ጎንደር (ዳንኤል ክብረት) Read more »

የአዲስ አበባ ፖሊስ መምህር ግርማ ወንድሙን በቁጥጥር ሥር አዋለ ሲል የገዢው መደብ አፈቀላጤ የሆነው ራዲዮ ፋና መምህር ግርማ የተባሉትን የሃይማኖት አባት በማጣጣል ዘገባ አስተላልፏል::ለመሆኑ መምህር ግርማ በሕወሓት ከሚመራው እና በሙስና ከተዘፈቀው የተዋህዶ መሪዎች ቡድን በላይ ሙስና እና ማጭበርበር ፈጽመው ነው …

መምህር ግርማ ወንድሙ ታሰሩ Read more »

ጥቅምት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከትናት ጀምሮ የአርበኞች ግንቦት7 አባሎች በሰገን ዞን ኮንሶ ወረዳ ውስጥ ገብተዋል በሚል የፖሊስ አባላት በከተማው የሚገኙ ወጣቶችን ሲያድኑ ከዋሉ በሁዋላ ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶችን ይዘው አስረዋል። በአካባቢው ሰሞኑን በፖሊስ አባላት ላይ የተፈጸመ የተባለ ጥቃትና ወጣቱን የሚያነሳሱ በራሪ ወረቀቶች መበተናቸው ለአሰሳው ተጨማሪ ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ነዋሪዎች …

ጥቅምት 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ረፋዱ ላይ ሰባራ ባቡር አካካቢ ከሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በመከላከያ ምስክርነት ሊቀርቡ ከነበሩት ሦስት እስረኞች መካከል፣ ሁለቱ የማምለጥ ሙከራ ሲያደርጉ አንዱ ሲገደል አንዱ ማምለጡ ተገለጸ፡፡ 

የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ሕዝብ ግንኙነት ተወካይ ምክትል ሰርጀንት ሳህለ ገብርኤል ይትባረክ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ እስረኞቹ ያመለጡት ፍርድ ቤት ደርሰው ለመውረድ ሲቃረቡ የመኪና በር በመስበር ነበር፡፡ በተለያዩ የውንብድና ወንጀሎች 31 ዓመት የተፈረደበት አንደኛው እስረኛ ሲያዝ፣ በተመሳሳይ ወንጀል የዘጠኝ ዓመት ከስድስት ወራት ፍርደኛ የሆነውና ተጨማሪ ሦስት ክሶች የነበሩበት ሁለተኛው እስረኛ ለማምለጥ ባደረገው ሙከራ ተገድሏል፡፡

እስረኛውን አሳዶ ለመያዝ ከፍተኛ ጥረት የተደረገ ቢሆንም መንደር ውስጥ በመግባቱ ሁኔታዎች አስቸጋሪ በመሆናቸው፣ በመጨረሻ መተኮስ ግድ እንደነበር የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው አስረድተዋል፡፡ ‹‹እስረኛውን ረዥም ርቀት ተከታትለነዋል፡፡ ላለመተኮስ ከፍተኛ ጥረት  ተደርጓል፡፡ ነገር ግን መንደር ውስጥ በመግባቱ የተወሰደው ዕርምጃ የግድ የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል፤›› ብለዋል፡፡

ለማምለጥ ከሞከሩት ሁለት እስረኞች ጋር በአንድ መኪና ውስጥ የነበረው ሌላ እስረኛ ለመንቀሳቀስ ምንም ዓይነት ሙከራ አድርጎ እንዳልነበር የገለጹት ምክትል ሰርጀንት ሳህለ ገብርኤል፣ ያመለጠውን እስረኛ ለመያዝ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ክትትሉ እየተደረገ ያለው ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ጋር መሆኑንና የእስረኛው ፎቶግራፎችም መበተናቸውንም አክለዋል፡፡

አልፎ አልፎ እስረኞች ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ሲሉ የማምለጥ ሙከራ እንደሚያጋጥም፣ ነገር ግን እስካሁን አምልጦ ሳይያዝ የቀረ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ ሪፖርተር የእስረኞቹን ሙሉ ስም በሚመለከት መረጃ ያለው ቢሆንም የሕዝብ ግንኙነት ተወካዩ እንዳይገለጽ ጠይቀዋል፡፡

 

1989 ዐም ነው የኤርትራ መንግስት “የቀይ ባህር ኮርፖሬሽን” የሚባል ግዙፍ የንግድ ድርጅተ አቋቁሞ እየሰራ የነበረበት ጊዜ ነው:: በርካሽ ዋጋ ከኢትዮጵያ የተለያዩ የግብርና ምርቶች እየገዛ ለዐለም የሚያቀርብበትና በአጭር ጊዜ በርካታ መቶ ሚልዮኖችን ማንቀሳቀስ የቻለበት ጊዜ ነበር፡፡ ከዚያ አንድ ዐመት ቀደም ብሎ …

71 የኤርትራ መንግስት “የቀይ ባህር ኮርፖሬሽን” ትራከሮች :- በአቶ ስየና በአቶ መለስ ጥልና መቃቃር ትልቁ መነሻ Read more »

ኣመፁ በወረዳው ትምህርት ፅህፈት ቤት ሓላፊዎችና የወረዳው ኣስተዳደር ላይ ያነፃፀረ ሲሆን በወረዳው የሚገኙ ከ53 በላይ ትምህርት ቤቶችያሉ ርእሳነ መምህራንና ኣስተማሪዎች የሚጠይቋቸው የእድገት፣ የዝውውር፣ የእርከን፣ የውጤት ተኮርና የመልካም ኣስተዳደር ጥያቄዎች በኣግባቡ ለመመለስ ባለመቻላቸው ነው። የወረዳዋ ኣስተማሪዎች ያስነሱት ጥያቄዎች በኣግባቡ ምላሽ ሊያገኙ …

በእንደርታ ወረዳ 10 ሱፐርቫይዘሮች የሚመሩት የመምህራን ኣመፅ ተነስተዋል። Read more »

የ.ተ. መ.ድ. 3ኛ ኮሚቴ በኤርትራ ውስጥ ስለሚገኘው የሰብአዊ መብት ሁኔታ ሪፖርት አድምጧል። ሪፓርቱን በተመለከተ በመንግሥታቱ ድርጅት የኤርትራ አምባሣደር ግርማ አስመሮም መልስ ሰጥተዋል።

Minilik Salsawi – የሃይል ሚዛን በጃችን ነው … ምእራባውያን ለብሄራዊ ጥቅማቸው እስከተባበርናቸው ድረስ ኢትዮጵያውያንን በፈለገው መንገድ ብንረግጥ እና ብንገዛ ተቀባይነት አናጣም … አንድ ወጥ ሃገራዊ ሳይሆን ጎሳዊ መዋቅር ዘርግተን የቀረውን ክፍል ብናሸው ብናሸብረው በራሳችን ስራ ሕዝብን ብንወነጅል ማንም ምንም የሚያመጣው …

የመብት ጥያቄዎችን በሃይል ለማድበስበስ መሞከር ፍርሃት የወለደው ፖለቲካዊ እብደት ነው:: Read more »

የወያኔ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ ውስጥ የአይሲስን አራጅ ቡድን አላማ በማስፋፋት የአይሲስ የኢትዮጵያ መቀመጫን ለመመስረት ግዛታቸውን ለመገንባት ሲሉ ደርሼባቸዋለሁ ያለውን 20 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አውያለሁ ሲል ተናገረ::ይህ ወያኔ ስለ አይሲስ ሕዋስ እና ግዛት መመስረት ሲናገር ለመጀመሪያ ጊዜው ሲሆን በደቡብ ኢትዮጵያ አይሲስ የራሱን …

አይሲስ በኢትዮጵያ የራሱን መሬት ከልሎ ራስ ገዝ አስተዳደር ሲያደራጅ ደረስኩበት ሲል ወያኔ ተናገረ:: Read more »

በኤርትራ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኋላ ሊኖር ስለሚችለው የፖለቲካ ሁኔታ መናገር ለአብዛኞቹ ኤርትራውያንም ሆነ ለውጪ ታዛቢ ቀላል ጉዳይ አይደለም። ፕሬዝዳንቱ 70ኛ የልደት በዓላቸውን ለማክበር እየተሰናዱ ነው። የጤንነታቸው ሁኔታ በሀኪም እጅ ያለ ነው። ያለፉትን በርካታ አመታት በውጪ ሀገር እየተመላለሱ ህክምና አድርገዋል። እንዳውም …

ኤርትራ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ በኋላ! (ዋዜማ ራዲዮ) Read more »

(የትነበርክ ታደለ) – ይህን ታላቅ ርእስ ለመጻፍ ስነሳ ራሴን እንደ ሰማእት ቆጥሬዋለሁ። እውነት ለመናገር አሁን ሀገራችን ባለችበት ሁኔታ ይህ ርእሰ ጉዳይ “ብሞትም ብኖርም” ተብሎ የሚጻፍ ሀሳብ ነውና እንግዲህ አምላክ ያውቃል። እና ስለ አስመሳይ የኢሃዴግ አባላት የተሰማኝን ልበል… 1) የኦሮምያ ፕሬዚዳንት …

ኢህአዴግ ማለት የአስመሳዮች ጥርቅም ነው ብል አልተሳሳትኩም! እድሜ ለአቶ ሙክታርና ለወይዘሮ አስቴር! Read more »

ጥቅምት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነዋሪዎች እንደሚሉት ከድርቁ ጋር ተያይዞ የውሃ ችግሩ በመባባሱ ፣ ህዝቡ ውሃ ለማግኘት በእጅጉ ተቸግሯል። የውሃ ችግሩ በመባባሱና በየአካባቢው የሚታየው የውሃ ጀሪካም ብዛት ” ሳምንቱን ” ቢጫው ሳምንት” አስብሎታል በማለት ነዋሪዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የውሃ ችግሩ ከሰቆጣ በተጨማሪ በተለያዩ አገሪቱ ክፍሎች ይታያል። በሌላ በኩል ደግሞ ክልሉን እመራዋለሁ የሚለው …

ጥቅምት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአርባምንጭ ምንጮች እንደተናገሩት በቅርቡ የአርበኞች ግንቦት 7 ደጋፊዎች ኢህአዴግን የሚያወግዙና ወጣቱ ለመብቱ እንዲነሳ የሚቀሰቅሱ በራሪ ወረቀቶችን ከበተኑ በሁዋላ፣ ድርጊቱን ፈጽመዋል ብለው የጠረጠሩዋቸውን ወጣቶች በጅምላ ለማሰር ከትናንት ጀምሮ አሰሳ አካሂደዋል። አሰሳውን ተከትሎ የ70 አመት አዛውንት እናትን ጨምሮ ሴቶችና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶች ተይዘዋል። ከተያዙት መካከል የሰማያዊ …

Minilik Salsawi – የደህንነት አባላት ግምገማ በጌታቸው አሰፋ ሰብሳቢነት ቀጥሏል::ትላንትና ቀዝቀዝ ብሎ የተጀመረው ግምገማ ዛሬ ላይ ተሟሙቆ የዋለ ሲሆን የደህንነት አባላቱን ከስራ የማፈናቀል ለእስር የመዳረግ እና ከደረጃ ዝቅ የማድረግ ውጤቶችን ግምገማው እንደሚወልድ ይጠበቃል::ትላንትና በሁለት የደህንነት አባላት ሞባይል ላይ የተጀመረው ግምገማ …

የደህንነት አባላቶች ስልኮቻቸውን የሚጠቀሙት የተቃዋሚዎችን ዘገባ በማየት እና በማሰራጨት ነው በሚል ተገመገሙ:: Read more »

የወያኔ ደህንነት ስብሰባና ግምገማ ተጀመረ ፍሪደም ሀውስ (Freedom House) አመታዊ ዘገባውን አወጣ የአምስቱ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የፍርድ ቤት ቀጠሮ ተላለፈ የአቮሪ ኮስት ፕሬዚዳንት በድጋሚ መመረጣቸው ተነገረ የናይጄሪያ መንግስት ቦኮሃራም ይዟቸው የነበሩ ዜጎችን አስለቀቀ በመካከለኛው አፍሪካ የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች በፈጠሩት ግጭት …

የወያኔ ደህንነት ስብሰባና ግምገማ ተጀመረ Read more »

ሚስጥራዊ መረጃው እንደሚያመለክተው ከሆነ በዛሬው እለት የተቋሙ ጀነራል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጌታቸው አሰፋ ዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ጎን በሚገኘው ቢሮአቸው የተቋሙን ከፍተኛ አመራሮችን ትዕዛዝ ለመስጠት መሰብሰባቸውንና በስብሰባውም ዳይሬክተሩ ተቋሙ ከጥቂት ወራቶች በፊት ብዛት ያላቸው አዳዲስ አባላትን መቅጠሩን እና ወደ ስራ ማሰማራቱን …

ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ቢሮ 16 የደህንነት አባላት እና አመራሮችን በስውር በቁጥጥር ስር ሊያውል ዝግጅት መጀመሩን ተጋለጠ። Read more »

ጥቅምት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኑዌር ዞን ዋና ከተማ ከሆነቸው ንያንግ 30 ኪሜ ራቅ ብሎ በሚገኘው የህንዱ ካራቱሪ ኩባንያ አጠገብ በሚገኘው አንዱራ የአነስተኛ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ዙሪያ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ሲፐርቪዥን ኢንተርፕራይዝ ሰራተኛ የሆኑት ኢንጂር ሙሉጌታ ደሳለኝ እና የጋምቤላ የእርሻ ቢሮ ሰራተኛ የነበሩት ወ/ሮ ሃይማኖት ተገድለዋል። …

ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ በሽብረተኝነት ወንጀል የተከሰሱት አቶ ደህናሁን ቤዛና አቶ ምንዳዬ ጥላሁን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ቀርበው እንዲመሰክሩ ፍርድ ቤቱ ለተለያዩ አካላት ደብዳቤ እንዲጽፍላቸው ለልደታ ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት በድጋሜ ደብዳቤ ጽፈዋል። ቃሊቲ እስር ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፣ ቃሊቲ አለመታሰራቸውን ጥቅምት 12 ፣ 2008 ዓም …

ጥቅምት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር ገዳሪፍ አቅራቢያ በተቀሰቀሰ ውጊያ 16 ሱዳናዊያን መገደላቸውን፣ 12 መቁሰላቸውን እንዲሁም 7ቱ ታግተው መወሰዳቸውንና የደረሱበት እንደማይታወቅ ከ300 በላይ የቁም ከብቶችም መዘረፉን የቀድሞው የአገሪቱ ጦር አዛዥና የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ለፓርላማ ሪፖርት አቅርበዋል። ኢስማት አብዱረሕማን ” ሽፍቶች” ያሉዋቸው መሬታችንን አሳልፈን አንሰጥም ያሉ የኢትዮጵያ አርሶ …

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የፖሊስ መርማሪ ቡድን ዛሬ ግለሰቡን በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የወንጀል ችሎት አቅርቧቸዋል።ፖሊስ ግለሰቡ በተጠረጠሩበት የማታለል ወንጀል ቀሪ የምርመራ ስራ ስላሉብኝ ተጨማሪ 14 ቀን ይፈቀድልኝ ብሏል።ተጠርጣሪው በራሳቸውና በጠበቃቸው በኩል ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ …

መምህር ግርማ ወንድሙ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።መምህር ግርማ ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄም ወድቅ ተደርጓል። …” ሆን ተብሎ ከጀርባ የተጠነሰሰብኝ ሴራ አለ ” መምህር ግርማ Read more »

በትናንትናው ዕለት አመሻሽ ላይ አስሩ የፌደራል ፖሊሶች መጀመሪያ አንድ አይሱዙ የጭነት መኪና በኃይል በማስገደድ አስቁመው የተሳፈሩ ሲሆን መኪናው መንቀሳቀስ ሲጀምር “የጫንካቸውን ፖሊሶች አራግፍ አለያ ከነንብረትህ አብረህ ትጋያለህ!” የሚል የስልክ ማስጠንቀቂያ መልዕክት ለአሽከርካሪው በመድረሱ አሽከርካሪው መኪናውን አቁሞ ፖሊሶቹን “አልሄድም” ይላቸዋል፡፡ ቀጥሎም ፌደራል ፖሊሶቹ ሾፌሩን ለማንገራገር ሞክረው ትዕዛዛቸውን በቀላሉ ሊቀበል ባለመቻሉ ስልክ ተደዋውለው ሌላ ላንድ ክሩዘር መኪና […]

ፍሪደም ሃውስ (Freedom House) መቀመጫውን እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገና በመናገር ነጻነት ላይ የሚሠራ ዓለም አቀፍ ተቋም ነው፡፡ይህ ተቋም መንግሥታት ለሕዝቦቻቸው የሚሠጡትን የኢንተርኔት ነጻነት አጥንቶ እያንዳንዱ ሀገር ያለበትን ደረጃ ‹‹Freedom on the net 2015 ›› በሚል ርዕስ ስር ሪፖርት አውጥቷል፡፡ በዚህ ሪፖርት ሰንጠረዥ‹‹ኢትዮጵያ ከቻይና፣ከሦሪያ እና ከኢራቅ ቀጥሎ ምንም ዓይነት የኢንተርኔት ነጻነት የሌለባት አገር ተብላለች፡፡ Listen

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር በትጥቅ ትግል መንግስት ለመቀየር የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ኃይሎች ውጤት አያመጡም ብለዋል። በአሥመራ የሚገኘውን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጨምሮ የሁለት ድርጅቶች ምላሽ ሰጥተዋል።

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ፣ “የአመጹ ወጣቶችን አጋልጡ” በሚል የመከላከያ ሰራዊት አባላት በግለሰቦች ቤት እየገቡ አዛውንቶችን፣ ወጣቶችንና ሴቶችን እየደበደቡ ሲያስሩ ከሰነበቱ በሁዋላ ትናንት ከምሽቱ ሶስት ሰአት ጀምሮ፣ ከጫካ በመጡ ወጣቶችና በመከላከያ ፖሊስ አባላት መካከል ለሰአታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል። ኢሳት ከተለያዩ ነዋሪዎች ባደረገው ማጣራት ከቴፒ 7 ኪሎሜትር …

በስልጤ ዞን በሁልባራግ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የሂጃብ ገፈፋውን በመቃወም በአደባባይ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ እንደነበር ተገለፀ በደቡብ ክልል በስልጤ ዞን የሂጃብ ገፈፋው ተጠናክሮ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት በከተማው ህዝበ ሙስሊም እና በመንግስት ሃይሎች መካከል ግጭት እየተፈጠረ መሆኑ ታውቋል፡፡ በስልጤ ዞን የሚገኙ የተለያዩ …

በስልጤ ዞን የሂጃብ ገፈፋውን በመቃወም በአደባባይ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ እንደነበር ተገለፀ:: Read more »

በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ -5ኛ መዝገብ ለተከሰሱት አቶ አሸናፊ አካሉ (2ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ደናሁን ቤዛ (3ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን (4ኛ ተከሳሽ) እናአቶ አንሙት የኔዋስ (5ኛ ተከሳሽ) በመከላከያ ምስክርነት ተጠቅሰው በነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ የልደታ ፍርድ ቤት …

በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ ልደታ ምድብ 19ኛው ወንጀል ችሎት ለሶስት አካላት ትዕዛዝ እንዲሰጥ ተጠየቀ Read more »

የሃገራችን ፓርላማ መስከረም 24/2008 በአምስተኛ ዘመን የመጀመሪያ ጉባኤው የሃገሪቱን ጠ/ሚኒስትር ሾሞ፤ ጠ/ሚኒስትሩ ደግሞ 30 የካቢኔ አባላትን ሹመት በማግስቱ አቅርበው አስፀድቀዋል፡፡ ተሿሚ የካቢኔ አባላቱ 30 የደረሱት በአስፈፃሚው ውስጥ አዳዲስ የሚኒስትር መስሪያ ቤቶች በመዋቀራቸው ነው፡፡ ከሚኒስትር መስሪያ ቤቶች በተጨማሪ በኤጀንሲ፣በባለስልጣን እና ኮርፖሬሽን …

የአዲሱ መዋቅር ብርታት ድካሞች(የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ላይ የተስተናገደ) Read more »

ለጤንነትዎ ያንብቡ : ለካንሰር ያጋልጣሉ የተባሉ እና በፍጹም ከንፈሮቻችንን መሻገር የሌለባቸው ለጤንነት እጅግ አደገኛ ንጥረ ነገሮችን የተሸከሙ አስር የምግቦች አይነቶች ከዚህ ሊንክ በዝርዝር ቀርበዋል:- http://betinews.com/?p=3818 Cancer Causing : 10 Toxic Foods That Should Never Cross Your Lips

የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ የተበየነላቸው የአንድነት፣ የሰማያዊ እና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች ላይ አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆ ጉዳያቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት አምስት ተከሳሾች ለጥቅምት 22/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡ …

እነ ሀብታሙ አያሌው ለጥቅምት 22 ተቀጠሩ ::ማረሚያ ቤት እነ ሀብታሙን አላቀረባቸውም Read more »

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – እንደኔ ሐይለማርያም ደሳለኝ የሚናገረው ንግግር ሁሉ ጊዜውን ያላገናዘበ ሕዝብ የሚያውቀውን ጉዳይ ያልመዘነ በእውነት ላይ ያልተመሰረተ በደመነፍስ የሚናገረው የጅል ፖለቲካ ድምር ውጤት ነው::የተመከረውን እና የተባለውን ሁሉ መልሶ የሚያስተጋባ በጥቂት ቡድናዊ ማፊያዎች የሚነዳ የአገር መሪ አለ ብሎ …

የሐይለማርያም ደሳለኝ ጅል ፖለቲካ ሕወሓት ከሚተገብረው ሐቅ የተለየ ነው:: Read more »

ኢሕአዴግ ሥልጣን ይዞ የሽግግር መንግሥቱ ሥራ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ ቁጥራቸው በጣም የበዛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተመሥርተዋል፡፡ ኅብረ ብሔራዊና ብሔር ተኮር የሆኑት እነዚህ ፓርቲዎች ተመሥርተው ሥራ መጀመራቸው በበጎ ጎኑ የሚወሳ ቢሆንም፣ ለረጂም ጊዜያት የተስተዋሉባቸው ችግሮች ግን ሳይቀረፉ ቀጥለዋል፡፡ በምርጫ ጊዜ እንደ መስቀል …

ለመርህ የቆሙ ጠንካራ እንጂ፣ በደመነፍስ የሚመሩና በጥላቻ የታወሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለፖለቲካው አይጠቅሙም፡፡ Read more »

በየዓመቱስለጡት ጥቅምት ወር ካንሰር ግንዛቤ የማስጨበጫ እንቅስቃሴዎች በተለያዩ ሃገራት ይካሄዳሉ። አመጋገብ ላይ ጥንቃቄ ከማድረግ አንስቶ የሰዉነት እንቅስቃሴ ማዘዉተር የትኛዉንም የአካል ክፍል ከሚያጠቃ ካንሰር ለመከላከል የሚረዳ ተቀዳሚ ርምጃ መሆኑን ሃኪሞች ይመክራሉ።

Prof. Merara Gudina
የኦሮሞ ፌደራሊስት ሊቀመንበር እና የመድረክ የአመራር አባል የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና ይህን ምላሽ የሰጡት ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የቀረበውን የውይይት ግብዣ ተቃዋሚዎች ውድቅ ማድረጋቸውን ለፓርላማ አባላት መናገራቸውን ተከትሎ ነው። መንግስት በጠራው የአምስት ኣመታት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውይይት ላይ ያልተሳተፉ እንደመድረክ፣ ሰማያዊ እና መኢአድ ያሉ ፓርቲዎች ያቀረቡት ምክንያተ ውሃ ያማያነሳ ነው ያሉት አቶ ሃይለማርያም ፣ ፓርቲዎቹ ያልተሳተፉት በሕጋዊ መንገድ የተመረጠ መንግስት አይደለም በማለት መሆኑን ጠቅሰው ወደፊት ከየትኛው መንግስት ጋር እንደሚወያዩ እናያለን ሲሉ ዝተዋል፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ከ30 ዓመታት በፊት የክብር ዶክተር ወ/ሮ አበበች ጎበና ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ያቀናሉ። እናም ያኔ ወቅቱ በሀገሪቱ የረሃብ አደጋ ያጠላበት ጊዜ ነበርና አንዲት ሕፃን የእናቷ አስክሬን እቅፍ ስር ሆና ጡት ለመጥባት ትሞክራለች። ይህ ትዕይንት እጅግ ከፍተኛ ሐዘን ውስጥ ይከታቸዋል።

ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ሽመልስ ፣ አቶ በረከት ስምኦን ከኮምኒኬሽን ሚኒስትርነት ተነስተው በአቶ ሬድዋን ሁሴን ከተተኩበት ካለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ወዲህ ከአቶ ሬድዋን ጋር መስማማት ባለመቻላቸው በስራ ገበታቸው ላይ የሚገኙት አልፎ አልፎ ነበር፡፡ የሁለቱ ሚኒስትሮች አለመግባባት በኢሳት ከቀረበ በኃላ ችግር የለብንም ለማለት ለአንድ ቀን አብረው መግለጫ በመስጠት ጎን ለጎን …