ለ35ኛ ጊዜ ማጉላላቱ ቀጥሏል::አራቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን በካንጋሮው ፍርድ ቤት ለነሃሴ 18 ተቀጠሩ::

ለ35ኛ ጊዜ ማጉላላቱ ቀጥሏል::አራቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን በካንጋሮው ፍርድ ቤት ለነሃሴ 18 ተቀጠሩ::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Freezone9bloggers‬ @zone9ners ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Kangaroocourt‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) «ኃላፊነት የማይሰማው ሥርዓት የገዛ ዜጎቹን ህይወት በእሳት ይማግዳል» በፌዴራል ከፍተኛው «ካንጋሮ ፍርድ ቤት» 19ኛ ወንጀል ችሎት ክሳቸው እንዲቀጥል በተወሰነባቸው አምስት የዞን9 ጦማሪያን ላይ «ነፃ ናችሁ» ወይንም «ተከላከሉ» የሚል ብይን ለመስጠት ለዛሬ ነሐሴ 13/2007 ዓ·ም ቀጠሮ መሰጠቱ ይታወሳል። ከጽሑፎቻቸው ውጪ ማስረጃም ሆነ ምስክር ያልቀረበባቸው ጦማሪያኑ በእስር ከዋሉ ዛሬ 481 ቀናት ተቆጥረዋል።

በዛሬው እለት በልደታ የካንጋሮ ፍርድ ቤት ችሎት ሙሉ ጥቁር ሱፋቸው እንደለበሱ የደረሱት አራቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን በፍቃዱ:ናትናእል:አቤል እና አጥናፍ እጅግ በራስ መተማመን እና ትልቅ ተስፋ በፊታቸው ላይ ይነበባል::አራቱ ጦማርያን አብረዋቸው የተከሰሱ ጓደኞቻቸው ቢለቀቁም እነሱ ታስረው ይገኛሉ ለብይን ተብሎ የተቀጠረው ፋይል ሲንከባለል ዛሬ ላይ ደርሷል::

በጠዋት ወዳጆቻቸው ጓደኞቻቸው አድናቂዎቻቸው እና የአዲስ አበባ ሕዝብ በተገኘበት የልደታው ችሎት ፖሊስ ከሚታየው መዝገብ ብዛት እና ከተከሳሽ ብዛት የተነሳ ወደ ችሎት መግባት አይቻልም በማለት ጉዳዩን ለመከታተል የመጡትን ሲክለክል ተስተውሏል::በቅርቡ የወያኔው ሚኒስቴር እና ቃል አቀባይ ዞን ዘጠኝን አስመልክቶ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ ይፈቷቸዋል የሚል ተስፋ ቢጣልም ታዛቢዎች ግን እንደሚሉት ይውሳኔው ጉዳይ የባለስልጣናት ንግግር ሳይሆን ጥቂት የሃገሪቱ ከፍተኛ የደህንነት እና ወታደራዊ አዛዦች የግል ውሳኔ ስለሆነ ፍትህ እንዳይዛባ ሲናገሩ ተደምጠው ነበር::ወደ ችሎቱ ምንም አይነት ዲፕሎማት፣ ጋዜጠኛ፣ ቤተሰብም ሆነ ወዳጅ እንዲገባ አልተፈቀደም።የፌዴራል ፖሊሶች እና ደህነቶች በልደታ ፍርድ ቤት የችሎቱን ውሳኔ ክደጅ የሚጠባበቁትን እያንገላታ እና እንቅስቃሴያቸውን እየተከታተለ እንደነበር በአከባቢው የሚገኙ ጉዳዩን የሚከታተሉ ተናግረዋል::

ለአስር ደቂቃ የተቀመጠው ችሎት በሕዝብ ልጆች ላይ መጫወቱን ቀጥሏል::ሰነዱ ሰፊ ነው ብዙ ማንበብ ይጠይቃል::ያለው የወያኔው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለማስመሰል የፖለቲካ ውሳኔን ለማንበብ፣ ቀጠሮ ቀጠሮ ቀጠሮ ትዕዛዝ አልደረሰንም በሚል ማጉላላቱን ቀጥሎበታል፡፡የፀረ ሽብር ክሶችን የሚያየው 19ኛ ወንጀል ችሎት ነሃሴ 15 ቀን ይዘጋል ተብሎ አስቀድሞ በዳኞች ተነግሮ የነበረ ቢሆንም ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ ለነሃሴ 18 የብይን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል። ግራ የገባው መንግስት! ግራ የገባው የፍትህ ስርዐት! ግራ የገባት ሀገር!

ላንቺ የምመኘው ህልም አለኝ አገሬ;
ግን እንዳልታሰር አልነገርሽም ዛሬ::

Minilik Salsawi's photo.