በቤልጂዬም የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የኢድ-አልፈጥርን በዓል በደማቅ ሁኔታ አከበሩ። በበዓሉ ላይ ተጋብዘው የነበሩት በቤልጂዬም የወያኔ ኤምባሲ ሰራተኞች የግንቦት7 አመራር አባል ባለበት ቦታ መገኘት ያስጠይቀናል ሲሉ አዳራሹን ጥለው ፈረጠጡ
ዕሁድ ጥቅምት 26 ቀን ተከብሮ የዋለውን የኢድ-አልፈጥርን በዓል በቤልጂዬም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች አንድ ላይ በመሰባሰብ በደማቅ ሁኔታ ማክበራቸውን የግንቦት 7 ዘጋቢ ከስፍራው በላከልን ሪፖርት ገለጸ። በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በየአመቱ በደማቅ ሁኔታ በሚከበረው በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ ሥነሥርዓት ላይ የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች መካከል እልቂት ሊያስነሳ የሚችል ክፍፍል ሆን ብሎ እየፈጠረ መሆኑን በድምጽና በቪዲዮ ማስረጃ የተደገፈ […]