የአንድነት ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና ማህበራዊ ጉዳዮች ኃላፊ የነበሩት አቶ አለነ ማህፀንቱ፤ ባሳለፍነው ሐሙስ ነሐሴ 7 ቀን 2007 ዓ.ም አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት 5ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው እንደነበር የተከሳሹ ጠበቃ አቶ ገበየሁ ይርዳው ገለፁ፡፡ አቃቤ ሕግ በአቶ አለነ ላይ …

አቶ አለነ ማህፀንቱ ለነሐሴ 21 ;በ‹‹እነ አንጋው ተገኝ›› ላይ የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ለጳጉሜ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ Read more »

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መንጌ ወረዳ የመንግስት ሃይሎች አርብ እለት በሰነዘሩት ጥቃት 12 ሰዎች ተገደሉ። ከሟቾቹ ውስጥ 5ቱ ህይወታቸው ያለፈው እስር ቤት ከተወሰዱ በኋላ በምግብ ተመርዘው እንደሆነ የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ አስታወቀ። የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ (ቤሕነን) ሊቀመመንበር አቶ አብዱልዋህድ መሃዲ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት አርብ ነሐሴ 8 ቀን 2007 የመንጌ ወረዳ ነዋሪዎች በስርዓቱ ላይ […]

በኬንያ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር የዋሉት 100 ኢትዮጵያዊያን ትናንት አመሻሽ ላይ ነው፡፡በወጣትነት የእድሜ ክልል የሚገኙት ታሳሪዎቹ በተፋፈነ ሁኔታ በአንድ ትልቅ መኪና ተሳፍረው ወደ ናይሮቢ በመገስገስ ላይ እንዳሉ በፖሊሶች በተደረገ ፍተሻ መያዛቸው ታውቋል፡፡ታሳሪዎቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት አቅደው የነበሩ መሆናቸውም ተነግሯል፡፡ እንደ ዴይሊ ኔሽን ዘገባ ከሆነም ስደተኞቹ በሞያሌ በኩል በድብቅ በማለፍ ወደ መሩ ካውንቲ ማምራታቸውን መረጃ የነበራቸው የኬንያ ፖሊሶች በቀላሉ በቁጥጥር ስር ሊያውሏቸው […]

የት እንዳሉ ሳይታወቁ ቀርተው የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በአባታቸው መጎበኘታቸው ተሰማ:: የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን ላይ ተይዘው ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው ከተሰጡ በኋላ አፍቃሪ የመንግስት ድረገጾች በፎቶ ሾፕ አንዳርጋቸው የአዳማን መንገድ ሲጎበኝ በሶሻል ሚድያዎች ለጥፈው ሲዋሹ ነበር:: ከዚህም በተጨማሪ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም አቶ አንዳርጋቸውን ልማቱን እያስጎበኘነው ነው ሲሉ በአሜሪካ ድምጽ ራድዮ […]

መንግስት በደ/ወሎ ለጋንቦ ወረዳ ያስነሳዉ እረብሻ እሱ እንደለለበትናዩኒቨርስቲዉ በጭራሽ እንዳልተነሳ ለማስተባበል እየሞከረና ጉዳዉን ከሙስሊሞች ጋራ ለማያያዝ ከዚህ ቀደም ጊባ ከተማ ላይ በተደረገዉ የሰደቃ ፕሮግራምና መንግስት ከፍተኛ ጭፍጨፋ ያደረገበትን ድርጊት በማንሳትበየመድረኩ እየለፈፈናደፋቀና እያለና የክልሉ ርእሰመስተዳደር አቶ ገዱ ለምክር ቤት አባሉናአቶ ደመቀ …

ዛሬ አቅስታ ከተማ የድንጋይ መከላከያ በለበሱና አስለቃሽ ጭስ በያዙ ፌደራል ፖሊሶች ተከባ በርካታ ወጣቶችን ሲያፍሱ ዉለዋል። Read more »

የነሐሴ 11 ቀን 2007 ዓ.ም.ዜና (August 17, 2015 News) ፍኖተ ዲሞክራሲ ራዲዮ ያዳምጡ – ለሃጅና ዑምራ ፀሎት ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚሄዱ ሙስሊሞች እየተንገላቱ ናቸው – የወያኔ ዲያስፖራ በዓልና ቀን በአቤቱታ አለቀ – ዛሬ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ጽሁፎች ተበትነው አደሩ [youtube …

ለሃጅና ዑምራ ፀሎት ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚሄዱ ሙስሊሞች እየተንገላቱ ናቸው :: የወያኔ ዲያስፖራ በዓልና ቀን በአቤቱታ አለቀ:: (ፍኖተ ዲሞክራሲ ) Read more »

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያን ህዝብ ንብረትና አንጡራ ሀብት በመመዝበር በአለም አቀፍ ደረጃ አሉ በሚባሉ ታላላቅ የንግድ ተቋማትና ባንኮች ላይ ባለድርሻ እየሆኑ ይገኛሉ ለጊዜዉ ስማቸዉን መጥቀስ አስፈላጊ የልሆኑ ከፍተኛ ባለስልጣናት በደቡብ አፍሪካ ዚምባብዌ ኡጋንዳ ቦትሱዋና ዉስጥ ትላላቅ ህንጻዎችን፣ እና የእንግዳ መቀበያ ሆቴሎችን ( gust houses ) ፣ መሬቶችና ሌሎችታላላቅ የንግድ ተቋማት ላይ እግራቸዉን እየተከሉ ይገኛሉ። […]

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ስሜታውያን በርክተዋል::ተናግረው እፎይ ብለው የሚተኙ በርካቶች ሆነዋል::ልክ ልኩን ነገርጉት ብለው ሌላውን ደሞ ለማሸማቀቅ (የሚሸማቀቅ ካገኙ) አስበው በየምናምኑ የሚንጎዳጎዱ ጊዜው ይቁጠራቸው::በነፈሰበት የሚነፍሱ ሳያገናዝቡ የሚያራግቡ የፈጠራ እሳት የሚያርገበግቡ በተገኘበት ተደናብረው እና ደንብረው ደንግጠው ለማስደንገጥ የሚርበተበቱ እንዳሉ ሁሉ …

ያለንበት ጊዜ በተገኘው አጀንዳ ላይ የሚነፈስበት ሳይሆን ብስለት የሚጠየቅበት ጊዜ ነው:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

– ለ3 ቀን ያክል እህል ውሃ እንዳልቀመሠ እና በድብደባ ብዛት የሱ ያልሆነ ቃል እራሳቸው ያዘጋጁት ላይ እንዳስፈረሙትም ተውቇል – በድብደባ ወቅት አፀያፊ ስድብ ይሰድቡት እንደነበረ ተረጋግጧል – በምርመራ ወቅ ት የሚከተሉትን ጥያቄ እየተጠየቀ ተደብድቧል – በድብደባ ብዛት በርካታ የሠውነት ክፍሎቹ …

የመኢአድ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ አብርሃም ጌጡ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ እየተሠቃየ ይገኛል :: Read more »

በባሌ ዞን ሰልጣ ቀበሌ፣ ሲናና ወረዳ የሰማያዊ ፓርቲ የፓርላማ ዕጩ ተወዳዳሪ የነበሩት አቶ ወርቅነህ ጋድይ አያና የእድር ስብሰባ ላይ ጥያቄ ጠይቀሃል ተብለው መታሰራቸውን የሰማያዊ ፓርቲ የዞኑ አስተባባ አቶ ደመላሽ በቀለ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ በተለይ ከምርጫው በኋላ ካድሬዎች አቶ ወርቅነህ እድርን …

የሰማያዊ ፓርቲ የፓርላማ ዕጩ ተወዳዳሪ እድር ላይ ጥያቄ አነሳህ ተብለው ታሰሩ Read more »

የመላው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ) የውጭ ግንኙነት ሀላፊ አብርሃም ጌጡ ሰኔ 12 /2007 ልደታ ፓሊስ መምሪያ ታሰረ ብዙም ሳይቆይ ወደ 5ኛ ፓሊስ ጣቢያ ተዛወረ ልደታ ፍርድ ቤት ሚያዝያ 13/2007 ዓም የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ወጣቶችን አደራጅተህ ሚያዝያ 14/2007 ዓም መንግስት የጠራውን ሠልፍ እንዲረበሽ አድርገሃል የሚል ክስ ቀረበበት ጊዜ ቀጠሮ ላይ እያለ ሳይቋጭ […]

_በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና በምክትላቸው በአርበኛ መዓዛው ጌጡ የተመራው የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር በኤርትራ በረሃ በተለያዩ የጦር ካምፖች የሚገኙትን የነጻነት ታጋዮችን ጎበኘ። አቶ ነዓምን ዘለቀና አቶ ኤፍሬም ማዴቦም ተገኝተዋል። ታጋዮቹ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡ ከአመራሮቹም ጋር ተወያይተዋል። _ባለፈው ዓርብ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መንጌ ወረዳ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚመራው መንግስት ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ 17 ኢትዮጵያውያን ተገደሉ። ስርዓቱ በቃን […]

አንደኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ‹‹ሀገሬ በፋሽስት አምባገነኖች ተይዛ ዜጎች በጨቋኝ ስርዓት ውስጥ ስላሉ ሀገሬንና ህዝቤን ነጻ ለማውጣት ወጣትነቴን ሰውቼ ለመታገል ግንቦት ሰባት ከሚባል ነጻ አውጭ ድርጅት ጋር ለመቀላቀል ወስኜ ወደዚያው አቅንቻለሁ፡፡ ስለዚህ ድርጊቱን ፈጽሜያለሁ፣ የግንቦት ሰባት አባል ነኝ፡፡ ወንጀለኛ ግን አይደለሁም›› ሲል ቃሉን ለፍርድ ቤቱ ሰጥቷል፡፡ ሁለተኛ ተከሳሽ እየሩሳሌም ተስፋው በበኩሏ፣ ‹‹ድርጊቱን ፈጽሜያለሁ፤ ነገር ግን […]

ወደ 150 ሚሊዮን የሚጠጋ ብር በሻንጣ ጠርቆ ለንደን የገባ የሀገራችን ዘራፊ የወያኔ ባልደረባ በእንግሊዝ ፖሊሶች ክትትል እጅ ከፈጅ ተያዘ።ከፍርድ ቤት ጋር በተያያዘ ለጊዜው ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቁ ምንጮች እንደገለጹት ፣ አንድ የህወሃት አባል 5 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ የሚገመት ጥሬ ገንዘብና ወርቅ በሻንጣው ይዞ ወደ ለንደን ሲገባ ጋትዊክ አየር ማረፊያ ላይ በፖሊሶች ተይዟል። ግለሰቡ ፍርድ ቤት ቀርቦአል። […]

– የረሃብ አደጋ በሀገራችን አንዥቧል። – የወያኔ ውስጣዊ ጭቅጭቅ ገና አላበቃም። – አርከበ ጠቅላይ ሚኒስቴር ካልሆንኩ በሚል ቅስቀሳውን አጧጡፏል ተባለ። – የአሜሪካ ፖለቲካ የአፍሪካ ቀንድን አካባቢ እያተራመሰ ነው። – የጅቡቲ ፖለቲካ ቀውስ በመባባስ ላይ ነው። – አድሃሪው የሳውዲ አገዛዝ የመንን …

የወያኔ ውስጣዊ ጭቅጭቅ ገና አላበቃም። አርከበ ጠቅላይ ሚኒስቴር ካልሆንኩ በሚል ቅስቀሳውን አጧጡፏል ተባለ። Read more »

የትግላችንን አቅጣጫ አስመልክቶ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ! ሰኞ ነሐሴ 11/2007 የመግለጫው ሙሉ ቃል በፒዲኤፍ፡- http://goo.gl/s0Zna5 የመግለጫው ሙሉ ቃል በጽሁፍ እንደሚከተለው ሰፍሯል፡- **** ‹‹አቅጣጫችን በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ የተቃጣውን ብሄራዊ ጭቆና ለዘለቄታው መግታትን ያለመ ነው!›› ‹‹የሙስሊሙን ሁለገብ መብቶች ለማስከበር እንታገላለን!›› እሁድ ነሐሴ 10/2007 …

‹‹አቅጣጫችን በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ የተቃጣውን ብሄራዊ ጭቆና ለዘለቄታው መግታትን ያለመ ነው!›› ድምፃችን ይሰማ Read more »

በለንደን ፖሊሶች በቁጥጥር ስር የዋለው የህወሀት አባል!!! በአውስትራሊያ ቻናል ፱ ቦርደር ሰቹሪትይ ልዩ ሽፍን ሰጥቶታል ከኢትዮጵያ ወደ ለንደን ቦርሳ ሙሉ ገንዘብና ወረቅ ይዞ ሊገባ ሲል በለንደን ፖሊሶች በቁጥጥር ስር የዋለው የህወሀት አባል ይህ ነው። የወያኔ አባል በትላንትናው እለት ሰርቆ ከኢትዮጵያ …

ቦርሳ ሙሉ ገንዘብና ወርቅ ይዞ ሊገባ ሲል በለንደን ፖሊሶች በቁጥጥር ስር የዋለው የህወሀት አባል ይህ ነው። PHOTO(አውስትራሊያ ቻናል ፱ ) Read more »

አቶ መለስ ምን አዲስ ነገር አበረከቱ? —– ጌታቸው ሺፈራው (የግል አስተያየት) አቶ መለስ እንደ አንድ ‹‹ኢትዮጵያዊ መሪ›› የሚገባቸው ክብር ካለ ቢሰጣቸው ክፋት አልነበረውም፡፡ ሆኖም እየተደረገ የሚገኘው ከሚገባቸው በላይ ማግነን ነው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ አቶ መለስ የሞቱበትን ጊዜ ያመነበትን ሶስተኛ አመትን አስመክክቶም ይህ …

አቶ መለስ ምን አዲስ ነገር አበረከቱ? ጌታቸው ሺፈራው Read more »

ሰላም ጤና ይስጥልን አድማጮችና ተመልካቾቻችን ይህ የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ ነው። ሳምንታዊ ዜናዎችን መጣጥፎችን እና መንፈስን የሚያድሱ ሙዚቃዎችን አሰናድተን ወደናንተ መጥተናል ያዳምጡት:: [youtube http://www.youtube.com/watch?v=wTCL1TFS_Og]

የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን በማቋረጥ ኤርትራ ከሚገኘው ግንቦት ሰባት የተባለ በተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ ከተፈረጀ የሽብር ቡድን ጋር ለመቀላቀል ሲጓዙ ድንበር አካባቢ ማይካድራ ላይ እንደተያዙ በመግለጽ በመንግስት የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ፡፡ ዛሬ ነሐሴ 11/2007 ዓ.ም …

‹‹ድርጊቱን ፈጽመናል፣ ጥፋተኞች ግን አይደለንም›› = እነ ብርሃኑ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ:: Read more »

የደቡብ ሱዳን የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር የኢጋድ ዋነኛ አደራዳሪ የሆኑትን ኢትዮጵያዊውን አምባሳደር ስዩም መስፍንን ከሰሱ፡፡ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ ማይክል ማኩኢ በአምባሳደር ስዩም መስፍን ላይ ጠንከር ያለ ወቀሳ ከመሰንዘር በተጨማሪም የኢጋድን የድርድር አካሄድ ወቅሰዋል፡፡ ከስምምነት ላይ የግዴታ መድረስ አለባችሁ ሲል ኢጋድ በደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ሀይላት ላይ ያስቀመጠውን ማሳሰቢያ የድርድር አካሄድ አይደለም ያሉት ሚኒስትሩ ኢጋድም ሆነ አምባሳደር ስዩም መስፍን ‘መመሪያ […]

ተጽፈው ባደሩ ጽሁፎች መንግስት ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ገብትዋል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Ethiomuslims‬ ‪#‎Graphics‬ ‪#‎AddisAbaba‬ ‪#‎BBN‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬ መልክቶቹን ህዝብ እንዳያያቸው ለማድረግ ና ለማጥፋት ፖሊሶች በከፍተኛ ቁጥር ተሰማርተዋል የተጻፈባቸው ባነሮች እየተቀደዱ ነው ቢቢኤን ሰኞ ነሃሴ 11/2007 በዛሬው እለት የሙስሊሙን ኮሚቴዎች ፍርድ ተከትሎ ጠንካራ መልክእት …

ተጽፈው ባደሩ ጽሁፎች መንግስት ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ገብትዋል:: Read more »

ወያኔ ሐርነት ትግራይ የሚመራዉ መንግስት ወታደራዊ ፍርድ ቤት በሁለት የሰራዊቱ ከፍተኛ አባላት ላይ እርምጃ ወሰደ. በተልይም ለአርበኞች ግንቦት 7 መረጃ አቀብላችኍል የተባሉት እነዚህ ሁለት ወታደሮች በሰሜኑ እዝ ዉስጥ የተካተቱና የ 24 ተኛ ክፍ ለ ጦርን በመረጃ ፍሰት ምክንያት በማስጠቃት እና የሜካናይዝዱን እንዲሁም የእግረኛዉን አስተላለፍ የማጥቃትና የአቀማመጥ ወታደራዊ ዲዛኖችን ወይም ጥብቅ የምህንድስና የጦር ስልችን ለጠላት አሳልፋችሁ […]

በጠቅላይ ሚኒስተራችን የትውልድ ቦታ በሆነችው በቦሎሶ ሶሬ በከተማ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ምክንያት ነዋሪዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጩ በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ሥር በምትገኘው የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ከከተማ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ, ሕገወጥ ግንባታዎችን ለማፍረስ የአረካ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በመሞከሩ ነዋሪዎች ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸው ታወቀ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የትውልድ ቦታ በሆነው የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዋና ከተማ […]

ፍትህ ለታሰሩት !!!! ….. አዲስ አበባ በግድግዳ ላይ ጽሁፎች እና ግራፊክስ አሸብርቃ አደረች:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Graphics‬ ‪#‎AddisAbaba‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ አዲስ አበባ በግሬቪቲ የተቃውሞ ፅሁፎችና ወረቀቶች ተጥለቅልቃ አደረች። በህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴዎች ላይ ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ ከ7 እስከ 22 መፈረዱን ተከትሎ የቁጣ መልእክት ያዘሉ …

አዲስ አበባ በግሬቪቲ የተቃውሞ ፅሁፎችና ወረቀቶች ተጥለቅልቃ አደረች። Read more »

ታዳጊዋ ህጻን ጽንሱን በጊዜ ማቋረጥ ወይስ መውለድ ነበረባት ? በማከላዊ አሜሪካ( ፓራጓይ) ውስጥ ነዋሪ የሆነችው ሰሟ ለጊዜው ያልተጠቀሰው የ 10 አመቷ ጨቅላ ባለፈው ሚያዚያ ወር ከፍተኛ የሆድ ቁርጠት ሰሜት ሲሰማት ችግሯን ለወላጅ እናቷ ትናገራለች። ወላጅ እናቷም በአቅራቢያቸው ከሚገኝ አንድ ሆስፒታል ይወስዷታል። ዶክተሮቹም ለራሳቸውም ሆነ ለእናቷ እና ለጨቅላ ለጃቸው አንድ የለጠበቁት መርዶ ያረዷቸዋል። እርሱም ያቺ ለአቅመ […]

የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ የተቃዋሚ ድርጅቶችን ትደግፋላችሁ በሚል ወያኔ ህዝብን እያሸበረ ነው የመቅደላ ዩኒቨርስቲ ከግንባታው በፊት ለእርስ በርስ ግጭት መንስኤ ሆኖ የሰው ህይወት መቅጠፉ ተሰማ። የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች በስብሰባ ተጠምደዋል በደቡብ ወሎ የወያኔ የፀጥታ ሃይሎች በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ነው ተባለ። ሁለት የአይማኖት መሪዎች የትጥቅ ትግሉን እንደሚቀላቀሉ አስታወቁ በሽብር ወንጀል ተከሶ ቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኘው አበበ ካሴ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመበት […]

ሰበር ዜና ቢቢኤን ሰኞ በዛሬው እለት አዲስ አበባ በግሬቪቲ የተቃውሞ ፅሁፎችና ወረቀቶች ተጥለቅልቃ አደረች። በህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴዎች ላይ ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ ከ7 እስከ 22 መፈረዱን ተከትሎ የቁጣ መልእክት ያዘሉ መልእክቶች በአዲስ አበባ በስፋት ተፅፈው ማደራቸውን የቢቢኤን ምንጮች ገልፀዋል። በቀይ ቀለም እንዲሁም በቀይ በቢጫ፣ ነጭ ወረቀቶች ከተፃፉት መልእክቶች መካከል ይብቃ!!! አንባገነን ስርአት ከትከሻችን ይውረድ! ዋ!ዋ! ዋ! […]

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ ከ70 በላይ አማርኛ ተናጋሪ ገበሬዎች፣ ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎ ከመኖሪያ ቀዬአቸው መፈናቀላቸውን የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) በሪፖርቱ አመለከተ፡፡ የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱንም አረጋግጫለሁ፤ ብሏል፡፡ ሰመጉ ጉዳዩን ሲመረምር መክረሙን ጠቁሞ፣ “ብሔር ተኮር ማፈናቀልና እንግልት በአስቸኳይ ይቁም” በሚል ርዕስ ይፋ ባደረገው 136ኛ ሪፖርቱ የወረዳው የጸጥታ ሓላፊዎችና ባለሥልጣናት የብሔር ግጭቱን […]

– የፖለቲካ እስረኞች ምሕረት እንዲደረግላቸው ጠይቋል

– የዳያስፖራ ልማት ባንክ ይቋቋም ተብሏል

መንግሥት የዳያስፖራ ፖሊሲን ይፋ ካደረገ ከሁለት ዓመት በኋላ በአገር አቀፍ ደረጃ በያመቱ እንዲካሄድ በወሰነው መሠረት፣ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰናዳው የዳያስፖራ ቀን በርካታ ቅሬታዎች ከዳያስፖራው ለመንግሥት ኃላፊዎች ቀረቡ፡፡ 

በተለያዩ አገሮች እንደሚኖሩ ከሚገመቱት ሁለት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መካከል አምስት ሺሕ ያህሉ ለአምስት ቀናት በሚሊኒየም አዳራሽ ሲካሄድ ቆይቶ እሑድ ነሐሴ 10 ቀን 2007 ዓ.ም. በሚጠናቀቀው የዳያስፖራ ቀን በዓል ላይ መሳተፋቸውን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በዚህ መሠረት ነሐሴ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. በተደረገ ውይይት ወቅት የዳያስፖራ አባላቱ በመንግሥት በኩል የሚገጥሙዋቸውን ችግሮች በመዘርዘር ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡ 

መንግሥት እንዲያስተካክል ከተጠየቀባቸው ጉዳዮች መካከል የዳያስፖራው ማኅበረሰብ በቢሮክራሲ ውጣ ውረድና በመረጃ እጦት የሚደርስበት እንግልት ይጠቀሳል፡፡ በተለይ ነዋሪነታቸው በእንግሊዝ የነበረውና ወደ አገር ቤት ከመጡ ሁለት ዓመታት ያስቆጠሩት አቶ ሀብቴ ፈረደ፣ ከቱርክ በወኪልነት በባቡር መስመር ግንባታ ላይ ለማሳተፍ ያመጡት ኩባንያ በቢሮክራሲ ሳቢያ ፋይናንሱን ወደ ኬንያና ወደ ኡጋንዳ ለመውሰድ መገደዱን ተናግረዋል፡፡ ሜጀር ግሩፕ የተባለውን የቱርክ ኩባንያ አፈላልገው ማምጣታቸውን የገለጹት አቶ ሀብቴ፣ ኩባንያው 375 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውንና ከአዋሽ-ወልዲያ እስከ ሃራ ገበያ የሚዘረጋውን የባቡር መስመር ለመገንባት ጨረታውን አሸንፎ እንደነበር ይናገራሉ፡፡ 

ይህ ኩባንያ ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገውን 1.7 ቢሊዮን ዶላር ለማምጣት የአንድ ዓመት ጊዜ ተሰጥቶት እንደነበር አስታውሰው፣ ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ምንጮች 1.9 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ችሎ እንደነበርም ጠቅሰዋል፡፡ ይሁን እንጂ ኩባንያው ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ከማምጣቱ አንድ ወር ቀደም ብሎ፣ ፕሮጀክቱ ያፒ መርከዚ ለተባለ ለሌላ የቱርክ ኩባንያ ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡ ጉዳዩን በማስመልከት የኢትዮጵያ ባቡር ኮርፖሬሽንን ሲጠይቁ፣ ሌሎች ያልተነኩ ፕሮጀክቶች ስላሉ እነዚያ ላይ ትሳተፋላችሁ እስከዚያ ጠብቁ የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ 

አቶ ሀብቴ እንደሚሉት፣ መንግሥት ከዚህ በኋላ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሌሎች አዳዲስ የባቡር ፕሮጀክቶችን ያስጀምራል የሚል ዕምነት ያጣው የቱርኩ ኩባንያ፣ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ሊያድርግ ያመጣውን ገንዘብ ወደ ኬንያና ኡጋንዳ ወስዷል፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው ግን የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ባቡር ኮርፖሬሽን ተገቢውን ምላሽ ሊሰጡ ባለመቻላቸው እንደሆነ አክለዋል፡፡ ውይይት እንዲደረግ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም አንድ ጊዜ ሚኒስቴሩ ሌላ ጊዜ ኮርፖሬሽኑን ይመለከተዋል በሚል ተደጋጋሚ ምክንያት ኩባንያው ሳይሳተፍ መቅረቱን ገልጸዋል፡፡ በመድረኩ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች ላይ አስረጅ ሆነው የቀረቡትና ጥያቄው በቀጥታ የተሰነዘረላቸው የገንዘብና ኢኪኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ አህመድ ሺዴ ምላሽ ሳይሰጡበት አልፈውታል፡፡ 

ከአቶ ሀብቴ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በኩል የሚታደሰውን የትውልደ ኢትዮጵያዊነት መታወቂያ አገልግሎት ለማግኘት የሚገጥማቸውን ውጣ ውረድ የገለጹም ነበሩ፡፡ ከኤምባሲ ሠራተኞች ተገቢውን መረጃና ማብራሪያ የሚሰጣቸው በማጣት ብቻ በእያንዳንዱ የሰነድ ልውውጥ እስከ 40 ዶላር እየከፈሉ እንደሚቸገሩ አባላቱ አስታውቀዋል፡፡ በውጭ አገር ፍች ከፈጸሙ በኋላ የጋራ ንብረታቸውን ጠቅልለው በመምጣት ባዶ ለሚያስቀሯቸው  ባሎቻቸው ፈቃድ እየተሰጠ ችግር ላይ እንደወደቁ የተናገሩ ሴቶችም እያለቀሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምንና አቶ አህመድን መፍትሔ እንዲሰጧቸው ተማጽነዋል፡፡ 

በአሜሪካ ለ30 ዓመታት መኖራቸውን ለሪፖርተር የገለጹት ወይዘሮ ሰብለ ነቢየልዑል፣ ወደ ኢትዮጵያ ጠቅልለው በመምጣት በቆዳና በውበት ክብካቤ ላይ የሚሠራ ‹‹ዚኒያ ኤስቴቲክስ ኤንድ አንታይ ኤጂንግ ክሊኒክ›› የተባለው የጤና ተቋም ሥራ በጀመሩ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ያለማስጠንቀቂያ እንዲዘጋባቸው መደረጉን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ላቀረበላቸው ቅድመ ሁኔታ የአንድ ዓመት ጊዜ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም፣ ከስምንት ወራት በላይ ሊሰጣቸው እንደማይችል ገልጾ ክሊኒካቸው ሊዘጋ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡ ክሊኒኩ ፈቃድ ያወጣው አሜሪካ በሚገኙት የወይዘሮ ሰብለ አጋር በሆኑት ዶ/ር ስም በመሆኑ እየተመላለሱ እንዲሠሩ፣ ወይም የአንድ ዓመት ጊዜ ተሰጥቷቸው በአሜሪካ የሚያስፈልጉ ጣጣዎችን ጨራርሰው እስኪመጡ ክሊኒካቸው ከሚዘጋ፣ እስከዚያው ድረስ ተመጣጣኝ በሆኑ የሕክምና ባለሙያዎች ሥራውን ለማስኬድ እንዲፈቀድላቸው ያቀረቡት ጥያቄም ውድቅ እንደተደረገባቸው አስረድተዋል፡፡ እስካሁን አሥር ሚሊዮን ብር ከግል ሀብታቸው ኢንቨስት ማድረጋቸውንም ገልጸዋል፡፡ 

ከክሊኒኩ ባሻገር አቬላሜድ ቢዝነስ ቴክኖሎጂ የተሰኘ የመረጃና የትንተና ተቋም ለመመሥረት ሲንቀሳቀሱ ቢቆዩም፣ በገጠማቸው ውጣ ውረድ ሳቢያ እውን ሊያደርጉት እንዳልቻሉ የሚናገሩት ወይዘሮ ሰብለ፣ እስከቻሉት ጊዜ ድረስ ሞክረው የማይቻል ከሆነ ግን ወደ ኬንያ ሊወስዱት ወይም ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሊያቀኑ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ በአሜሪካ ሳይቀር ጥቂቶች ብቻ የሚገለገሉበት የዚህ ዓይነቱ ክሊኒክ ተፈላጊነቱ ከፍተኛ በመሆኑ፣ ጥያቄ እየቀረባለቸው እንደሚገኝም አስረድተዋል፡፡ 

በመድረኩ ለባለሥልጣናቱ ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል የፖለቲካ እስረኞችና በሃይማኖት ምክንያት የታሰሩ ካሉ እንዲፈቱ የሚለው ይገኝበታል፡፡ መንግሥት በፖለቲካና በሃይማኖት ምክንያት ያሰራቸው ሰዎች እንዳሉ እንሰማለን ያሉት ጥያቄ አቅራቢዎች፣ ምሕረት እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡ ከዚህ ባሻገርም ለዳያስፖራው ጥያቄዎች መፍትሔ ሊሆኑ ይችላሉ ከተባሉት መካከል የዳያስፖራ ልማት ባንክ እንዲቋቋም፣ ገለልተኛ የዳያስፖራ ኮሚሽን እንዲመሠረት፣ የዳያስፖራው አባላት በአክሲዮን መደራጀት የሚችሉበት ዕድል እንዲሰጥ የሚጠይቁት ይጠቀሳሉ፡፡ ዶ/ር ቴድሮስና አቶ አህመድ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችና ማስተካከያ ይደረግባቸዋል ስላሏቸው የመልካም አስተዳደር፣ የመንግሥት አገልግሎትና መሰል ጉዳዮች ላይ ማሻሸያ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡ በፖለቲካና በሃይማኖት ጉዳይ ታሰሩ ስለተባሉት ሰዎች ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በቀጥታ ምላሽ ሳይሰጡበት አልፈዋል፡፡

ተደጋግመው ለባለሥልጣናቱ ከቀረቡት ችግሮች ባሻገር የዳያስፖራው መድረክ ለዶ/ር ቴድሮስ አፍቅሮት የታየበትም ነበር፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እንደ አንድ ታዋቂ አርቲስት ከፍተኛ ጭብጨባና ፉጨት ተስተጋብቶላቸዋል፡፡ ፎቶ አብረዋቸው እንዲነሱ የሚጠይቋቸውና ፊርማቸውን እንዲያኖሩላቸው የሚወተውቱም በርካቶች ነበሩ፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ ሎሬት ሰዓሊና ገጣሚ ገብረክስቶስ ደስታ ከደረሰው ስደት ተኮር ግጥም በመዋስ የመግቢያ ንግግራቸውን አሰምተዋል፡፡ አንጋፋው ድምፃዊ ዓሊ ቢራን በማጀብም አንጎራጉረዋል፡፡  

በሌላ በኩል ለአሥረኛ ጊዜ በተካሄደው ዓመታዊ የዳያስፖራ ኢንቨስተሮች ሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ፣ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ቢዝነስ ፎረም አምባሳደር ግርማ ብሩን ጨምሮ ሁለት ኢንቨስተሮችን ሸልሟል፡፡ ሐሙስ ነሐሴ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ምሽቱን በሸራተን አዲስ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት አምባሳደር ግርማ ብሩ ለዳያስፖራ ኢንቨስትመንትና የንግድ መስኮች ላበረከቱት ድጋፍ ‹‹የዓመቱ የቢዝነስ ሻምፒዮና›› ተብሎ የተሰመውን አምና በአሜሪካ የተጀመረውን የተቋሙን ሽልማት ከዶ/ር ቴድሮስ እጅ ተቀብለዋል፡፡ ዶ/ር አከዘ ጣዕመና አቶ ታምራት በቀለ በጤና ዘርፍ ባደረጉት ኢንቨስትመንትና አስተዋጽኦ ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ 

ዘንድሮ የልዩ አስተዋጽኦ ተሸላሚ እንደሚሆኑ ይፋ የተደረጉት በኢትዮጵያ የሕምክና አገልግሎት ዘርፍ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ሁለት ባለሀብቶች ናቸው፡፡ ከቢዝነስ ፎረሙ በተገኘው መረጃ መሠረት በአሜሪካ ሲማሩና ሲሠሩ ቆይተው ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ኢንቨስት በማድረግ ትልልቅ የሕክምና ተቋማትን የሚያንቀሳቅሱት አቶ ታምራት በቀለና ዶክተር አከዛ ጣዕመ ናቸው፡፡

 አቶ ታምራት የኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላብራቶሪስ እህት ኩባንያ ለሆነው ሜድፋርም ሆልዲንገስ አፍሪካ መሥራችና ዋና ሥራ አስፋጻሚ ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ. በ2004 ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ የላቦራቶሪውን ተቋም በአዲስ አበባ መሥርተዋል፡፡ በአፍሪካ ዓለም አቀፍ መሥፈርቶች የጤና ክብካቤ ዕውቅና በማግኘት የሚሠራ ተቋም ለመሆን የበቃ ላቦራቶሪ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በኢትዮጵያ ብቸኛው ፈቃድ ያገኘ ተቋም በመሆን የሚንቀሳቀሰው ይህ ላቦራቶሪ፣ ባለፉት አሥራ አንድ ዓመታት 900 ሺሕ ደንበኞችን ማፍራት መቻሉም የኩባንያው ዝክረ ታሪክ ይዘረዝራል፡፡ ባለትዳርና የአምስት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ታምራት ኑሯቸው በአዲስ አበባ ካደረጉ ሰንብተዋል፡፡ 

ዶ/ር አከዛ በበኩላቸው የቅዱስ ያሬድ ጠቅላላ ሆስፒታልንና በቅርቡም አሜሪካን ሜዲካል ሴንተርን ከሸሪኮቻቸው ጋር በመመሥረት፣ በሜዲካል ዳይሬክተርነት እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በግል ሆስፒታሎች ማኅበር ፕሬዚዳንትነት ማገልገላቸውም ይታወቃል፡፡ የሦስት ልጆች አባት የሆኑት ዶ/ር አከዛና አጋሮቻቸው የመሠረቷቸው የሕክምና ተቋማት፣ በአዲስ አበባና በአጎራባች አካባቢዎች ለሚኖሩ አንድ መቶ ሺሕ ታካሚዎች አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በአሁኑ ወቅትም ግማሽ ቢሊዮን ብር በሚጠጋ ካፒታል የሜዲካል ቱሪዝም ይፈጥራል ያሉትን ዘመናዊ ሆስፒታል ለመገንባት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ ባለፈው ዓመት አቶ አዲስ ዓለማየሁና አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ በአሜሪካ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ተሸላሚ እንደነበሩ ይታወሳል፡፡ 

 

 

 

ፖሊስ ዋና ተጠርጣሪ ያላቸውን አራት ሰዎች ከሷል

በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ሥር በምትገኘው የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ከከተማ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ፣ ሕገወጥ ግንባታዎችን ለማፍረስ የአረካ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በመሞከሩ ነዋሪዎች ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸው ታወቀ፡፡ 

የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የትውልድ ቦታ በሆነው የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዋና ከተማ አረካ ዙሪያ የሚገኙ ስድስት ቀበሌዎችን በከተማው ሥር ለማካለል፣ በሕገወጥ መንገድ ተገንብተዋል በተባሉ ከ940 በላይ ቤቶች ላይ ማዘጋጃ ቤት እንዲፈርሱ ሐሙስ ነሐሴ 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀለም መቀባት ጀምሮ ነበር፡፡ 

ነገር ግን ባለይዞታዎች የተገነቡትን ቤቶች በቀጥታ በከተማ ማካለሉ ውስጥ ማስገባት እየተቻለ ሊፈርስብን አይገባም በማለት በመቃወማቸው፣ በተጠቀሰው ዕለት ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ ግጭት መነሳቱን ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 

ፖሊስ የተወሰኑ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ቢያውልም፣ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ በድጋሚ ከረር ያለ ግጭት ተከስቷል፡፡ 

በተለይም በሁለተኛው ግጭት ባለይዞታዎቹ ድንጋይ መወርወር በመጀመራቸው፣ ፖሊስም በድብደባ አፀፋ መመለሱ ተገልጿል፡፡ ከ20 በላይ ሲቪሎችና አሥር የሚሆኑ የአፍራሽ ግብረ ኃይል አባላት መጎዳታቸው ታውቋል፡፡

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኢዮብ ዋቴ የተነሳውን ግጭትም ሆነ የደረሱ ጉዳቶችን አረጋግጠው፣ የብጥብጡ ዋና ተጠያቂዎች በሕገወጥ መንገድ ቤት የገነቡ ሰዎችና የእነሱ ተባባሪ ደላሎች ናቸው በማለት ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ግጭት ለማነሳሳት ዋነኛ የተባሉ አራት ሰዎች ክስ ተመሥርቶባቸው የጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸውም አቶ ኢዮብ ገልጸዋል፡፡

የቤቶቹን ሕገወጥነት አስመልክቶ ዋና አስተዳዳሪው፣ ‹‹ሕገወጦቹ ከደላሎች ጋር በመሆን ስድስቱ ቀበሌዎች ወደ ከተማ እንደሚካለሉ እያወቁ በሕገወጥ መንገድ ቤቶቹን ገንብተዋል፤›› ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ቤቶቹን መገንባት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ በተደጋጋሚ ግለሰቦች ምንም ዓይነት ግንባታ እንዳያደርጉ የወረዳው አስተዳደር ማስጠንቀቁን አቶ ኢዮብ አስታውሰዋል፡፡ 

እሳቸው የታሰሩት ሰዎች አራት ብቻ ናቸው ቢሉም፣ ምንጮች ግን የታሳሪዎች ቁጥር እስከ 40 እንደሚደርስ ይናገራሉ፡፡ 

ነገር ግን አቶ ኢዮብ ብዛት ያላቸው ሰዎች መቁሰላቸውን አልሸሸጉም፡፡ በፖሊስ በኩልም ሁለት ፖሊሶች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸውም አክለው ገልጸዋል፡፡ 

የከተማ ማስፋፋት ፕሮግራሙን አስመልክተው በሶዶና በቦዲቲ ከተሞችም ተመሳሳይ የማካለል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን፣ ችግሩ ግን የተፈጠረው አረካ ላይ ብቻ እንደሆነ አቶ ኢዮብ አስረድተዋል፡፡ 

በዋነኛነት ግጭቱ በተፈጠረበት የአረካ ማስፋፊያ ፕሮግራም በከተማው ዙሪያ የሚገኙ ስድስት የቀበሌ ገበሬ ማኅበሮችን ለማካለል ታቅዶለታል፡፡ ነገር ግን ግጭቱ የተቀሰቀሰው ዱቦ፣ አቹራ፣ ዶላና ኡቶ በተባሉት አራቱ ቀበሌዎች መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

 

// // <meta http-equiv=”refresh” content=”0; URL=/hirut.kidane.16?fref=ufi&_fb_noscript=1″ />// አደጋው በአማራ ውሃ ስራዎች ና ኮንስትራክሽን ድርጅት ተነስቱ ወደ ደሴ በመጓዝ ላይ እያለ በተለምዶ ኮብራ እየተባለ የሚጠራው መኪና እና አንድ ሞተር ሳይክል ተጋጭተው የተፈጠረ ነው። አደጋው የተከሰተውም ሞተረኛው የጭንቅላት መከላከያ ሄልሜት ይወድቅበትና እያሽከረከረ ሄልሜቱን ለማድረግ በሚሞክርበት ወቅት ነው ከመኪናው ጋር የተጋጨው። የመኪናው ሹፌር ወርዶ ሲመለከትም ሞተረኛው የገዛ ጓደኛው […]

(የትነበርክ ታደለ) ትናንት ምሽት የኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩ ከጋዜጠኞች ጋር ያደረጉትን የጥያቄና መልስ ቆይታ የተከታተለ ሰው እንደ ተለመደው የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ብዥ እንደሚልበት የታወቀ ነው። ጋዜጠኞቹ ራሳቸውን እየጨመቁና እየተሽቆጠቆጡ ለሚያቀብሏቸው ጥያቄዎች ሚንስትሩ ለራሳቸው ብቻ በሚመች መልክ ብቻ ሳይሆን ራሳቸውን ብቻ በሚያሳምን መልኩ ምላሽ ሰጥተው ዞር ብለዋል። ይደንቃል! አሁን አለም በሀገራችን ውስጥ የተከሰተውን ድርቅና ረሀብ በደምብ አብላልቶ እያወራው […]

የወያኔ ጉጅሌ አገዛዝ 7 መቶ አለቆች 5 ሻምበሎች 8 ሻለቆች 13 ኮሎኔሎች በድምሩ 33 የወያኔ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከሰሜን እዝ እና ከደቡብ ምስራቅ እዝ ታስረው የነበሩበት መኮንኖች ተግዘው አዲስ አበባ ቃሊቲ አለም በቃኝ ካለፍርድ መወርወራቸው በወታደራዊ ደህንነት መምሪያ ከፍተኛ መኮንን የሆኑና እስረኞቹ ተግዘው ወደ አለም በቃኝ ሲወርዱ የተመለከቱ የአይን እማኝ ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል። የአይን እማኙ […]

ሰላሳ ሶስት መኮንኖች ከየታሰሩበት እዝ ተግዘው አለም በቃኝ ተወረወሩ:: (ስም ዝርዝር ተያይዟል::) ……… #‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎EthiopianArmy‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Unity‬ ‪#‎Change‬  …. Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ….   የወያኔ ጉጅሌ አገዛዝ 7 መቶአለቆች 5 ሻምበሎች 8 ሻለቆች 13 ኮሎኔሎች በድምሩ 33 የወያኔ መከላከያ …

ሰላሳ ሶስት መኮንኖች ከየታሰሩበት እዝ ተግዘው አለም በቃኝ ተወረወሩ:: (ስም ዝርዝር ተያይዟል::) Read more »

ኢሳት ዜና ፦ ሃኪን ቲም ሰብዓዊ መብትን ከሚያፍኑ መንግስታት ጋር አብሮ መስራቱ ይፋ ከሆነ በኋላ፣ ከዚህ ዕኩይ ተግባሩ ይታቀብ ዘንድ በተደጋጋሚ ጊዜ ማሳሰቢያ ቢደርሰውም ፣ አሁንም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት አላቋረጠም ሲል ሂውማን ራይትስ ወች በሪፖርቱ ገልጿል። የጣልያኑ መረብ ጠላፊ ድርጅት ሃኪን ቲም ለተለያዩ መንግስታት የመገናኛ መረብ መጥለፊያ ቴክኖሎጂዎችን በመሸጥና ስልጠና በመስጠት ጭምር አምባገነን […]

የመከላከያው ዩሐንስ ገ/መስቀል አከራካሪ በነበረው የዛሬ ሶስት ዓመቱ ሹመት የሜጀር ጀነራልነት ማዕረጋቸውን ትከሻቸው ላይ ከመደርደራቸው ቀደም ብሎ በኮሎኔልነት ማዕረግ በምስራቅ ጎዴ ተመድበው ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡በጅጅጋ ቆይታቸው ወቅትም ተራ የጫት ነጋዴ የነበረችውን ሐዋን በፍቅር ማርከው ልጅ ለመውለድ በቅተዋል፡፡ ኮሎኔሉ ከሐዋ ጋር ከመተዋወቃቸው ቀደም ብሎ ግን ትዳር መስርተው የአባትነት ወግ ደርሷቸውም ነበር፡፡ተራ የጫት ነጋዴ የነበረችው ሐዋ ከኮሎኔሉ ከተጣመረች […]

የኩናማ ብሄረሰብ ኣባል የሆነችውና በ2007 ዓ/ም ሃገራቀፍ ምርጫ ዓረና_መድረክ ወክላ ለፌደራል ምክር ቤት የተወዳደረችው ወይዘሪት ኣብረሀት ረዳ ዛሬ ሓሙስ 07 / 12 / 2007 ዓ/ም በሸራሮ ከተማ በህወሓት ካድሬዎችና ፖሊሶች ታስራለች። ወይዘሪት ኣብረሀት ረዳ በካድሬዎችና በፖሊስ ልትታሰር የቻለችው በምርጫ ወቅት …

የኩናማዋ ፖለቲከኛ ታሰረች። Read more »

ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንግድ የሆነው የኢትዮጵያ አውሮፕላን ውስጥ የእቃ ማስቀመጫ ካርጎ ውስጥ በመደበቅ ማንነቱ ያልታወቀ አንድ ሰው ከኢትዮዽያ በመነሳት ያለምንም ችግር ስዊድን ገባ ሰውየው ኢትዮጳዊ ይሁን አይሁን የስዊድን መንግስት የተናገረው ነገር የለም የስዊድን ሚዲያዎች በግርምት ዜናውን በመዘገን ላይ ናቸው ‪ Man found in the trunk of Arlanda A man found in the trunk of a […]

በፍንዳታው የሟቾች ቁጥር ከዚህም ከፍ እንደሚል የተገመተ ሲሆን 500 ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል። የቻይና ዜና አገልግሎትን ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው፥ ፍንዳታዎቹ የተከሰቱት ሩሃይ ሎጂስቲክስ በተባለ አደገኛ የሆኑ ኬሚካሎችን በያዘ መጋዘን ላይ ነው። ፍንዳታው የፈጠረው የእሳት አደጋ በርካታ ህንጻዎችንና ተሽከርካሪዎችን ከጥቅም ውጪ አድርጓል። ሁለተኛው ፍንዳታ ከመጀመሪያው የበለጠ ከባድ እንደነበር የተነገረ ሲሆን፥ በሬክተር ስኬል 2 ነጥብ 9 የተመዘገበው የመሬት […]

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ከምርጫው ማግስት ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በፖሊስ ተይዘው ነሃሴ 6/2007 ዓ.ም እያንዳንዳቸው በ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ተጠይቀው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ዋስትናቸው በአቃቤ ህግና በፖሊስ መታገዱን የፓርቲው የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ በአመራሮቹ ላይ ላቀረበው ክስ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ነሃሴ 6/2007 […]

የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በከፍተኛ ስብሰባ ላይ መጠመዳቸውን ከቦታው ያገኘነው መረጃ አስታወቀ።በአዲስ አበባ ከተማ ከሃምሌ 25 ቀን 2007 ዓ/ም ጀምሮ በከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ሳሞራ የኑስና ሲራጅ ፈርጌሳ ስብሰባ መካሄዱና በስብሰባው እንደመወያያ ርእስ ሁኖ የቀረበውም አዲስ ሰራዊት ቢጨመርም አብዛኛው የሚፈርስና የሚበታተን በመሆኑ አሁንም የሰራዊቱ ይዘት አነስተኛ ነው። እናንተ ምን እያደረጋችሁ ነው? […]

ከወራት በፊት በም/ጠ/ሚኒስቴር ደመቀ መኮነን የመሰረት ድንጋዩ የተቀመጠው የመቅደላ ዩኒቨርስቲ ግንባታው ሳይጀመር የእርስ በእርስ ግጭት አስነስቷል። በመካነሰላም ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች የዩኒቨርስቲ ግንባታው እድል ለእኛ ወረዳ ሊሰጥ ይገባል፣እኛ ከሁሉም ወረዳዎች ለዞኑ መናገሻ ከተማና ለወሎ ዩኒቨርስቲ በከፍተኛ እርቀት ላይ ስለምንገኝ የዩኒቨርስቲ የመገንባቱ እድል ለእኛ ሊሰጥ ይገባል፣………… ወዘተ የሚሉ መከራከሪያዎችን በመያዝ አቤቱታና ቅሬታቸውን ለመንግስት ሀላፊዎች ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ይህን […]

በአገራችን በሰሜን ምስራቅ እና በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ መጠኑ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ጉዳዩ ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው ተመሳሳይ ድርቅ በመጪው አመት 2008 ዓ.ም በጥቅምት እና በህዳር ወር ሊከሰት እንደሚችል ባለሙያዎች እየጠቆሙ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ገዥው መንግሰት አሁንም የችግሩን አሳሳቢነት ወደ-ጎን በማድረግ ፤የስራዓቱ ደጋፊ እና አቀንቃኝ ከሆኑ ዲያስፖራ ጋር “አስረሽ ሚቺው” እያለ ከበሮ እየደለቀ ይገኛል፡፡ ሆኖም በአገራችን በተለይ […]

ከሓምሌ ወር 2007 ዓ/ም ጀምሮ መብራት በተደጋጋሚ በመቆራረጡና በመጥፋቱ ምክንያት ባለ ድርጅቶች ለኪሳራ መጋለጣቸው ተገለፀ።ምንጮቻችን እንደገለፁት በአዲስ አበባ ከተማ ካለፈው ሓምሌ ወር 2007 ዓ/ም ጀምሮ መብራት በተደጋጋሚ በመቆራረጡና በመጥፋቱ ምክንያት። በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰሩ የተለያዩ ድርጅቶች ለኪሳራ መጋለጣቸውን የገለፀው መረጃው መንግስት መፍትሄ እንዲሰጥበት በማለት ባለድርጅቶቹ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ ቢያቀርቡም። ችግሩን አይቶ መፍትሄ የሚሰጥ አካል ባለመገኘቱ ምሬታቸውን […]

ታገሉ! ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ /ከዝዋይ እስር ቤት/ #Ethiopia : ስለሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ፍርድም ሀሳቡን ሰንዝሯል ቦሌ አካባቢ ብርዱ ጠንከር ያለ ነበር፡፡ ከቦሌ ብራስ ወደሚሊኒየም አዳራሽ በሚወስደው ቀጭን መንገድ ላይ ወንዱም ሴቱም በፍጥነት ይራመዳል፡፡ ከታክሲ በሁለቱም አቅጣጫዎች የወረዱ ሰዎች …

ታገሉ! ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ /ከዝዋይ እስር ቤት/ : ስለሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ፍርድም ሀሳቡን ሰንዝሯል Read more »

በቦረና ክልል በኖኖ-አሎ ቀበሌ በሚኖሩ ዜጎች ላይ ጥቃት ተፈጸመ ሲሉ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድን ሀላፊ ተናገሩበቦረና ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በኖኖ-አሎ ቀበሌ በሚኖሩ ዜጎች ላይ ባካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናትና ጥቂት ተባባሪዎቻቸው ብሄር-ተኮር ጥቃት ደርሶባቸዋል ሲል ሰ መ ጉ የተሰኘው የሰብዓዊ …

በቦረና ክልል በኖኖ-አሎ ቀበሌ በሚኖሩ ዜጎች ላይ ጥቃት ተፈጸመ :: Read more »

ከየመን አየር ማረፊያ ትራንዚት ላይ በወያኔ ደህንነቶች የታፈነው ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ እስከዛሬ በማይታወቅ ቦታ ታስሮ ከፍተኛ ቶርች እየተፈጸመበት ሲሆን ባለፈው ሊጠይቁት የሄዱት የእንግሊዝ አምባሳደር እንዳሉት አንዳርጋቸው ካለሁበት ሁኔታ ይልቅ ሞትን እመርጣለሁ እንዳላቸው የሃገራቸው ጋዜጣ አምባሳደሩን ጠቅሶ ማውጣቱ ይታወሳል:: http://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=102550 ከዚህ …

ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ ቃሊቲ “ዋይት ሃውስ” እስር ቤት ተዘዋወረ:: ሁለት ነብሰ ገዳይ ወንጀለኞች አብረውት ታስረዋል:: Read more »

የመለስ ዜናዊ ግፍ = የገብረመድህን አርዓያ ምስክርነት! ስለ ሀውዜን ጭፍጨፋና ስለ ሌሎች የህወሓት ሚስጥሮች በቀዳሚነት እየተናገሩ ከሚገኙት መካከል ገብረመድህን አርዓያ የተባሉ የቀድሞ የህወሓት አመራር ይገኙበታል፡፡ አቶ ገብረ መድህን እንደሚሉት የሀውዜን ጭፍጨፋ ሚስጥር የሚጀምረው የህወሓት ሰራዊት ከትግራይ ውጭ መዋጋት እንደማይፈልግ አቋን …

የመለስ ዜናዊ ግፍ – የገብረመድህን አርዓያ ምስክርነት! Read more »

አርበኞች ግንቦት ሰባትን በ አሸባሪነት በምዕራባዊያን ዘንድ ለማስፈረጅ ያደረገው ከንቱ ውትወታ ያልሰመረለትና በተቃራኒው ጫናው የበረታበት ወያኔ የነጽነት ኮከቡን አንዳርጋቸው ጽጌ ሰውሮ ካስቀመጠበት ያፈና እስር ቤት ወደ ቃሊቲ ተዛውሮ መታየቱ ታወቀ። ከየመን አየር ማረፊያ ትራንዚት ላይ በወያኔ ደህንነቶች የታፈነው ታጋይ አንዳርጋቸው …

አንዳርጋቸው ጽጌ ቃሊቲ ማራሚያ ቤት ታዬ! Read more »