በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ለመከላከል ወይም ሳይከላከሉ በነፃ ለመሰናበት ውሳኔ ዛሬ ለ35ተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት አራቱ በእስር የሚገኙት ጦማርያን በድጋሚ በተለዋጭ ቀጠሮ ተሸኝተዋል። በዛሬው ውሎ ችሎቱ ያልተሰየመ ሲሆን ተከሳሾች እና ጠበቆች በቢሮ ተጠርተው ዳኞች ተሟልተው ስላልተገኙ ችሎቱ ለመሰየም አለመቻሉን ዶክመንቶችን ማየትና ውሳኔውን ፅፎ ማጠናቀቅ አሁንም እንዳልቻሉ በመግለፅ ዳኛ ዘሪሁን ለጷግሜ 2 ተለዋጭ ቀጠሮ […]

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የፍርድ ቤት ውሎ (Update) #Freezone9bloggers በዛሬው እለት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የወያኔ ካንጋሮ ፍርድ ቤት ቀርበዋል::አራቱ ጦማርያን በፍቃዱ:ናትናኤል:አቤል:እና አጥናፍ በጥቁር ሱፍ ደምቀው በፍርድ ቤቱ ተገኝንዋል::ንጽሕናቸውን በተለያየ መንገድ እየገለጹ ያሉት እና የፍርድ ቤቱን ነጻ አለመሆን በተግባር ያሳዩት ጦማርያን በራስ …

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የፍርድ ቤት ውሎ – የካንጋሮ ፍርድ ቤቱ ድራማ – ቀጠሮ ለ36ኛ ጊዜ ጳጉሜ 2 2007 Read more »

በገዢው ስራዓት የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ እየተካሄደ ባለው ሰፊ የዓመቱ ግምገማ “የተቃዋሚዎች ሬድዮ መስማት” እንደዋነኛ መገምገሚያ ነጥብ ሆኖ መነሳቱን ተገለፀ።በምንጮቻችን መረጃ መሰረት- በሁሉም የስርዓቱ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እየተካሄደ ያለውን መጠነ ሰፊ የዓመቱ ግምገማ ወታደሩ ያለማቋረጥ እየፈረሰ በመጥፋት ላይ ያለው የትጥቅ ትግል እያካሄዱ በሚገኙ ድርጅቶች የሚሰራጨውን ሬድዮ መስማት ዋናው ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ ስለሆነ ለምን ታዳምጣላችሁ፤ እነማን ናቸው የሚያዳምጡት መታወቅ አለባቸው በማለት እየተካሄደ ባለው ስብሰባ የሰራዊቱ አዛዦች ራሳቸው […]

ኢትዬጲያዊያን ሙስሊሞች አሁን በሃገራችን ያለንበት ተጨባጭ ይህን ይመስላል አቡ ዳውድ ኡስማን ወደፊት ለመጓዝ አሁን ያለንበትን ተጨባጨ መመዘን ተገቢ ነው፡፡ የተጋረጠብንን ችግሮችም ለመጋፈጥ እና ችግሩን ጥሶ ለማለፍ ያሉትን ችግሮች ማወቁም ተገቢ ነው፡፡ ሙስሊሙ ማህበረሰብ 3 ቀላል ጥያቄዎችን ለመንግስት አቅርቧል፡፡ ይህም ጥያቄዎች …

ኢትዬጲያዊያን ሙስሊሞች አሁን በሃገራችን ያለንበት ተጨባጭ ይህን ይመስላል :: (አቡ ዳውድ ኡስማን ) Read more »

– የወያኔው ጉባኤ ጥበቃና ጸጥታ ውዝግብ አስነስቷል – የወያኔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በካድሬዎች እየተተቸ ነው – ሱማሊያ ውስጥ ሰርገኞችን የገደሉ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት ለፍርድ ቀረቡ – በደቡብ ሱዳን የመገናኚያ ብዙሀን አባላት የዜና ማእቀብ አድማ አደረጉ – በሰሜን …

የወያኔው ጉባኤ ጥበቃና ጸጥታ ውዝግብ አስነስቷል:: የወያኔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በካድሬዎች እየተተቸ ነው Read more »

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በድጋሜ የሰማያዊ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በድጋሜ የሰማያዊ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ያደረገው ሰማያዊ ፓርቲ ኢ/ር ይልቃል ጌትነትን በድጋሜ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡ ትናንት ነሀሴ 16/2007 ዓ.ም ጉባኤውን የጀመረው ፓርቲው በዛሬው ሁለተኛና የማጠቃለያ …

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በድጋሜ የሰማያዊ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ Read more »

‹‹ታግዬ ለውጥ ማምጣት እችላለሁ!›› የሚል ትውልድ አይሸነፍም! የአስተሳሰብ የበላይነት የትግል እና የድል መሰረት ነው! እሁድ ነሐሴ 17/2007 ማንኛውም የመብት ትግል የሚጀምረው በበደል ነው፡፡ አምባገነኖች በደልን የሚያደርሱት እጅግ ስልታዊ በሆነ መንገድ በመሆኑና ለዚህ በደልም ሽፋን ስለሚያደርጉለት ብዙዎች የሚበደሉት እየተበደሉ መሆናቸውን ሳይረዱ …

ታግዬ ለውጥ ማምጣት እችላለሁ!›› የሚል ትውልድ አይሸነፍም! – ድምፃችን ይሰማ Read more »

ዛሬ እንደወትሮዬ አብርሀ ደስታን ለመጠየቅ ወደ ቃሊቲ አምርቼ ነበር። ታዲያ አብርሀን ሆነ መሰሎቹን ለመጠየቅ እንዲህ በቀላሉ የሚቻል አይደለም። በጥብቅ ከሚጠበቀው ቃሊቲ ውስጥ ለመጠየቅ የሚፈቀደው ከ 6:00 – 6:30 ያለችን 30 ደቂቃ ብቻ ስትሆን እሱም በር ላይ ቆመው የአይንህ ቀለም አላማረንም …

አመክሮ ካልታሰበ አብርሃ ደስታ ጥቅምት 24 2008 የሽዋስ እና ዳንኤል ነሃሴ 30 ይፈታሉ:: Read more »

በሁለተኛው ቀን ውሎ የሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ቀጣይ የፓርቲውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ የጉባኤው አባላት አጠቃላይ ውይይት እየተደረጉ ይገኛል፡፡ በቀጣይም የብሄራዊ ምክር ቤት፣ የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን አባላት እና የፓርቲው ሊቀመንበር ጥቆማ እና አስመራጭ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ይደረጋል፡፡ ጠቅላላ ጉባኤው ቀጣዩን የሰማያዊ ፓርቲ …

የሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ በሁለተኛው ቀን ውሎ Read more »

#Ethiopia ከኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ በሳተላይት የሚሰራጭ የራዲዮ ፕሮግራም (EPRP’s Satellite Radio transmissions to Ethiopia and Horn of Africa.) የነሐሴ 15 ቀን 2007 ዓ.ም.ዜና (August 21, 2015 News) – ወያኔ ውስጥ ውስጡን እርዳታ እየጠየቀ ነው – የወያኔ ምክር ቤት ስብሰባ …

ከኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ በሳተላይት የሚሰራጭ የራዲዮ ፕሮግራም Read more »

‹‹መጠየቅ ካለብኝ በክልል እንጂ በፌዴራል አይደለም›› አቶ ወንድሙ ቢራቱ

ለመንግሥት መግባት የነበረበትን ተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች የመንግሥት የግብር ገቢዎች በማጭበርበር በግላቸውና በዘመዶቻቸው ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ በማካበት በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩት፣

የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ወንድሙ ቢራቱ ሰው በመግደል ወንጀል መጠርጠራቸው ለፍርድ ቤት ተገለጸ፡፡

ነሐሴ 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ውለው ነሐሴ 4 ቀን 2007 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው 11 ቀናት ለተጨማሪ ምርመራ ተሰጥቶባቸው የነበሩት አቶ ወንድሙ፣ በሰው መግደል ወንጀል የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኖች ያደረጉት የምርመራ መዝገብ ቀርቦ እየተጣራባቸው መሆኑ ተነግሯል፡፡ 

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ነሐሴ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት ተጠርጣሪውን አቅርቧቸዋል፡፡ ቀደም ብሎ በተፈቀደለት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ 13 ሚሊዮን ብር የተንቀሳቀሰበት ሰነድ ከባንክ ተፈልጐ መሰባሰቡን፣ በፌዴራልና በክልል ባሏቸው ቤቶች ብርበራ መካሄዱን፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የሲዲ መረጃ መሰብሰቡንና የሁለት ምስክሮችን ቃለ መቀበሉን መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ አስረድቶ፣ የሚቀረው ምርመራ እንዳለ በመግለጽ ተጨማሪ 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠይቋል፡፡

መርማሪ ቡድኑ ተጨማሪ ቀናት የጠየቀበትን ምክንያት ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው፣ ከአዲስ አበባና ከፌዴራል ፖሊስ የነፍስ ግድያ ወንጀል ምርመራ መዝገብ መጥቶለት፣ ምርመራው በደንብ መካሄዱን መገምገም ከፌዴራልና ከክልል የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ተጨማሪ የሰነድ ማስረጃዎች መሰብሰብ፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ የተለያዩ ሰነዶችን መሰብሰብ፣ ከኦሮሚያ ገቢዎች የኢንስፔክሽን ሪፖርት መሰብሰብና ሌሎች ተጠርጣሪዎችን መያዝ እንደሚቀረው አስረድቷል፡፡ 

በተጠርጣሪው ዘጠኝ ቤቶችና በአራት ከተሞች የተደረገውን የብርበራ መረጃ መተንተን፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሰባሰቡትን የመሬትና የቤት ባለቤትነት ሰነድና  ከተለያዩ ባንኮች ገንዘብ የተቀባበሉባቸውን ደረሰኞች ማስረጃ መሰብሰብ እንደሚቀረው፣ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት የተጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ቀን እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡

አቶ ወንድሙ በበኩላቸው ባቀረቡት ተቃውሞ፣ መርማሪው የፈለገውን ሰነድም ሆነ ሌላ ነገር ማግኘቱን ገልጸዋል፡፡ መርመሪዎች እሳቸውን ካሰሩ በኋላ መኖሪያ ቤታቸው በመሄድ የአምስት ዓመት ሕፃን ልጃቸው ላይ ሽጉጥ በመደቀን ያደረጉትን ማስፈራራት አምርረው ተቃውመዋል፡፡

ከታሰሩበት ዕለት ጀምሮ ማንም ቤተሰብ እንዳልጠየቃቸው፣ ምክንያቱ ደግሞ መርማሪዎቹ እንዳስፈራሯቸው መስማታቸውን ተናግረዋል፡፡ እሳቸው የክልል ተሿሚና የካቢኔ አባል መሆናቸውን በመግለጽ፣ መጠየቅ ካለባቸውም በክልል እንጂ በፌዴራል አለመሆኑን አስረድተዋል፡፡ ኮሚሽኑ በመገናኛ ብዙኃን ስማቸውን እያጠፋ መሆኑን በመግለጽ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡

የኮሚሽኑ መርማሪ በበኩላቸው አቶ ወንድሙ ያቀረቡትን አቤቱታ የሰሙት በዕለቱ ለችሎቱ ሲያስረዱ መሆኑን ገልጸው፣ እሳቸው እንዳሉት ሆኖ ከተገኘ ኮሚሽኑ በድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ ዕርምጃ እንደሚወስድ አሳውቀዋል፡፡ ሥልጣኑ የክልል ነው ስለመባሉ ግን፣ የግብር ጉዳይ የፌዴራሉ ጭምር መሆኑን በመጥቀስ አስረድተዋል፡፡ የቫትንና የጉምሩክ ቀረጥን በሚመለከት የማየት ሥልጣን የፌዴራል ፍርድ ቤቶች መሆኑንም አክለዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ አቶ ወንድሙ ያቀረቡትን አቤቱታ በሚመለከት በሰጠው ትዕዛዝ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው መከበር እንዳለበት አሳስቦ በቤተሰብ፣ በዘመዶቻቸው፣ በሃይማኖት አባትና በሕግ አማካሪያቸው የመጐብኘት መብት እንዳላቸው በመግለጽ ኮሚሽኑ ተግባራዊ እንዲያደርግ አዟል፡፡ 

በሕፃን ልጃቸው ላይ ተደረገ የተባለው እውነት ከሆነና ማስረጃ ከቀረበ ዕርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቆ፣ የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን በሕግና በአግባቡ መመርመር እንዳለበት፣ ከዚያ ውጪ የሆነ በግዳጅና በኃይል የሚገኝ መረጃን ውድቅ እንደሚያደርግ በማሳሰብ፣ መርማሪ ቡድኑ ለጠየቀው ተጨማሪ ምርመራ አሥር ቀናትን ፈቅዷል፡፡ 

 

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ከአክሰስ ቦርድ ሰብሳቢነታቸው ተነሱ

‹‹መንግሥት አክሲዮን ማኅበሩን ለማፍረስ በሚደረግ እንቅስቃሴ ላይ ጥብቅ ዕርምጃ ይወስዳል›› አቶ ኑረዲን መሐመድ፣ የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ

በድንገት ከአገር ወጥተው በተባበሩት ኤምሬት ዱባይ ከተማ ለሁለት ዓመታት ከቆዩ በኋላ ከመንግሥት ጋር ባደረጉት ድርድር ከለላ ተሰጥቷቸው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣

አገር ውስጥ ከተመለሱ በኋላ ቀድሞ ወደነበሩበት የአክሰስ ሪል ስቴት አክሲዮን ማኅበር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የተሾሙ ቢሆንም፣ ‹‹ምንም ዓይነት ሥራ አልሠሩም›› ተብለው ከሰብሳቢነታቸው ተነሱ፡፡

የቦርድ አባላት ነሐሴ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ አቶ ኤርሚያስን ከቦርድ ሰብሳቢነታቸው ያነሷቸው፣ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ከተሾሙ ከመጋቢት 26 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በእሳቸው ሰብሳቢነት በርካታ ስብሰባዎችን ያደረጉ ቢሆንም፣ በሥነ ሥርዓት ጉዳዮችና አሉባልታ ወሬዎች ላይ ከመነታረክ ያለፈ ምንም ዓይነት ቁምነገር አለመሥራታቸውን የቦርዱ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባዔ ያስረዳል፡፡ አቶ ኤርሚያስ በሕግና በሥርዓት ሊሠሩ ባለመቻላቸው፣ ቦርዱ የኩባንያውን ችግር ለመፍታት በመንግሥት ለተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ በማሳወቁ ኮሚቴው መመርያ ሰጥቶ እንደነበርም በቃለ ጉባዔው ተገልጿል፡፡ ኮሚቴው በሰጠው መመርያ ቦርዱ ስለ አክሰስ ሪል ስቴት አካሄድ ፍኖተ ካርታ እንዲያቀርብ አዞ የነበረ ቢሆንም፣ ጥቃቅንና የትም የማያደርሱ ድርጅቱን ሥጋት ላይ የሚጥሉ ነገሮች ከመነሳታቸው ባለፈ ፋይዳ ያለው ነገር ሊሠሩ ባለመቻላቸው ከቦርድ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን የቦርዱ ቃለ ጉባዔ አስታውቋል፡፡ አክሰስ ሪል ስቴት በአቶ ኤርሚያስ ሲመራ ወደ ድርጅቱ ካዝና መግባት ያለባቸውን ተሰብሳቢ ሒሳቦች ከማንሳት ይልቅ ዕዳ መቀበልን እንዲያስቀድም መደረጉን ቦርዱ ገልጿል፡፡ ድርጅቱን ከውድቀት ሊያነሳ የሚችል ብዙ ተሰብሳቢ በሕጋዊ ሰነድ የተያዘ ገንዘብ ቢኖርም፣ በእሱ ጉዳይ ላይ ውይይት አለመደረጉንም ጠቁሟል፡ 

አቶ ኤርሚያስ ወደ አገር ቤት የተመለሱበት ዓላማ እንዲያሳካ በሚል ቦርዱ ብዙ ነገሮችን እያየ እንዳላየ ማለፉን ጠቁሞ፣ አሁን ግን ሥጋው መሬት ላይ እያለ የደረቀ ቋንጣ እያወረደ መሆኑን በመገንዘብ ዕርምጃውን ለመውሰድ መገደዱን ገልጿል፡፡ አቶ ኤርሚያስ ያለ ቦርዱ ተሳትፎ በራሳቸው ለተለያዩ ድርጅቶች ደብዳቤ መጻፋቸው፣ ቅጥር ማካሄዳቸውና ‹ፒንግል ሪል ስቴት› ከተባለ የቻይና ኩባንያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን ቦርዱ ጠቁሞ፣ ነገር ግን ኩባንያው በሕይወት ይኑር አይኑር የሚታወቅ ነገር እንደሌለ አስታውቋል፡፡ በአጠቃላይ አቶ ኤርሚያስ ከነሐሴ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ከቦርድ ሰብሳቢነታቸው ተነስተው ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት ወ/ሮ መብራት ወልደ ትንሳዔ በሰብሳቢነት እንዲመሩ በመስማማት መወሰኑን አስታውቋል፡፡ 

አቶ ኤርሚያስ መሥራችና የቦርድ ሊቀመንበር ከነበሩበት አክሰስ ሪል ስቴት፣ በአገር ውስጥና በተለያዩ አገሮች የሚኖሩ ከ2,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች የቤት ግዢ የፈጸሙ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ቤትም ሆነ ገንዘባቸውን አለማግኘታቸውን እየገለጹ ነው፡፡ አቶ ኤርሚያስ በድንገት ከአገር ሲወጡ ቤት ገዢዎቹ የተለያዩ ተቃውሞዎችን ሲያቀርቡ ከርመው፣ በመጨረሻ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ከአቶ ኤርሚያስ ጋር በመደራደር ለተለያዩ ግለሰቦች ቆርጠውት በነበረ ደረቅ ቼክ ምክንያት እንደማይታሰሩ ዋስትና ተሰጥቷቸው፣ በየካቲት ወር 2007 ዓ.ም. ወደ አገር ቤት ተመልሰዋል፡፡

አቶ ኤርሚያስ በወቅቱ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ከየካቲት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራ እንደሚጀምሩና ማንኛውም ቤት ገዢ የፈለገውን ማለትም ቤቱን ወይም ገንዘቡን ከነወለዱ እንደሚመልሱ ቃል መግባታቸው በወቅቱ ተዘግቧል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ቤት ገዢዎች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አቶ ኤርሚያስ እንኳን ገንዘብ ሊመልሱና ስለቤት ሊያናግሯቸው ቀርቶ በአካል አይተዋቸው እንደማያውቁ እየገለጹ ነው፡፡ መንግሥት የሰጣቸውን ተስፋም ማየት ባለመቻላቸው ተስፋ እየቆረጡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአጭር ጊዜ ተብሎ ላለፉት ስድስት ወራት ምንም ነገር አለማየታቸውን አስረድተዋል፡፡ 

የአቶ ኤርሚያስ ፍላጐት በተለያዩ መንገዶች ነገሮችን በማጓተት ድርጅቱ እንዲፈርስና ከተጠያቂነት ለመዳን ስለሆነ፣ ቃል የገባው መንግሥት በነገሩ ላይ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡ 

በቦርዱ ጽሕፈት ቤት ለሚሠሩ 13 ሠራተኞች የሰኔና የሐምሌ ወር ደመወዝ መክፈል ሳይቻል ቀርቶ ቴክኒክ ኮሚቴውና ከቤት ገዢዎች ለተለያዩ ወጪዎች ከሰበሰበው ገንዘብ አክሲዮን ማኅበሩ ተበድሮ መክፈሉን አስረድተዋል፡፡ ይኼ የሚያሳየው ድርጅቱ ችግር ውስጥ መሆኑን እንደሆነ አስረድተው መንግሥት አስቸኳይ ውሳኔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ 

የቴክኒክ ኮሚቴው ሰብሳቢ የንግድ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ኑረዲን መሐመድ ግን በቤት ገዢዎቹም ሆነ በቦርዱ ሐሳብ አይስማሙም፡፡ እሳቸው እንደሚሉት ሰው የፈለገውን ቢያወራ ኮሚቴው መሥራት የሚችለውን እየሠራ እንደሆነና በሥራውም ውጤታማ መሆኑን ነው፡፡ 

ከየአቅጣጫው እየጮሁ የሚገኙት ከቤት ገዢዎቹ አሥር በመቶ የማይሆኑትና አቶ ኤርሚያስ ሲነኩ የሚነኩ ሰዎች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ አቶ ኤርሚያስ የሕግ ከለላ የተሰጣቸው ሥራዎች ተስተካክለው እንዲሄዱ እንጂ ከሕግ ተጠያቂነት ለማዳን አለመሆኑን የገለጹት አቶ ኑረዲን፣ በአቶ ኤርሚያስ በኩል ስላሉ ሰዎች መረጃ መጠየቅ ሲጀመር የእሳቱ ወላፈን የሚነካቸው ሰዎች ብዙ ነገር ለማድረግ እየጣሩና እየተወራጩ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ከአንድ ወይም ሁለት ሳምንት በኋላ በተለይ አምቼ አካባቢ ያለው ፕሮጀክት ይፋ እንደሚደረግና ሥራ እንደሚጀመር የጠቆሙት ሰብሳቢው ቦርዱ፣ የቦርዱ አባላትና አስፈጻሚው የየራሳቸው አጀንዳ ስላላቸው ምንም ነገር እንዳልተሠራ የሚያስወሩት ወሬ እንደሚቆም ተናግረዋል፡፡ ሁሉም የሚሮጠው የራሱን መብት ለማስከበር መሆኑን ጠቁመው መንግሥት ግን ተረጋግቶና ሁሉንም ነገር በአግባቡ በመሥራት እያንዳንዷን ነገር ማስተማሪያ ማድረግ እንደሚፈልግ ገልጸዋል፡፡ 

አክሲዮን ማኅበሩ ከፈረሰ ተጠያቂነት ስለማይኖር በንግድ ሚኒስቴር የአክሲዮን ማኅበራት ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት የመጀመሪያ የቤት ሥራው ጥንቃቄ አድርጐ ጅምሩን ዳር ማድረስ መሆኑንም አቶ ኑረዲን አስረድተዋል፡፡ አክሲዮን ማኅበሩን ለማፍረስ የሚደረግ እንቅስቃሴ ከታየ መንግሥት ጥብቅ ዕርምጃ እንደሚወስድም አስረድተዋል፡፡ የሆነ ያልሆነ መረጃ ወጥቶ ቤት ገዢውን ተስፋ የሚያስቆርጥ ወሬ እንደሚሰማ የገለጹት አቶ ኑረዲን፣ መንግሥት አቶ ኤርሚያስ ሳይኖሩ ኃላፊነት መውሰዱን ቤት ገዢው መዘንጋት እንደሌለበት አስታውሰዋል፡፡

አቶ ኤርሚያስ ወደ አገር ቤት እንዲመጡ የተደረገው ሥራ እንዲሠሩ፣ ሚስጥሮችን እንዲያወጡና ሦስተኛ ወገኖችን እንዲታገሉ መሆኑን የገለጹት አቶ ኑረዲን፣ ቦርዱ ራሱ ሾሞ ራሱ እንዳወረዳቸው መግለጹ አግባብ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሌላ መሾምም ሆነ መነሳት ካለባቸው በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽሕፈት ቤት የፀደቀ ሰነድ መኖር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ይኼ ባልሆነበት ሁኔታ ስለሚካሄደው ነገር የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ አሁን በቦርዱም ሆነ በጥቂት ቤት ገዢዎች እየተደረገ ያለው ነገር ሥራውን የሚያስትና የሚያደናቅፍ አለመሆኑን አቶ ኑረዲን ተናግረዋል፡፡     

ቦርዱ ባሳለፈው ውሳኔና ቤት ገዥዎች እያቀረቡት ስላለው ተቃውሞ ምላሽ እንዲሰጡ አቶ ኤርሚያስን ሪፖርተር ቢሮቸአው ድረስ በመሄድና በስልክ ጭምር ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡    

 

እነ ሃብታሙ አያሌውን ለመፍታት/ከበር መልሶ ለመያዝ/ የደህንነት ቢሮ ትእዛዝ እየተጠበቀ ነው:: የቀረበባቸው ክስ ከጥርጣሬ ባለፈ በሽብርተኝነት ላይ ተሳትፎ አላደረጉም በሚል በነጻ እንዲሰናበቱ ከተደረጉት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ለመፍታት የደህንነት ቢሮ ትእዛዝ እየተጠበቀ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በፍርድ ቤት መዳፈር ወንጀል ተለጥፎባቸው እዛው …

እነ ሃብታሙ አያሌውን ለመፍታት/ከበር መልሶ ለመያዝ/ የደህንነት ቢሮ ትእዛዝ እየተጠበቀ ነው:: Read more »

በደ/ወሎ ለጋንቦ ወረዳ የመቅደላ አንባ ዩንቨርስቲ የመሰረት ድንጋይ ወደ ቦረና በመዛወሩ የተነሳዉን ሰላማዊ ስልፍ ምክናየት በማድረግ ከጊባ ከተማ፣ጭሮ ከተማናአቅስታ ከተማ በፌደራል ፖሊስ እየታፈሱ ብዙ ወጣቶች መታሰራቸዉ ይታወቃል። በደ/ወሎ ለጋቦ ወረዳ መንግስት በፈጠረዉ በመቅደላ አባ ዩንቨርስቲ ችግር ምክናየት ሲታፈሱ የከረሙት ቁጥራቸዉ …

ከደቡብ ወሎ ዩንቨርስቲ የታፈሱ ወጣቶች ወደ ደሴ እስር ቤት ተወሰዱ:: Read more »

ነሐሴ 14ቀን 2007 ዓ.ም. ርዕስ አንቀጽ · የወያኔ የፖለቲካ ፍርድ ቤት አምስት ፖለቲከኞችን ከሽብርተኛ ወንጀል ነጻ ናቸው አለ · በአዲስ አበባ የአምባገነኑ መለሰ ዜናዊ 3ኛ ሙት ዓመት በግዳጅ ታሰበ · የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምርቱን አቆመ · የአዲስ አበባ ፖሊስ አዲስ …

የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምርቱን አቆመ · የአዲስ አበባ ፖሊስ አዲስ የፖሊስ ቅጥር ማስታወቂያ ሊያወጣ ነው (Finote Democracy) Read more »

የደቡብ ሱዳን ጦርነት በእስከአሁን ሂደት ከ 10 ሺህ በላይ ዜጎችን ህይወት መቅጠፉና በመቶ ሺህዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ስደት መንስኤ መሆኑ አይዘነጋም ይሁን እንጂ ለሀገሪቱ ሰላም ያመጣል ተብሎ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት የቅርብ ጊዜው የአዲስ አበባ ድርድር ውጤቱ የተጠበቀውን ያክል መሆን ሳይችል ቀርቷል በሰላም ስምምነቱ ሰነድ ላይ ተቃዋሚው ሪክ ማቻር ፊርማቸውን ቢያኖሩም የሀገሪቱ መንግስት ፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪር ግን […]

የሰማያዊ ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጉባኤ በአዲስ አበባ ማንራሸዋ ሆቴል ተጀመረ:: የሰማያዊ ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጉባዬ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተጀመረ ሲሆን የድርጅቲ ሊቀመንበር ለተሳታዊዎቹ እንኳን ደህና መጣቹ በሚል ንግግር ጉባዬውን ከፍተውታል::በጉባዬው ላይ የጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴው የስራ አስፈፃሚ ሪፖርት በአቶ …

የሰማያዊ ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጉባኤ በአዲስ አበባ ማንራሸዋ ሆቴል ተጀመረ:: Read more »

የደብል ዲጅቱ የኢኮኖሚ እድገት ፕሮፓጋንዳ እርቃኑን እየወጣ ነው:: #Ethiopia #EPRDF #DoubleDigitDevelopment #MinilikSalsawi 11% የተባለ የኢኮኖሚ እድገት ሕዝቡን ከድህነት ሊያወጣ ቀርቶ ጭራሽ የደሃ ደሃ የሚል አዲስ የቋንቋ ስያሜ ወልዷል::የኑሮ ውድነቱ እያሻቀበና ህዝቡን እያስደነገጠ ነው፡፡አጠቃላይ የምግብ ፍጆታዎች ዋጋቸው እጅግ አሻቅቧል፡፡በሚቀጥሉት ስድስት ወራት …

የደብል ዲጅቱ የኢኮኖሚ እድገት ፕሮፓጋንዳ እርቃኑን እየወጣ ነው:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

ዛሬ ለኢሳት የደረሰው ጥብቅ መረጃ 11ዓመታትን ወደ ኋላ በትዝታ ወሰደኝ:: ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዋናው ጸሀፊ ቢሮ አፈትልኮ የወጣው መረጃ እንደሚያጋልጠው ለሰላም አስከባሪ 11 ሺህ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሚከፈለው ደምወዝ ከ90 በመቶ በላይ የህወሀት ካዝና ውስጥ የሚገባ ነው:: በወር 13 ሚሊዮን ዶላር(500 ሚሊዮን ብር ገደማ) የወታደሩን ገንዘብ ህወሀቶች ይቀራመቱታል:: ይህን ጉዳይ የመንግስታቱ ድርጅት የሚያውቀው ይመስለኛል:: ለዚህም እኔ […]

የትግራይ ምእራባዊ ዞን አስተዳዳሪ የሆነው ፍስሃ በርሀ ከ44 ሚልዮን ብር በላይ ለግል ጥቅሙ በማዋሉ የተነሳ የዞኑ ነዋሪዎች ምሬታቸውን በማሰማት ላይ መሆናቸው ተገለፀ። ለደህሚት በደረሰው መረጃ መሰረት የምእራብ ትግራይ ዞን አስተዳዳሪ የሆነው ፍስሃ በርሀ ለሁመራ ከተማ መሰረተ ልማት ተብሎ በተለያየ መልኩ ከህዝብ የተዋጣው 44 ሚሊዮን ብር ስልጣኑን ተገን በማድረግ ለግል ጥቅሙ ማዋሉን ታውቆ እያለ እስከ አሁን […]

1• ደስታ እና ሀዘን ሰሞኑን ፍቺ በፍቺ ሆነናል። የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ከፊል አካል ተፈታ። ደስ አለን። የተፈቱት ካልተፈቱት ያላቸው ልዩነት ለብዙዎች ግራ ቢያጋባም!…ዛሬ ደግሞ እነ ሀብታሙ አያሌው ተፈተዋል። ይህም በግለሰብ ደረጃ ደስ የሚል ዜና ነው። ቢያንስ በቅርብ የማውቀው ሀብታሙ (” ሀብትሽ!”) ክፋ ደጉን የማታውቀው ልጁ እጁ ላይ ስታንቀላፋ፣ ወደ አልጋዋ ወስዶ ሲያስተኛት፣ ከእንቅልፏ ስትነቃ አቅፎ […]

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ይገኙ የነበሩትና በትላንትናው እለት ነሐሴ 15 ቀን 2007 ዓ.ም የልደታው ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በነጻ ያሰናበታቸው፤ የአንድነት ፓርቲ የቀድሞ ህ/ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ ከእስር ሊለቀቁ እንዳልቻሉ ‹‹በበላይ ፍቃዱ›› ይመራ የነበረው አንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ገለፁ፡፡ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እንደገለፁት የአቶ ሀብታሙ […]

በአቡነ ቴውፍሎስ  ተረቅቆ በግ. ቀ. ኃይለ ሥላሴ ዘመን ጊዜ ታውጆ በደርግ ዘመን ሥራ ላይ የዋለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መተዳደሪያ ደንብ (ቃለ አዋዲ) ዛሬ የሚታየውን የሰበካ ጉባኤ የተጀመረበት ነበር። ይህንን ታላቅ ተግባር ጫንቃቸው ላይ አርፎ  ከነበሩት አባቶች መካካለ  ከጥቂት ዓመታት በፊት  ከዚህ …

ቃለ አዋዲና ፍልሰታን አስመልክተው ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በነጻነት ለኢትዮጵያ ሬዲዮ የሰጡት ቃለ-መጠይቅ Read more »

የኢትዮጵያ የስደት መንግስት መመስረት አስፈላጊነት ላለፉት ሁለት አስርት አመታት፣ በተለይ ደግሞ የግንቦት 1997 ዓ.ም. ሃገራዊ ምርጫን የህወሃት/ኢህአዴግ ስርዓት በጠመንጃ አፈሙዝ ከህዝብ መንጠቁን ተከትሎ ውይይትና ክርክር ሲደረግበት ቆይቷል። የተሰረቀውን የህዝብ ድምፅ ለማስመለስ የተለያዩ ግለሰቦችና ድርጅቶች የተለያየ የትግል ስልት መከተልን መርጠዋል። አንዳንዶች …

የኢትዮጵያ የስደት መንግስት፤ ከህሳቤ ወደ ተግባራዊነት Read more »

‹‹እንሰሳት በዋሉበት እየቀሩ ነው›› ነዋሪዎች በሀገሪቱ በተፈጠረው የዝናብ እጥረት ምክንያት በተለይ በአፋር፣ በሶማሊና በሌሎች አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ ጎጃም ውስጥም በመከሰቱ በርካታ እንሰሳት እየሞቱ መሆኑንና ሰውም ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፁ፡፡ በተለይ ድርቁ በሶማ፣ አራራ፣ እነገ እና ሰንጠርጌ ቀበሌዎች ለበርካታ እንሰሳት ሞት ምክንያት ከመሆኑም ባሻገር ነዋሪዎችም ለከፍተኛ ችጋር ተጋልጠዋል ተብሏል፡፡ ድርቁ አስከፊ ደረጃ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ በቀጣይ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይ የተመረጡ እና የተለመዱ ፊቶችን ስብስበው ጥያቄ ሲያቀርቡና ማብራሪያ ሲሰጡ ነበር፡፡የእኔን ቀልብ የሳበው ግን አውቀውም ይሁን ሳያውቁት ወጣቶችን እየበላ ያለ ስርዓት ባለቤት እና መሪ መሆናቸውን የገለፁበት አስተያየት ከታዳሚው ሞቅ ባለ በተደጋጋሚ ጭብጨባ መታጀቡ ነው፡፡ ባለፈው የኦባማ ጉብኝት ወቅት ዲሞክራሲ ማላት ምርጫ በስላም ማጠናቃቅ ብቻ አይደለም፡፡ ጋዜጠኞችን አክቲቪሰቶችን […]

ከታሳሪ የህሊና ሰዎች መካከል አብጦ ሊፈነዳ የተቃረበውን የፖለቲካ ድባብ ለማስተንፈስ ሲባል ወዳጄን፣ ጓዴንና የቀድሞ ባልደረባዬን አብርሀ ደስታን፣ የሽዋስ አሰፋን፣ ሐብታሙ አያሌውን፣ ዳኤል ሽበሽንና አብሃም ሰለሞንን «በነፃ» መለቀቅ በሰማሁ ጊዜ ደስታ ቢሰማኝም፤ ንጹሓኑ «በነጻ» መለቀቃቸው ከጠባቡ ጓንታናሞ ወደ ሰፊው ጓንታናሞ መዛወራቸው እንጂ አሁንም ነጻ አለመሆናቸውን፤ እንዴውም አሁን ያለንበት በነጻነት የመናገርና የመጻፍ ሁኔታ እነሱ ከመታሰራቸው በፊት ከነበረው […]

''የሜ/ ጄነራል'' አብረሃ ወ/ ማሪያም መኖሪያ ቤት

የሕወሓት መሐይም የጦር ሹማምንት በእንደዚህ አይነት ቪላ ተንደላቀው ሲኖሩ ተራው ወታደር 500 ብር ባልሞላ ደሞዝ እየተሰቃየ አፈር ድሜ እየበላ ይኖራል። በፎቶው የምትመለከቱት ቪላ ጦር ኃይሎች ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ ከተማ የሚገኝ የሶስተኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ”የሜ/ ጄነራል” አብረሃ ወ/ ማሪያም መኖሪያ …

የወያኔ ጄነራል አብረሃ ወልደማሪያም መኖሪያ ቤት አዲስ አበባ (ፎቶ) Read more »

ዛሬ ነሐሴ 13/2007ዓም በ8:00 ሰዓት የጠቅላይ ፍርድ ሰበር ሰሚ ችሎት ወሳኔ ለመስጠት ሲያነጓትተው የነበረውን የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሰበር አቤቱታ ላይ ዛሬ ውሳኔውን አስተላልፏል። ፍርድ:- ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ ከዚህ ቀደም የእስር ፈርድ ቤቱ የሰጠው የ 3 አመት ፍርድ አግባብም ትክክልም ነው፣ ስለዚህ የስር ፈርድ ቤቱ ካስተላለፈው ውሳኔ ውጪ አይደለንም ፍርዱን አፅንተነዋል ፍርዱ ልክ ነው ምንም […]

በመረጃ መረብ ሰንሰለቱ አማካኝነት ወደ መንግስት መዋቅር ዘልቆ በመግባት ያገኘው የታማኝ ምንጮች መረጃ እንዳረጋገጠው በሙስሊሙ ዑማ ላይ ከፍተኛ በደልና ጭቆና የፈፀመው ህወሓት መራሹ መንግስት በአሁኑ ሰዓት የሙስሊሙ ማህበረሰብ አጠቃላይ ሁኔታ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ዘፍቆታል ። በአሁኑ ሰዓት ሙስሊሙ ማህበረሰብ የትግል ስልቱን ቀይሮ ውስጥ ለውስጥ በመደራጀት አንድነቱን እያጠናከረ እና በተናጠልና በቡድን በመሆን ስለ ቀጣይ ትግሉ እየተወያየ […]

በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በሽብርተኝነት ክስ ተመሥርቶባቸው በእስር ላይ የቆዩት የቀድሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)፣ የሰማያዊና የአረና ፓርቲ አመራሮችና ሁለት ተከሳሾች በነፃ እንዲሰናበቱ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ነሐሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ወሰነ፡፡ የአንድነት ፓርቲ የቀድሞ …

የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ሀብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና ፓርቲ አመራር አብርሃ ደስታ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የሺዋስ አሰፋና ሌሎች 2 ተጠርጣሪዎች በነፃ እንዲሰናበቱ ተወሰነ Read more »

ላለፉት ጊዜያት በተለያዩ እስር ቤቶች ሲንገላቱ ሲገረፉ ሲሰቃዩ ከርመው ካለወንጀላቸው ወንጀለኛ ነን ብለው ፈርመው ከማእከላዊ ማሰቃያ ወደ ቃሊቲ ማጎሪያ ከተዘዋወሩ በኋላ በካቴና ከርመው በካንጋሮው ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት የቀረበባቸው የሽብርተኝነት ክስ ከጥርጣሬ ባለፈ ተሳትፎአቸውን ማረጋገጥ አልተቻለም በማለት የለቀቃቸው መሆኑ ታውቋል::መጀመሪያም …

ካለማስረጃ የተጠረጠረ ሁሉ የሚንገላታበት ጉዳይ ሊወገድ የሚችለው በኛ ትግል ብቻ ነው:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

በተባበሩት መንግሰታት የሰብአዊ ድጋፍ ቢሮ ይፋ ባደረገው አዲስ ሪፖርት በኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር በያዝነው ወር 4.5ሚልዮን መድረሱን ይፋ አድርጓል፡፡ የ2015 ግማሽ አመት የሰብአዊ ድጋፍ ተፈላጊነት ከተገመገመ በኋላ ሪፖርቱ ይፋ ሲደረግ ለጋሽ አገራትና የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዩች በስፍራው መገኘታቸውን መረጃው ጨምሮ ጠቁሟል፡፡ ሪፖርቱ በተጨማሪ ለምግብና ምግብ ነክ ላልሆኑ ነገሮች የሚያስፈልገው የእርዳታ መጠን በጃንዋሪ(ጥር)ወር ተተንብዮ ከነበረው […]

Yared E Yimura :  “ኢትዮጵያዉያንን ማከም ሄዴክ ነዉ። መድሃኒት መዉሰድ አይወዱም። ቢጀምሩም አይጨርሱም። የረጅም ጊዜ ክትትል የሚፈልግን ህመም በአግባቡ አይከታተሉም። ደግሞ የ አብዛኛዎቹ ኬዝ የስኳር ህመም ነዉ። ምንድነዉ የምትመገቡት? ብዬ ስጠይቃቸዉ ሁሉም እንጀራ ይሉኛል። እና እንጀራ ከምን እንደሚሰራ ለማወቅ በከተማዉ …

በሰሜን አሜሪካ እንጀራ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያመጡ ከሚችሉ ንጥረ ነገሮች እንደሚዘጋጅ መረጃዎች ይጠቁማሉ:: Read more »

የ14 አመቷን ታዳጊ ለተከታታይ ሶስት ዓመታት /2003- 2007/ ዓም ድረስ እግርሽ ላይ ለወጣው ጭርት መድሀኒት ነው በማለት ወሲባዊ ግንኙነት በማድረግ 2 ግዜ ስታረግዝ እንድታስወርድ ያደረገ እና ከዛ በሁዋላ እንዳታረግዝ የረዥም ጊዜ የወሊድ መከላከያ (ሉፕ ) በክንዷ ያስቀበረ ሰው በፍትህ አደባባይ …

ለተከታታይ ሶስት ዓመታት የ14 አመት ልጁን አስገድዶ የደፈረው አባት በእስር ተቀጣ :: Read more »

ዛሬ ነሃሴ 14/2007 ዓ.ም የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱትን 2ኛ ተከሳሽ ሀምታሙ አያሌው፣ 3ኛ ተከሳሽ ዳኤል ሽበሽ፣ 4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታና 5ኛ ተከሳሽ የሸዋስ አሰፋ እንዲሁም 7ኛ ተከሳሽ አብሃም ሰለሞን በነፃ እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡ በአንፃሩ …

ሀብታሙ አያሌው፣ዳንኤል ሽበሽ፣አብርሃ ደስታና የሸዋስ አሰፋ እንዲሁም አብረሃም ሰለሞን በነፃ እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡ Read more »

ዛሬ ነሃሴ 14/2007 ዓ.ም የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱትን 2ኛ ተከሳሽ ሀምታሙ አያሌው፣ 3ኛ ተከሳሽ ዳኤል ሽበሽ፣ 4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታና 5ኛ ተከሳሽ የሸዋስ አሰፋ እንዲሁም 7ኛ ተከሳሽ አብሃም ሰለሞን በነፃ እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡ በአንፃሩ አንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ከአሁን ቀደም ተከሶበት በነበረውና ከ15 አመት በላይ እንደሚያሳስር የሚታወቀው የፀረ ሽብር ህጉ አንቀፅ አራት ‹‹ማሴር፣ […]

የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት የህወሓት አገዛዝ የደህንነት ቢሮ ጮርቃ ህፃናትን በሰላይነት እያሰለጠነ እንደሚገኝ ታወቀ፡፡ የህወሓት ብሄራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ በርካታ ህፃናትን ከየአካባቢው መልምሎ አዲስ አበባ ውስጥ የስለላ ትምህርት በስውር እያስተማረ ይገኛል፡፡ ብሄራዊ መረጃና ደህንነት ህፃናቱን አገዛዙን ብቻ በታማኝነት እንዲያገለግሉ የሚያመቻች የስለላና ሌሎች ተያያዥ ትምህርቶችን ለረጅም ጊዜ በተከታታይ በመስጠት አስተሳሰባቸውን በመግራት አእምሯቸውን በሚፈለገው መልኩ ለመቅረፅ […]

የተመሠረተበትን 35ኛ ዓመት በታላቅ ፌሽታ ለማክበር ደፋ ቀና በማለት ላይ የሚገኘው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ንቅናቄው ሰሞኑን በሚያካሂደው ጉባዔ ላይ እንደማይመረጡ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ህወሃትም በተመሳሳይ ሁኔታ የሟቹን የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ያሰናብታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የብአዴን ምንጮች እንደሚሉት ኢህአዴግ ባስቀመጠው የመተካካት ስርዓት መሠረት […]

ተጨማሪ 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ የረሃብ አደጋ ስለተጋረጠበት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል:: Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) : የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ቢሮ (UNOCHA)ባወጣው አዲስ ሪፖርት እንዳመለከተው በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ከተራበው በድርቅ ከተጎዳው ሕዝብ በተጨማሪ በዚህ ወር ውስጥ ብቻ 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ …

ተጨማሪ 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ የረሃብ አደጋ ስለተጋረጠበት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል:: Read more »

“ሀገር የተቀማ ትውልድ” የተሰኘው የዳንኤል ተፈራ ወጥ የፖለቲካ መጽሐፍ ዛሬ ከሰአት በኋላ የመጽሐፍ ገበያውን ተቀላቅሏል፡፡ ዳንኤል ተፈራ ከዚህ ቀደም በሳምንት ብቻ 20 ሺህ ኮፒ የተሸጠውን “ዳንዲ የነጋሶ መንገድ” እና “ከፓርላማው በስተጀርባ” የተሰኙ መጽሐፍትን ለአንባብያን አብቅቷል፡፡ እነሆ አሁን ደግሞ ወጣቱ ባለብዕር …

“ሀገር የተቀማ ትውልድ” የተሰኘው የዳንኤል ተፈራ መጽሐፍ ለገበያ ዋለ :: Read more »

(ስሉሥ ወልደሂወት) “ማንም የቆመ የሚመስለው ቢኖር እንዳይወድቅ ይጠነቀቅ”! መጽሓፍ ቅዱስ የሰው ልጅ ፍላጎት ሁሌ የሚያድግና የማይሟላ በመሆኑ የለውጥ ጥያቄን ለመመለስ ሁሌም ሰለተሻለ አማራጭ፣ ስለተሻለ ዘዴ ወይም ስትራቴጂ ማሰቡና መነጋገሩ ተገቢና ጤናማ መሆኑ የማይታበል እውነት ነው፡፡ በዲሞክራሲያዊ ማህበረሰብ ዘንድ የተቀደሰና ከነቀፋና ትችት የፀዳ የፖሊሲ አቋም ወይም የፖሊሲ አፈፃፀም የማይኖር መሆኑም እንደዚሁ። ዜጐች በግልም ይሁን በተደራጀ መልኩ በነፃነትና ከማንኛውም ተጽእኖ በጸዳ መልኩ የፖሊሲ አማራጮችን መተቸችና የመልካም አስተዳደር ግድፈቶችን ነቅሶ ማውጣት የሚችሉበት ሁኔታ ከተፈጠረ ያ ማህበረሰብ የታደለ ነው ማለት ይቻላል፡፡ የፖለቲካ መሪዎች በዓቅም ውስንነት፣ በግንዛቤ እጥረት፣ የግል ፍለጎት በማሰቀደም ወይም በቅንነት እጦት ምክንያት የሕዝቦችን ጥቅም አደጋ ውስጥ ሊከቱ የሚችሉበት እድል ሰፊ ነው። በመሆኑም የፖሊሲ አማራጮችንና የአፈፃፀም ግድፈቶችን ከመተቸት ባላፈ ፖሊሲውን ለማስፈፀም ሃላፊነት የወሰዱ የፖሊቲካ ድርጅቶች አመራር፣ ውስጣዊ ድርጅታዊ ህይወትና የአመራሩ የግል ማንነት ሳይቀር አብጠርጥሮ ማወቅና መተቸት በሰለጠነው ዓለም የተለመደና ውጤታማ የሆነ የዲሞክራሲ ባህል ነው፡፡ ከሰሞኑ አቶ ዳዊት ገብረ እግዚአብሔር የተባሉ ዜጋ በተለየ ሁኔታ በህወሓትና ህወሓት በሚመራው የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የልማትና መልካም አስተዳደር ፖሊዎችና አፈጻጸም ላይ የሰላ ትችት በመሰንዘር ላይ ይገኛሉ፡፡ የአቶ ዳዊት ትችት ከግል ገጠመኝና ትዝብት በመነሳት በአጠቃላይ በስርዓቱ፣ ስርዓቱ በቆመባቸው ምሰሶችና የማስፈፀምያ ፖሊሲዎች ስትራቴጂዎች እንደዚሁም የድርጅቱና የድርጅቱ አመራር ዓቅምና ህዝባዊነት ላይ ጥያቄ አስነስቷል፡፡ ቀደም ብዬ እንዳልኩት ከፖሊሲ የተሻለ ፖሊሲ፣ ከተሻለው ፖሊሲ እጅግ የተሻለ ፖሊሲ መኖሩ የማይቀር ስለሆነ፤ አቶ ዳዊት ስለተሻለ አመራር፣ […]

ለ35ኛ ጊዜ ማጉላላቱ ቀጥሏል::አራቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን በካንጋሮው ፍርድ ቤት ለነሃሴ 18 ተቀጠሩ:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Freezone9bloggers‬ @zone9ners ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Kangaroocourt‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) «ኃላፊነት የማይሰማው ሥርዓት የገዛ ዜጎቹን ህይወት በእሳት ይማግዳል» በፌዴራል ከፍተኛው «ካንጋሮ ፍርድ ቤት» 19ኛ ወንጀል ችሎት ክሳቸው እንዲቀጥል …

ለ35ኛ ጊዜ ማጉላላቱ ቀጥሏል::አራቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን በካንጋሮው ፍርድ ቤት ለነሃሴ 18 ተቀጠሩ:: Read more »

በሕዝብ ሃብት መቀለድ ተይዟል::ሰበታ አከባቢ ያልተጠናው የባቡር ሃዲድ እየፈረሰ ነው:: ሰበታ አካባቢ ያለ የባቡር ሃዲድ መስመር በወያኔ ባለስልጣናት ትእዛዝ እየፈረሰ ነው በምስሉ እንደሚታየው አሁን ከተገነቡት መሀል አንዱ ሲሆን ምክንያትቱ ሳይታወቅ ሁኔታ በ24 ሰአት አንዲፈረሰ ትዕዛዝ ተሰጥቷል በተለያዩ የአዲስ አበባ አከባቢዎች በርካታ የሆኑ የባቡር መስመሮች የሚፈርሱ እንዳሉ የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል::ይህ ያልተጠና እና በሕዝብ ሃብት ላይ እየተቀለደ […]

በሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ሶልያና ሽመልስ (በሌለችበት) በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፍ ብርሃኔ እና አቤል ዋበላ በዛሬው ዕለት ‹ክሳቸውን መከላከል ያስፈልጋቸዋል ወይስ አያስፈልጋቸውም› በሚል የመጨረሻ ውሳኔውን ለመስማት በፍርድ ቤት ተገኝተው ነበር፡፡ በዕለቱ የተሰየመው ችሎት ‹‹ሰነዱ ሰፊ ነው ብዙ ማንበብ ይጠይቃል …

የዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ (Zone 9) Read more »

ዛሬ በዞን 9 ጦማሪያን የፍርድ ቤት ውሎ የገረመኝ ዛሬ ረፋድ ላይ፤ ናቲ፣ አጥናፍ፣ በፍቄና አቤል በፊት ለፊት በር ችሎት ከገቡ በኋላ፣ እኛም ችሎቱን እንታደማለን ብለን ስንጠብቅ፤ ለጠበቃቸው ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱ ተነገረ፡፡ ጦማሪያኑንም በጓሮ በር በማስወጣት ‹‹አንበሳ ቤት›› እንዲቀመጡ ተደረገ፡፡ በፊት ለፊት አስገብቶ በጓሮ በር ማስወጣት ምን ይባላል? ለምንስ ይሆን? በስፍራው የተገኙ የእስረኛ ቤተሰቦች፣ ዘመዶች፣ ጓደኞች፣ […]

በሕዝብ ሃብት መቀለድ ተይዟል::ሰበታ አከባቢ ያልተጠናው የባቡር ሃዲድ እየፈረሰ ነው:: Minilik Salsawi ሰበታ አካባቢ ያለ የባቡር ሃዲድ መስመር በወያኔ ባለስልጣናት ትእዛዝ እየፈረሰ ነው በምስሉ እንደሚታየው አሁን ከተገነቡት መሀል አንዱ ሲሆን ምክንያትቱ ሳይታወቅ ሁኔታ በ24 ሰአት አንዲፈረሰ ትዕዛዝ ተሰጥቷል በተለያዩ የአዲስ …

በሕዝብ ሃብት መቀለድ ተይዟል::ሰበታ አከባቢ ያልተጠናው የባቡር ሃዲድ እየፈረሰ ነው:: Read more »

የደቡብ ክልል ዋና ከተማ የሆነችው ውቧ ሃዋሳ ከተማ በኮሚቴው ላይ መፈረዱን ተከትሎ በግራፊቲ ፅሁፎች አሸብርቃ ማደሯን የቢቢኤን ምንጮች ገለፁ። የአካባቢ ፖሊስ ማእከላትን ጨምሮ፣ በግድግዳዎች፣ በኤሌክትሪክ ፖሎች ላይ ድምፃችን ይሰማ የተፈረደው በኛ ላይ ነው እና ሌሎች መልእክቶቹም በቀይ ቀለም በስፋት ተፅፈው …

የሃዋሳ ከተማ በግራፊቲ ፅሁፎች አሸብርቃ አደረች ::(PHOTOS) Read more »

( የአባ ዳኘውን ድምፅ ከታች ያገኙታል) በሸክላ (ዲስክ) እየተቀረፀ የሚጫወተው መሣሪያ ( ግራሞፎን) ወደ ኢትዮዺያ የገባው በምኒልክ ዘመነ ምንግስት ነው:: የመጀመሪያው ግራማፎን በ1889 ዓ.ም ሄንሪ ደ ኦርሊንስ እና ኒኮላስ ሊዎንቲቭ ለምኒልክ አመጡላቸው:: ይህም እነሊዎንቲቭ ያመጡት ግራማፎን መጫወት ብቻ እንጂ ድምፅ …

በኢትዮዺያ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፃቸው በዲስክ የተቀረፀው የምኒሊክና የጣይቱ ነው:: Read more »