(በብአዴን/ኢህዴን 35ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ የጻፍኩት) የህወሓት ፈተና – ‹‹የታገልኩት፣ የቆሰልኩት፣ የሞትኩትም እኔ ብቻ ነኝ እና የታሪኩ ባለቤትም የትግሉ ውጤት ይበልጥ ተጠቃሚም መኾን ያለብኝ እኔ ነኝ››። ይህ ትርክት ጫፍ ሄዶ ሄዶ ኢዲሞክራሲያዊነት እና ጠባብነት የወለደው ኾኖ ወደ ትምክህተኝነት ሊያድግ ይችላል። ኣብዛኞቹ የዚህ ፈተና ሰለባ የኾኑ የድርጅቱ ኣባሎች ብ1993ቱ የድርጅቱ የውስጥ ትግል የተሸኙ ሲኾን የነሱ ደጋፊዎች እዚሁ የማሕበረሰብ ሚዲያ ላይ የሚያሳዩት ትምክህት አሁንም አለ። ድርጅቱ የዚህ አይነቱ አዝማሚያ ዋናው ፈተናው ሲኾን በቀጣይ የቀሩ ትርፍራፊ የማጽዳት ስራዉን አጠናክሮ የማካሄድ ሓላፊነት አለበት። ይህንን ፈተና ተቋቁሞ እኩልነት በመቀበል የታገልነው በጋራ እና ለጋራ ጥቅም ነው በማለት እዚህ ለበቃ አብዛኛው አባሉን በዚህ አስተሳሰብ ዙሪያ ማሰለፍ ከቻለ ህወሓት ውጤታማ ይኾናል። ብአዴን፦ ያለፉ ስርዓቶች፣ በተለይ የአጼኣዊው የዘውድ ስርዓት፣ ናፍቆት። ይህ በእኩልነት ያለማመን የአንዳንድ የብአዴን ትልቁ ፈተና ነው። የጥንት ታሪኮች የአንድ ብሔር ይኾኑ ዘንድ የመመኘት ከዚህ በዘለለም የትምክህት ሃይሉ የሚያራምደው በአለፉት ስርአቶች የተፈጸሙ በደሎች የመካድ አዝማሚያ። ብአዴን የዚህ አይነቶቹ አባላት ሽኝቶ ብቻ ሳይኾን የተፈጠረው አዲስ የኢትዮጵያዊነት የእኩልነት ትርጉም አልጥም ብሏቸው ወደ ድሮ አመለካከታቸው በመኮብለል ብዙ አባላቶቹ እና አመራሮች ሳይቀር ከመስመሩ ወጥተዋል። አንዳንዶቹ ወደ ትክክለኛ ቀለማቸው በመሄድ ፓርቲዎች አቋቁመው ብአዴንን ዞረው ታግለዉታል። ይህንን ፈተና ተቋቁሞ የጋራ ሀገር ነው ያለን የልፉት ስርዕእቶች ሁላችንንም በድለዋል። እነዚህ ስርዓቶች ላይመለሱ በተባበረ ክንድ ተወግደዋል። ስርዓቶቹን ለማስወገድ የአማራ ብሔር ተወላጆችም አኩሪ ተጋድሎ መፈጸማቸውን ማስተማር […]

በ10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የተመረጡ የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና የምክር ቤት አባላት ፣ የኢህአዴግ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ደኢህዴን 1 ጓድ ኃ/ማርያም ደሳለኝ 2 ጓድ ሽፈራው ሽጉጤ 3 ጓድ ደሴ ዳልኬ 4 ጓድ ተስፋዬ በልጅጌ 5 ጓድ ሲራጅ ፈጌሳ 6 ጓድ ሬድዋን ሁሴን 7 ጓድ መኩሪያ ኃይሌ 8 ጓድ መለሰ ዓለሙ 9 ጓድ ተ/ወልድ አጥናፉ ኦህዴድ 1 ጓድ ሙክታር ከድር 2 ጓዲት አስቴር ማሞ 3 ጓድ ወርቅነህ ገበየሁ 4 ጓድ ዳባ ደበሌ 5 ጓድ ድሪባ ኩማ 6 ጓድ አብዱልዓዚዝ መሐመድ 7 ጓድ በዙ ዋቅቤካ 8 ጓድ ኡመር ሁሴን 9 ጓድ በከር ሻሌ ህወሓት 1 ጓድ አባይ ወልዱ 2 ጓድ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል 3 ጓድ ዶ/ር ቴድሮስ ኣድሓኖም 4 ጓድ በየነ ምክሩ 5 ጓዲት አዜብ መስፍን 6 ጓድ አለም ገ/ዋህድ 7 ጓድ ጌታቸው አሰፋ 8 ጓድ ዶ/ር አዲስአለም ባሌማ 9 ጓዲት ፈትለወርቅ ገ/ሄር ብአዴን 1 ጓድ ደመቀ መኮንን 2 ጓድ ገዱ አንዳርጋቸው 3 ጓድ አለምነው መኮንን 4 ጓድ ብናልፍ አንዱ አለም 5 ጓድ ተስፋዬ ጌታቸው 6 ጓድ ዶ/ር አምባቸው መኮንን 7 ጓድ አህመድ አብተው 8 ጓድ ከበደ ጫኔ 9 ጓድ ካሳ ተ/ብርሃን የኢህአዴግ ምክር ቤት አባላት ህወሓት 1. ጓድ ኪሮስ ቢተው 2. ጓዲት ኣረጋሽ በየነ 3. ጓድ ምኪኤለ ኣብርሃ 4. ጓድ ማሙ ገ/ሄር 5. ጓድ ጎይትኦም ይብራህ 6. ጓድ ኢሳያስ ታደሰ 7. […]

(ስሉሥ ወልደሂወት) “ማንም የቆመ የሚመስለው ቢኖር እንዳይወድቅ ይጠነቀቅ”! መጽሓፍ ቅዱስ የሰው ልጅ ፍላጎት ሁሌ የሚያድግና የማይሟላ በመሆኑ የለውጥ ጥያቄን ለመመለስ ሁሌም ሰለተሻለ አማራጭ፣ ስለተሻለ ዘዴ ወይም ስትራቴጂ ማሰቡና መነጋገሩ ተገቢና ጤናማ መሆኑ የማይታበል እውነት ነው፡፡ በዲሞክራሲያዊ ማህበረሰብ ዘንድ የተቀደሰና ከነቀፋና ትችት የፀዳ የፖሊሲ አቋም ወይም የፖሊሲ አፈፃፀም የማይኖር መሆኑም እንደዚሁ። ዜጐች በግልም ይሁን በተደራጀ መልኩ በነፃነትና ከማንኛውም ተጽእኖ በጸዳ መልኩ የፖሊሲ አማራጮችን መተቸችና የመልካም አስተዳደር ግድፈቶችን ነቅሶ ማውጣት የሚችሉበት ሁኔታ ከተፈጠረ ያ ማህበረሰብ የታደለ ነው ማለት ይቻላል፡፡ የፖለቲካ መሪዎች በዓቅም ውስንነት፣ በግንዛቤ እጥረት፣ የግል ፍለጎት በማሰቀደም ወይም በቅንነት እጦት ምክንያት የሕዝቦችን ጥቅም አደጋ ውስጥ ሊከቱ የሚችሉበት እድል ሰፊ ነው። በመሆኑም የፖሊሲ አማራጮችንና የአፈፃፀም ግድፈቶችን ከመተቸት ባላፈ ፖሊሲውን ለማስፈፀም ሃላፊነት የወሰዱ የፖሊቲካ ድርጅቶች አመራር፣ ውስጣዊ ድርጅታዊ ህይወትና የአመራሩ የግል ማንነት ሳይቀር አብጠርጥሮ ማወቅና መተቸት በሰለጠነው ዓለም የተለመደና ውጤታማ የሆነ የዲሞክራሲ ባህል ነው፡፡ ከሰሞኑ አቶ ዳዊት ገብረ እግዚአብሔር የተባሉ ዜጋ በተለየ ሁኔታ በህወሓትና ህወሓት በሚመራው የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የልማትና መልካም አስተዳደር ፖሊዎችና አፈጻጸም ላይ የሰላ ትችት በመሰንዘር ላይ ይገኛሉ፡፡ የአቶ ዳዊት ትችት ከግል ገጠመኝና ትዝብት በመነሳት በአጠቃላይ በስርዓቱ፣ ስርዓቱ በቆመባቸው ምሰሶችና የማስፈፀምያ ፖሊሲዎች ስትራቴጂዎች እንደዚሁም የድርጅቱና የድርጅቱ አመራር ዓቅምና ህዝባዊነት ላይ ጥያቄ አስነስቷል፡፡ ቀደም ብዬ እንዳልኩት ከፖሊሲ የተሻለ ፖሊሲ፣ ከተሻለው ፖሊሲ እጅግ የተሻለ ፖሊሲ መኖሩ የማይቀር ስለሆነ፤ አቶ ዳዊት ስለተሻለ አመራር፣ […]

የ2007 የኢትዮጵያ ምርጫ ተጠናቆ ሙሉ ውጤቱ ይፋ ከሆነ እነሆ ሳምንታት አለፉ። የምርጫው ሂደት ያስነሳው የፖለቲካ ትኩሳትና አቧራ በርዶ ፤ የምርጫው ተዋናዮች ግርግርና አስረሽ ምቺው ሰክኖ ምርጫ 2010 ከሰበር ዜናነት ወደ ታሪክ ማህደርነት የሚተላለፍበት ደረጃ ላይ እንገኛለን። የዚህን ምርጫ ታሪካዊ አንድምታና በታሪክ መዝገብ ውስጥ የሚኖረው ስፍራ በታሪክና ሶሻል ሳይንስ ተመራማሪዎች ወደፊት የሚለካ ሲሆን ይህ ጽሁፍ የዚህን ምርጫ ሁለት ለየት ያሉ ባህርያት ላይ ትኩረት በመስጠት ለመቃኝትና ለመዳሰስ ይሞክራል። በመጀመሪያ ይህን ምርጫ ካለፉት ምርጫዎች የተለየ የሚያደርገው ለምርጫ የወጣው ህዝብ ብዛት (turn out) ሲሆን ከተመዘገበው 36.8 ሚሊየን ህዝብ 34.8 ሚሊየን ህዝብ በነቂስ ወጥቶ በምርጫው ተሳትፏል። በዚህም በኢትዮጵያ ታሪክ ታላቁ ቀጥተኛና ነጻ የሆነ  ህዝባዊ ተሳትፎ የታየበት የፖለቲካ ክስተት ያደርገዋል። ይህን መሰል ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር የታየበት ምርጫ በአገራችን ብቻ ሳይሆን በብዙ አገሮች ከሚታዩት የህዝብ የምርጫ ተሳትፎዎች ጋር ሲንጻጸር ከፍተኛ አሃዝ ከተመዘገበባቸው አንዱ የሚያደርገው ሲሆን ይህም የምርጫውን የዲምክራሲያዊ መሰረት ያሰፋ፤ ፉክክራዊ ባህርይውን ያጎለበትና ለተአማኒነቱንም ዋስትና እንዲኖረው ካደረጉት ምክንያቶች እንደ አንዱ ሆኖ ሊጠቅስ የሚያስችል ነው። ከሁሉ በላይ ግን ለምርጫ ከወጣው የህዝብ ቁጥር አሃዝ ጀርባ ያለው ዋናው ቁምነገርና ይህንን ምርጫ ካለፉት ምርጫዎች በይዘት የተለየ የሚያደርገው ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ባለቤትነት መብቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ በስፋትና በጥልቀት እየተረዳ መምጣቱ የተንጸባረቀበት፤ ለዲሞክራሲ ስርአት ያለው ፍላጎትና ቁርጠኝነት እየሰፋና እየጎለበት መምጣቱን በግብር ያረጋገጠበት ምርጫ መሆኑን ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫን የማይገሰስና የማይቀለበስ ቋሚ ባህሉ […]

(አዲስ ከድሬዳዋ) መንግስት ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ በማድረግና በሚፈለገው ደረጃ ባይሆንም ኢንቨስትመንቶችን በማስተናገድ ኢኮኖሚው እያደገ ነው፡፡ ዋነኛው የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽና የስራ እድል ፈጣሪ መንግስት በሆነበት ሁኔታ በመንግስት ሜጋ እና ትናንሽ ፕሮጄክቶች አማካኝነት ወደገበያው እየተለቀቀ ያለው ገንዘብና ከገበያው የሚሰበሰበው የገንዘብ መጠን ልዩነቱ ሰፊ በመሆኑ የግሽበት ተጋላጭነታችን ከፍተኛ ነው፡፡ ባንድ ወቅት ከ40 ፐርሰንት በላይ ደርሶ የነበረው የሀገራችን የዋጋ ግሽበት አሁን ወደ ባለአንድ አሀዝ ግሽበት(ከ10 ፐርሰንት በታች) መውረዱ እንደትልቅ ስኬት እየተነገረ ነው፡፡ ለመሆኑ ቀድሞ ነገር ኢንፍሌሽኑ እንዴት ጀመረ፣ አሁንስ እንዴት ሊቀንስ ቻለ ኢንፍሌሽኑ የጀመረው በተደጋጋሚ እንደሚነገረው መንግስት በሚያስተገብራቸው በርካታ ፕሮጀክቶች አማካኝነት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ወደገበያው እየለቀቀ ስለሆነ ነው፡፡ በኢኮኖሚስቶች የሚመከረውና መንግስት ኢንፍሌሽኑን ለማረጋጋት መውሰድ ያለበት እርምጃ በዋናነት ወደገበያው እየለቀቀው ያለውን ገንዘብ መቀነስ ነው፡፡ መንግስት ግን ይህ ኢኮኖሚያዊ እድገቱን ያቀዘቅዝብኛል በሚል ተመራጭ እርምጃ አድርጎ አልወሰደውም፡፡ አንድ አመት በከፊል ሞክሮት የነበረ ቢሆንም ቀጣይነት ግን አልነበረውም፡፡ መንግስት ይልቁንም በገበያው ላይ ያሉ ተጫዋቾች ላይ ቁጥጥሩን በማጥበቅ፣ ቁጠባን በማበረታታትና የግብር መሰብሰብ አቅሙን ለማሳደግ ጥረት በማድረግ ነው ችግሩን ለመፍታት የሞከረው፡፡ በእርግኑን ይህንን አማራጭ በመከተሉ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገቱ ሳይቀዛቀዝ ኢንፍሌሽኑን በእጅጉ መቀነስ ችሏል፡፡ ሆኖም ለዚህ የተወሰኑ ዜጎች ያለአግባብ ዋጋ እንዲከፍሉም ተደርጓል፡፡ ሁለቱን ልጥቀስ የመንግስት ሰራተኞች፡- በ1994 ዓ.ም. የነበረው 400 ብር የመግዛት አቅም በ2004 ከነበረው 1000 ብር ጋር ተመጣጣኝ በሆነበት ሁኔታ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ በእነኚህ አስር አመታት 250 ፐርሰንት ሊያድግ ይገባ ነበር፤ […]

የጀርመን ሬድዮ አማርኛ አገልግሎት አምስተኛውን ዙር የፌዴራልና የክልል ምርጫ በተመለከተ ከሶስት ጋዜጠኞች ውይይት አድርጎ ነበር። የራዲዮ ጣቢያው ጋዜጠኛ ሂሩት መለሰ፡- ከየማነ ናግሽ (ሪፖርተር ጋዜጣ)፣ ከ.ይልማ ኃ/ሚካኤል (የጀርመን ሬድዮ የበርሊን ወኪል) እና ከገበያው ንጉሴ(የጀርመን ሬድዮ የብራስልስ ዘጋቢ) ጋር፤ ስለቅድመ ምርጫውና ድምፅ የተሰጠበት ሂደትና ውጤቱ እንዲሁም የወደፊት ዕጣፈንታና የውጭ ኃይሎች ሚና አስመልክቶ ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱ ከተነሱት መህል፡- 1/የማነ ናግሽ (ሪፖርተር ጋዜጣ):- *የተቃዋሚ ተወካዮች እንዳይታዘቡ ተከልክለዋል። ውጤቱ ለጥርጣሬ ክፍት ያደርጓል። *አባሎቻቸውን ገለልተኛ ታዛቢ ሆነው የቀረቡት የአገርውስጥ ማህበራት የፓለቲካ ድጋፍ እንዲሰጡ የተደራጁ እንጂ ገለልተኛ አይደሉም። *የውጭ ኃይሎች ላይ መንጠልጠል ጥገኛ አስተሳሰብ ነው። የጉዳዩ ዋና ባለቤት ህዝብ ነው። ህዝቡ ድምፄን ተሰርቋል ብሎ ካመነ እስከመቼ(ለምን) ቁጭ ብሎ ያያል? *ተቃዋሚዎች በራሳቸው ለማሸነፍ አልገቡም። ተበታትነውና ዓቅመቢስ ሆነው ነበር የቀረቡት። አንድም ተቃዋሚ በተወዳደረባቸው ቦታዎች በሙሉ ቢያሸንፍ መንግስት ለመመስረት የሚችል አልነበረም። * በእኛ ዓይነት ብዝኃ-ህብረሰብ ውስጥ በዚህ ደረጃ ማሸነፍ አይቻልም። አንድም ድርጅት እንዲህ ዓይነት የአስተሳሰብ አንድነት መፍጠር አይቻለውም። ውጤቱ ለኢህአዴግ አስደንጋጭ እንጂ መልካም ነገር አይደለም።ድርጅቱ ያየዘው አቋም መፈተሽ አለበት። *ተቃዋሚዎችን በማድቀቅ ሳይሆን ሜዳውን ክፍት አድርጎ በተሻለ አስተሳሰብ ለመብለጥ መስራት አለበት። *ነገሩ ሂዶ ሂዶ ወዴት እንደሚያደርሰን አይታወቅም። —– 2/ ይልማ ኃ/ሚካኤል (የጀርመን ሬድዮ የበርሊን ወኪል)፡- *ማን አሸናፊ ሆኖ እንደሚወጣ ሳይታለም የተፈታ ነበር። *የሸንጎ ምርጫ ከኳስ ጨዋታ ጋር እኩል ነው። ገለልተኛ ዳኛና ሜዳ በሌለበት አይደረግም። *ተቃዋማ ፓርቲዎች ምንም ተስፋ አልነበራቸውም። *ዕርዳታ ሰጪ […]

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ግንቦት 19/2007 የ5ኛውን አገራዊ ምርጫ ጊዜያዊ ዉጤት ገለፀ፡፡ የመጨረሻዉ ዉጤት ሰኔ 15/2007 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚገለጽ መሆኑን እንደተጠበቀ ሆኖ ጊዜያዊ የምርጫው ዉጤት ‹‹እስካሁን በደረሰን ሪፖርት መሰረት ብቻ›› በማለት ቦርዱ ገልጿል፡፡ በቦርዱ ዛሬ የተገለፀው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤቶች ግዜያዊ ውጤት እንደሚከተለው ነው፡፡ 1. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካሉት 547 ወንበሮች የ442ቱ ጊዜያዊ የምርጫ ዉጤት ተ/ቁ ክልል የምርጫ ክልል/ወንበር ብዛት ያሸነፈው ወንበር ብዛት ያልተገለፁ (ቀሪ) ወንበር ብዛት አሸናፊ የፖለቲካ ፓርቲ 1 ትግራይ 38 31 7 ህወሓት/ኢህአዴግ 2 አፋር 8 6 2 አብዴፓ 3 አማራ 138 107 31 ብአዴን /ኢህአዴግ 4 ኦሮሚያ 178 150 28 ኦህዴድ/ኢህአዴግ 5 ኢትዮጵያ ሶማሌ 23 16 7 ኢሶዴፓ 6 ቤንሻንጉል ጉምዝ 9 7 2 ቤጉህዴፓ 7 ደቡብ ብ/ብ/ህዝቦች 123 95 28 ደኢህዴን/ኢህአዴግ 8 ጋምቤላ 3 3 – ጋሕአዴን 9 ሐረሪ 2 11 — ሐብሊኦህዴድ/ኢህአዴግ 10 ድሬዳዋ ከ/አስተዳደር 2 11 — ኢሶዴፓኢህአዴግ 11 አዲስ አበባ ከ/አስተዳደር 23 23 – ኢህአዴግ ድምር 547 442 105 2. ለክልል ምክር ቤቶች ካሏቸው  1900 ወንበሮች የ1508 ጊዜያዊ የምርጫ ዉጤት ተ/ቁ ክልል የወንበር ብዛት ያሸነፈው ወንበር ብዛት ያልተገለፁ (ቀሪ) ወንበር ብዛት አሸናፊ የፖለቲካ ፓርቲ 1 ትግራይ 152 123 29 ህወሓት/ኢህአዴግ 2 አፋር 96 77 19 አብዴፓ 3 አማራ 294 230 64 ብአዴን /ኢህአዴግ 4 […]

 መግቢያ የአሜሪካ መንግስት እ.አ.አ በ2009ዓ.ም በኢራቅ የሚገኘዉን አምባገነናዊ የሳዳም ሁሴን አገዛዝ ለማስወገድ ከሌሎች ምዕራባውያን ሀገራት ጋራ በመሆን ባካሄደው ወረራ የሳዳም ሁሴን አገዛዝን አስወግደው በፋንታው ጠንካራ የኢራቅ መንግስት ሳያቋቋሙና መልሶ ግንባታ ሳያካሄዱ በመቅረታቸው የእልቂቷ ምድረ-ኢራቅ እንዲትፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡ በቀደምት የሰው ልጅ ስልጣኔ የምትታወቀው የባቢሎን ምድረ ኢራቅ በአሁኑ ወቅት በተቃራኒው ተሰልፋ ምድረ እልቂት፡ ምድረ ጦርነት፡ ምድረ ዱንቅርና ሆናለች፡፡ ቀድሞውም በሳዳም አገዛዝ ወቅት የነበረው የ”ሱኒ-ሺዓ” ፖሎቲካ ውጥረት በአከባቢያዊ ጎሳ ግጭት ላይ ተደምሮ የሀገሪቱ ስጋት የነበረ በመሆኑ ከአሜሪካና አጋሮቿ ወረራ ቡኋላ በፈራረሰችውና በመንግስት አልባዋ ምድረ ኢራቅ ነግሶና ግሎ የስንቱን ንጽሃን ዜጎች ህይወት በቀላሉ ቀጥፏል፡፡ ይህ አስከፊ ጦርነት መንግስት አልባ ሊባል የሚትችል ኢቅን በማምጣቱ እንደ IS አይነቱ ሰው-በላ አረመኔያዊ ቡዱን በሃማኖት ሽፋን እንዲፈጠር አድርጓል፡፡ የሰሞኑ የአረብ አብዮት ተከትሎ በሶሪያ መንግስት ላይ የተነሳዉን ህዝባዊ አመጽ ከህዝብ በመንጠቅ የኢራንና ሺዓ አከባቢያዊ የበላይነትን ለማስቆም በሳዑዲ ዓረቢያና ኳታር የሚመራው የገልፍ አረብ ሱኒ ሀገራት ከአሜሪካ ጋር በመተባበር የበሽር አል-አሳድ አገዛዝን ለመገልበጥ ISን ጭምሮ የIS ገባር የሆኑ የተለያዩ ፅንፈኛ ቡዱኖችን አስታጥቋል፡፡ በዚህም IS በሰው ሀይል፡ በገንዘብ፡ በትጥቅና ሌሎች ወታደራዊ ሎጂስቲኮች በሚገባ ተደራጅቷል፡፡ ይህም የIS መቋቋም ጀርባ ማን እንዳለ ፍንጭ ሊሰጠን ይችላል፡፡ የIS ጉዞ አልቃይዳን የማያስታውስ አለ? ኦሳማ ቢን ላዲንን የማያስታውስ አለ? የታሊባን ተዋጊዎችን የማያስታውስ አለ? የሴፕቴምበር 2001 የኒውዮርክ መንትያ ህንፃዎች ጥቃት የሚረሳ አለ? በዓለማችን ኣቻ ያልተገኘለት፡ አለ የተባለ ፖሎቲከኛ፡ ምሁር፡ የሃይማኖት […]

ኢስላሚክ ስቴት ወይም ISIS/ISIL በመባል የሚታወቀው አሸባሪ ድርጅት በሊቢያ በኢትዮጲያውያንን ክርስቲያኖች ላይ የፈፀመውን ግድያ ቪድዮ ባለፈው እሁድ ማሰራጨቱን ተከትሎ፤ ድርጊቱን ለማውገዝ ዛሬ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ ያንን አስመልክቶ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒስተር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ከጽ/ቤቱ ያገኘነውን የመግለጫው ጭማቂ ጽሑፍ ከዚህ በታች አትመነዋል፡፡ 1) የተሳካ ሰልፍ ተካሂዷል፣ * ህዝቡ ከጫፍ ጫፍ ወጥቷል፣ * በሰላማዊ መንገድ በጋራ ሀዘኑ ዙሪያ፣ በቀጣይ የጋራ ጥረቶች ዙሪያ ያጠነጠነ መልዕክቱን አስተጋብቷል፣ * አንድነቱን በማጉላት ሽብርተኞች ለመፍጠር የፈለጉትን የመከፋፈል ሴራ ሙስሊም ክረስቲያን ሳይል በጋራ ተሰልፎ በመምጣት አክሽፏል፣ * ሽብርተኝነት ሃይማኖታዊ መሰረት እንደሌለው በማንኛውም ሃይማኖት ጀርባ መሸሸሸግ እንደማይገባ አረጋግጧል፣ * ISIS ማንኛውንም ሃይማኖት እንደማይወክል ፅንፈኝነትና አክራሪነትን እንዲሁም የሽብር ተግባርን ብቻ እንደሚወክል ስለዚህም የጋራ ጠላት መሆኑን በአንድ ድምፅ አስረግጧል፡፡ * የፀረ ሽብርና አክራሪነት ትግሉን ከመንግስት ጎን ቆሞ ለማጧጧፍ ያለውን ፅኑ አቋም አስተጋብቷል፡፡ * ህገ ወጥ ስደትን በመላ ህዝቡ ተሳትፎ ማስወገድ እንደሚገባ በቁጭት ገልጿል፣ * በሀገራችን ሰርቶ መለወጥ የሚቻልበት ዕድል እየተፈጠረ በመሆኑ ከነክብራችን በሀገራችን ሰርተን እንለወጥ የሚል ፅኑ አቋም አስተጋብቷል፣ * የሃይማኖት አባቶችንና የመንግስትን መልዕክት በጥሞናና በትእግስት አዳምጦ የቀጣይ ትግል ባለቤትነቱን አረጋግጧል፣ * በመሆኑም መንግስት የከበረ ምስጋና ያቀርባል፣ * ከህዝቡ በተጨማሪም የሀገራችን ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ከአንዳንዶች በስተቀር የደረሰው አደጋ በሰው ልጆች ላይ የተቃጣ ኢሰብአዊ ድርጊት መሆኑንና የኢትዮጵያውያን የጋራ ሀዘን መሆኑን፣ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በሚደረገው ጥረትም የበኩላቸወን ድርሻ የሚወጡ መሆኑን በፓርቲዎች […]

IS ወይም ISIS/ISIL በመባል የሚታወቀው አለም-ዓቀፍ አሸባር ቡድን አል ፉርቃን በተባለ ሚዲያ በኩል “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን አባላት የሆኑ የመስቀሉ ተከታዮችን” በአረመኔያዊ አኳኋን የገደለበትን ቪዲዮ መልቀቁ ይታወሳል፡፡ ቪዲዮውን መሰረት በማድረግ እንደሚከተለው ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡ ዋና ዋና ነጥቦች፡- * ነሳራ (Christians/The people of the book) * ኢብን ቴይሚያ (Ibn Teymiyyah) * ጂዝያ (ያላመኑ ላይ የሚጣል ግብር) * የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን አባላት የሆኑ የመስቀሉ ተከታዮች (The Oriental Orthodox Church (Ethiopia & Egypt)) ይሀ ቪዲዮ የ29 ደቂቃ ርዝመት ያለው ሲሆን በጥቅሉ በነሳራ/በክርስትያኖች (The people of the book) ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በዚህም ነሳራን በአራት ክፍሎች ያስቀምጣል፡፡ 1/Western Catholic Church (Europe & other Eastern countries). 2/ The Oriental Orthodox Church (Ethiopia & Egypt). 3/ The Eastern Orthodox Church (Russia, Greece, Many Mediterranean states). 4/ The Protestant Church (Germany, America, Scotland, Norway and Holland) ከዚህ ቪዲዮ አላማ አንፃር ሲታይ ይህ ቪዲዮ ያነጣጣረው የኢትዮጵያና ግብጽ የጋራ መለያ በሆነው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ላይ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ ለዚህም ነው የግድያውን ምክንያት “ጠላት የሆነችው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን መስቀል ተከታዮች” በማለት የገለፀው፡፡ ከ22፡30 – 23፡40 ባሉት ደቂቃዎች ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን አባላት የሆኑ የመስቀሉ ተከታዮች ሁለት (2) መሰረታዊ መልዕክት ያላቸውን ለማስተላለፍ የሞከረው፡፡ እነኝህም፡ 1/የኢስላሚክ ኢስቴት (IS) አገዛዝ ስርዓትን እስልምናን በመቀበል እንዲቀላቀሉ ጥሪ ማቅረቡ 2/ ከባርነት ወደ ነጻነት እንዲሸጋገሩ – አንድ ግዛትና አንድ መሪን በመቀበል ከ24፡00 […]

በሳውዲ፣ የመን፣ ደቡብ ኣፍሪካና ሊብያ በኢትዮጵያውያን ላይ ችግር ባጋጠመ ጊዜ በቦታው የሌሉ ብዙ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ መንግስት በነዛ ኣገራትና ቡድኖች ላይ እንዲወስደው የሚጠብቁት እርምጃ ኣርበኛዊ እርምጃ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ ጥሎበት (በባህሪው) ኣርበኛዊ ዲፕሎማሲ ኣያራምድም፡፡ ቢያንስ መንግስት በኣንዳንድ ወገኖች የሚነሳበትን የ”ወኔ-ቢስነት” ክስ ለመከላከልና ለዜጎቹ እንደሚቆረቆር ለማሳየት ያክል እንኳን (ባያደርገዉም) በቴሊቪዥን ብቅ ብሎ ዘራፍና ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ኣይሆንለትም ወይም ኣያምንበትም፡፡ ይሄ ማለት ግን መንግስት ምንም ኣይነት እርምጃ ኣይወስድም ማለት ኣይመስለኝም ፡፡ በኢትዮጵያውያን ላይ ችግርና ጥቃት በደረሰ ቁጥር እኛ ዜጎች እንደምናሳየው ኣይነት ቁጣ የመንግስት ፊት (ግንባር) ላይ ባናየዉም በጊዜው እንደየሁኔታው የተሻለ የሚለው እርምጃ ይወስዳል የሚል ግምት ኣለኝ፡፡ ይሄንን ባህሪው ተቃዋሚዎቹ የፖለቲካ ነጥብ ለማስቆጠር ኣንዳንድ ደጋፊዎቹ ደግሞ የሚደግፉትን ፓርቲ/መንግስት ባህርይ በደንብ ካለመረዳት ኣሊያም በስሜትና ሃዘኑና ጥቃቱ በሚፈጥርባቸው ተፅእኖ ምክንያት መንግስትን ይወቅሳሉ፡፡ ለነገሩስ የኛን ስሜትና ምክር እየተከተለ እርምጃ የሚወስድ መንግስት ቢሆን ኖሮ ይሄኔ ከሱዳንና ግብፅ (በኣባይ ምክንያት)፣ ከሳውዲ ኣረቢያ (በዜጎች ምክንያት)፣ ከኤርትራ (በሄሊኮፕተር ምክንያት) እንዲሁም ከሌሎች ኣገሮች ጋር ጦርነት ውስጥ እንገባ ኣልነበር ? የሰሞኑ የ ISIL ጉዳይ ግን ትንሽ ስሜትን ይፈታተናል፡፡ ድህነት ኣንገሽግሽዋቸውና የቤተሰቦቻቸውን ኑሮ ለመቀየር የሰሃራ በረሃን ኣቋርጠው የመሞትና የመትረፍ ኣጋጣሚው እኩል የሆነበትን የሜዲትራኒያን ባህር የጀልባ ጉዞ ለማድረግ የተዘጋጁትን ወጣት ወገኖች በኣደባባይ ኣንገታቸው ሲቀላና ሰረሸኑ ማየትን የሚያክል ዘግናኝ ነገር የለም፡፡ ህዝባችን በሃዘንም በቁጭትም ኣደባባይ ወጥቶ ሆ ቢል፣ እስቸኳይ የኣጸፋ እርምጃ እንዲወሰድ ቢጠይቅ ኣይገርምም፡፡ ጥያቄው […]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስትያን ሲኖዶስ ዛሬ ሚያዝያ 13/2007 ባወጣው ባለ9 ነጥብ መግለጫ፡- በሊቢያ ውስጥ በተደረገው አሰቃቂ ድርጊት ቤተ ክርስቲያንኒቱ እጅግ ያዘነች መሆኗን ገልጾ በዚህ ግድያ ውስጥ ግን ሟቾቹ ሰማዕት በመሆን የተጠቀሙ ጀግኖች እንጂ ተጐጂዎች እንዳልሆኑም ጭምር ማሰብ እንደሚገባ ገልጿል፡፡ በነገው ዕለት በአዲስ አበባ የሚገኙ ገዳማት እና አድባራት በአጠቃላይ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት ጸሎተ ፍትሐት እንዲያደርሱ ጥሪ አስተላለፏል፡፡ በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ከሚያዚያ 14 ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት በሁሉም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ምህላ እንዲያረግ ቅዱስ ሲኖዶስ አያይዞ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ አክሎም ለሟቾቹ የሰማዕትነት ክብርን በቀኖናው መሠረት መስጠት እንዲቻል ቤተሰቦቻቸውን የሚያውቁ ምዕመናን ፎቶአቸውንና ስማቸውን አሰባስባው ለቅዱስ ሲኖዶስ እንዲያቀርቡ አዝዟል፡፡ ሙሉ የሲኖዶስን ሙሉ መግለጫ ለማንበብ ከሥር ካለው ምስል ያንብቡ ወይም እዚህ ጋር በመጫን (link) ዳውንሎድ ያድርጉ፡፡ *********** — More from Horn Affairs AmharicSendek | የጁነዲን ሳዶ ባለቤትን ጨምሮ 29 ሰዎች በሽበርተኝነት ተከሰሱETV | የግንቦት 7ቱ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን ተይዞ ለኢትዮጵያ ተላልፎ ተሰጥቷልማዕተብም መስቀልም በግለሰቦች ነፃነት ውስጥ የሚካተት ነው – ዶ/ር ሺፈራው ተክለማርያምየዩኒቨርስቲዎች ሃይማኖታዊ ስነስርአትና አለባበስ ደንብን በመቃወም በሽብር የተሳተፉ ግለሰቦች ጥፋተኛ ተባሉሕገ-መንግስት እንዲያከብሩ ሲመከሩ – በሃይማኖታችን ጣልቃ ተገባ ይላሉ (ሚ/ር እውነቱ ብላታ)ማዕተብ ከሂጃብ

የኢኮኖሚ ችግር ሲፈጠር ስደተኛዉን ኢላማ ኣድርጎ ጥቃት መሰንዘር በደቡብ ኣፍሪካ ብቻ የታየ ችግር ኣይደለም። ግሪክ፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ሩስያ እና በብዙ ኣገሮች የታየ የተለመደ ክስተት ነው። ህንዳውያን በግሪክ ጎዳና ለመንቀሳቀስ ኣዳጋች እየሆነባቸው እንደሆነ ሁሉ ሞስኮም ኣሁን የውጭ ዜጋ እንደልቡ እማይንቀሳቀስባት ከተማ ሁናለች፤ ለምን ቢባል የኢኮኖሚ ችግር።በነዚህ ኣገሮች ከፈተኛ የፀረ ስደተኛ ጥቃትም እሚፈፀምባቸው ኣገሮች እየሆኑ ነው:: ይሄ ነገር ከዘር እና ከጥቁረት እያገናኙ ደቡብ ኣፍሪካውያንን የቀኝ ገዢዎች ንድፈ ሃሳቦች እየተጠቀሙ “ድሮስ ጥቁር….ለነፃነት ኣቅም ያልደረስ እንስሳ” ምናምን እያሉ የትምክህት ቃል መሰንዘር የጉዳዩን ትክክለኛ ገፅታ ኣለመረዳትን ነው እሚያሳየው። የኢኮኖሚ ችግር ወደ ፖለቲካዊና የፀጥታ ችግር እንደሚቀየር ሳይታለም የተፈታ ሃቅ ነው። በሩዋንዳም በሌሎች ኣገራትም የታየው ይህ ነው። እንዲህ ኣይነት ሁኔታ ለሰነፍ ፖለቲከኞች ጥሩ ኣጋጣሚ ይፍጥራል፤ የሰነፍ ፖለቲካ ደግሞ ቀላል ግን ኣውዳሚ ስለሆነ ዉጤቱ ኣሁን ደቡብ ኣፍሪካ ላይ እያየን ያለነው ኣይነት እልቂት ያስከትላል።ኣንዱን በማስወገድ “መፍትሄ” ለመሻት መጣር ነው የሰነፍ ፖለቲካ ማለት።ለዚህ መዋቅራዊ መደላድል እሚፈጥረው ግን የኢኮኖሚ ችግር ነው። ሁቱዎች ቱትሲዎች ላይ ገጀራቸውን ከማሳረፋቸው በፊት የዋጋ ንረት እና ስራ ኣጥነት ሂወታቸው ላይ ገጀራዉን ኣሳርፎ ነበር። ይህ ቀቢፀ ተስፋነት ሰለፍ ፖለቲከኞች ተመቻቸው እና ዘርን ለማጥፋት ተጠቀሙበት። ደቡብ ኣፍሪካ ላይ እየተፈፀመ ያለ ነገርም ከጄኔቲክ ሳይሆን ከኢኮኖምያዊ ሁኔታ መመሰቃቀል እሚመነጭ ነገር ነው። የደቡብ ኣፍሪካ ለየት እሚያደርገው የኣፓርታይድ ስርኣት በፖለቲካው ረገድ “ሲገረሰስ” የኢኮኖሚው ሁናቴ በነጮች እንደተያዘ እንዲቀጥል መፈቀዱ ነው። ማንዴላ ከዚ ዉጪ ኣማራጭ […]

ክቡር አቶ አባይ ፀሐዬ የህ.ወ.ሓ.ት/ኢህአዴግ መስራች አባል ታጋይና በአሁኑ ግዜ በሚኒስትር ማአርግ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማእከል ዋና ዳይርክተር ናቸው፡፡ ከጋዜጠኛ ዘርአይ ሀ/ማርያም በኦህዴድ ታሪክና የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳዮች ቆይታ አድርገዋል፡፡ ሙሉ ቃለ-ምልልሱ ከዚህ በታች በጽሑፍ የቀረበ ሲሆን፤ ቪዲዮውን ደግሞ ከታች መመልከት ይችላሉ፡፡ —— ዘርአይ ኃ/ማርያም:- በትጥቅ ትግሉ ዘመን ኦህዴድ የኢህአዴግ አንድ አባል ድርጅት ሆኖ መቆሙ የነበረው ፋይዳ ምን ነበር? አቶ አባይ ፀሐዬ፡- የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ አንድ የኢህአዴግ አባል ድርጅት ሆኖ መደራጀቱ በመጋቢት 1982 ዓ.ም ፋይዳው ከዛ በፊት የኦሮሞ ህዝብ በዴሞክራሲያዊ አላማ ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝብ አስተሳስሮ የሚያታግለውና የሚመራው ዴሞክራሲያዊ ድርጅት በማጣቱ የተፈጠረ ድርጅት ነው፡፡ ከዛ በፊት የነበረ የኦሮሞ ህዝብ ትግል የብሄር ጭቆናው የሌላው በደልንም ከተጀመረበት /ከተፈጠረበት ግዜ ጀምሮ ሲታገል የቆየ ህዝብ ነው፡፡ በብሄራዊ መብቱም ለአጠቃላይ የኢኮኖሚያዊና ዴሞክራሲያዊ አጠቃላይ መብትም፡፡ ግን ከዛ በፊት የነበሩ ድርጅቶች የተለያዩ በኦሮሞ ህዝብ ስም የተደራጁ ድርጅቶች ቢኖሩም አንደኛ ጠንካራ የህዝብ ድጋፍ እና ጠንካራ የህዝብ ማደራጀት ስራ አልነበረባቸውም፡፡ ወደ ህዝብ ገብተው ህዝቡን አደራጅተው ከህዝቡ ጋር ሆኖ የህዝቡን ስሜት አዳምጠው ሀይል የፈጠሩ አቅም የፈጠሩ ጠንካራ ድርጅቶች ጠንካራ የትጥቅ ትግል ሰራዊት የፈጠሩ አልነበሩም፡፡ ስለዚህ እየተደነቃቀፉ እየተኳላሹ ወደ አጎራባች ሀገሮች ወጣገባ እያሉ ነው ግዚያቸውን ያሳለፉትበአብዛኛው፡፡ ሁለተኛ መላውን የአማራ ህዝብና የኢትዮጵያ ህዝብ እንደጠላት የሚወስዱ ናቸው የነበሩ፡፡ ይህ ደግሞ የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎትና ጥያቄ አልነበረም፡፡ የህዝቡ ጥያቄ የፖለቲካ ዲሞክራሲ የማንነትና የኢኮኖሚ […]

(ኃይለሚካኤል ዘስላሴ) በዓለም ያለት የተለያዩ የሕግ ሥርዓቶች ከሚሰማሙባቸው የሕግ ጽንስ ሐሳቦች አንዱ የሕጋዊ ሰውነት ጽንስ ሐሳብ ነው፡፡ በዚህ ጽንስ ሐሳብ መሠረት ከተፈጥሮ ሰው በተጨማሪ እንደተፈጥሮ ሰው የሚቆጠር ወይም ሰው የሆነ አካል አለ፡፡ በዚህም መሠረት ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ ማለት ነው፡፡ አንደኛው ሰው የተፈጥሮ ወይም ግለ ሰብ ሲሆን ሁለተኛው ሰው ደግሞ በሕግ የሰውነት መብት (ግዴታም ጭምር) ያለው ወይም የተሰጠው አካል ማለትም ማኅበር፣ የንግድ ማሕበር ወይም ድርጅት ነው፡፡ በመሠረቱ ማነኛውም ሰው የተፈጥሮም ይሁን በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ወይም ያለው አካል የመብትና የግዴታ ባለቤት ነው፡፡ በዚህም ውል መዋዋል፣ የነብረት ባለቤት መሆን፣ መክሰስና መከሰስ ይችላል፡፡ ከቤተሰብ ሕጎች እና ከአንዳንድ የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎች በስተቀር የየአገሩ ሕጎች በተፈጥሮ ሰውና በሕግ የሰውነት መብት ያለው አካል በእኩልነት ተፈጻሚነት አላቸው፡፡ የተፈጥሮ ሰው የመብትና ግዴታ ባለቤት የሚሆነው እና በሕግ ኃላፊነት የሚኖረው በተፈጥሮ ሰው በመሆኑ ነው፡፡ ግዑዝ የሆኑ አካላት ማለትም ማሕበራት የንግድ ማኅበራት እንዲሁም ድርጅቶች እንደ ተፈጥሮ ሰው የሚቆጠሩትና በሕግ የሰውነት መብት ይጣቸዋል የሚል ጥያቄ ለመመለስ በርካታ ንደፈ-ሐሳቦች ተቀምሯል፡፡ እነዚህ በርካታ ንድፈ-ሐሳቦች በሁለት ክፍሎች ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያወ ምናባዊ ወይም ሕግ ወለድ ንድፈ ሐሳብ (fiction theory) የሚባለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እርግጠኛ ንድፈ ሀሳብ (Real theory) በመባል የሚታወቀው ነው፡፡ እነዚህ ንደፈ ሃሳቦች ጥልቅ መሠረት እና ትንታኔ ያላቸውና አመሠራረታቸውና ዕድገታቸው ሰፊ እና ከመንስት አመሠራረት ጋር የተያያዘ ቢሆንም ለአጠቃላይ ግንዛቤ ይረዳል በሚል በሁለቱም ንድፈ […]

ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን በአባይ ወንዝ ፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ በቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃ ሲያደርጉት የነበረውን ድርድር ወደ ፖለቲካ ኮሚቴ ከፍ በማድረግ ለወራት የዘለቀ ድርድር በሶስቱ አገራት ረዕሰ መዲናዎች ላይ ሲያካሂዱ ቆይተዋል። እነዚህ ድርድሮችም ፍሬ አፍርተው አገራቱ የአባይ ወንዝን ዓለም አቀፍ መርህዎችን ተከትለው ለመጠቀም የሚያስችላቸውን ስምምነት ትናንት በሱዳን ካርቱም ተፈራርመዋል። በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ በግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ ኤልሲሲ እና በሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር መካከል የተፈረመው ስምምነት ሶስቱንም አገራት እኩል ተጠቃሚ እና ዓለም አቀፍ መርህዎችን መሰረት ያደረገ ነው ተብሎለታል። የዚህን ስምምነት ሰነድ ሙሉ ቃል ከአስረጅ ጋር እንደሚከተለው ቀርቧል። መግቢያ የግብፅ አረብ ሪፐብሊክ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራሊያዊ ዴሞክራሲያ ሪፐብሊክ እና የሱዳን ሪፐብሊክ እየጨመረ የሚገኘውን ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብቶቻቸውን የመጠቀም ፍላጎትን መሰረት በማድረግ የናይል ወንዝ የግብፅ፣ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ህዝቦች ህይወት እና ልማት ምንጭ የሆነ ሀብት መሆኑን በመገንዘብ ሶስቱ አገራት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ለተዘጋጁት ቀጣይ መርህዎች ይሰራሉ። በዚህ የስምምነቱ የመግቢያ ክፍል ላይ ቀደም ሲል ግብፅ የናይል ወንዝ ለግብፃውያን የህይወት ጉዳይ ለኢትዮጵያውያን ግን የቅንጦት ያህል ለመልማት ብቻ የሚፈልጉት አደርጋ የያዘችውን አቋም በመቀልበስ ናይል ለሶስቱም አገራት ዜጎች ህይወት እና ልማት መሰረት መሆኑን በእኩል እውቅና የሰጠ ነው። 1. የትብብር መርህ – በጋራ መግባባት ላይ የተመሰረተ ትብብር፣ የጋራ ፍላጎት፣ መልካም አሳቢነት፣ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ እና የአለም አቀፋዊ ህጎች መርህዎችን የተከተለ – የታችኛውም ሆነ የላይኛው የተፋሰሱ ሀገራት […]

ነብሱን ይማረውና ነውጠኛው ቅንጅት በ1997ዓ.ም የማይናቅ የህዝብ ድምጽና ድጋፍ ያገኘው ከኢህአዴግ የተሻለ ብቃት ስለነበረው ወይም ያቀረበው የፖሊሲ አማራጭ ሳቢ ስለነበረ እንዳልሆነ ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡ ወይም የህዝባችን ኑሮ ሊቀይር የሚችል የመነጠቀ ሐሳብ በማቅረብ አልነበረም፡፡ ጅብ በቀደደው ውሻ ይገባል እንደሚባለው የኢህአዴግ ንዝህላልነትና ቸልነትነት እንጂ! ይህን ያልኩት ያለምክንያት አይደለም፡፡ ኢህአዴግ ከቅንጅት ቡድን ጋር ለክርክር ሲቀርብ ማሰብ እና ማድረግ የነበረበት ብዙ ስትራተጂዎች ነበሩ፡፡ እንደምናስታውሰው ቅንጅቶች በነበረባቸው የብልጣ ብልጥነት (ተራ የአራዳነት) ስብእና በከፍተኛና በሚያስገርም ጥበብ የኢሀአዴግን ደካማ ጎን ተጠቅመውበታል፡፡ የኢህአዴግ ቸልተኝነት፣ በክርክር ታክቲክ በልጦ አለመገኘት እንዲሁም እዚህም እዛም ይታዩ የነበሩ የመልካም አስተዳደር እጦት ፣ የአፈጻጸም ግድፈቶች እና የልማት እጥረቶችን በሚሊዮን ግዜ በማጋነን ፣ ልብ የሚነኩ ቃላቶች በመደርደር የተወሰነ ህብረተሰብን በማሳመን ረገድ ቅንጅቶች ከፍተኛ ብልጫ አሳይተዋል፡፡ በኔ ግምት ይህን ሊያደርጉ የቻሉበት ዋናው ምክንያት 1ኛ የኢህአዴግ ጠንከር ላለ ፖለቲካዊ ክርክር በቂ ዝግጅት አለማድረግ እና የሰራውን ስራ በሚማርክ ቃለት እና በሚመጥን መልኩ መግለጽ አለመቻሉም ጭምር ነው፡፡ 2ኛ ደግሞ መቶ በመቶ በሚያስብል መልኩ አጀንዳው በኢህአዴግ የፖለቲካ መስመር ፣ ርእዮት ዓለምና ኢህአዴግ በሚመራው የመንግስት የፖሊሲ አፈጻጸም ዙርያ መሆኑ ነው፡፡ ታድያ ብልጣ ብልጦች የቅንጅት ተከራካሪዎች እነሱ ገምጋሚዎች ኢህአዴግዬ ደግሞ ተገምጋሚ ሆና መቅረብዋ ምን ያህል ለነሱ አመቺ ሜዳ እንደነበረ ማንም ሰው ሊስተው አይችልም፡፡ ቅንጅቶች ይህን ክፍተት በመጠቀም ኢህአዴግ የሰራውንና ያልሰራውን ስራ አፈር ድሜ አበሉት፡፡ ኢህአዴግ በትምህረት ፣ በልማት ፣ በጤና ፣ በድህነት ቅነሳ […]

Editor’s note:በቅርቡ ከጄ/ል ጻድቃን ጋር ያደረግነውን ቃለ-መጠይቅ በተከታታይ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ በቃለ-መጠይቁ ከተነሱት ርዕሰ-ጉዳዮች በተወሰኑት ላይ ዶ/ር አረጋዊ በርኸ አስተያየታውን ልከውልናል፡፡ዶ/ር አረጋዊ ከህወሓት መሥራቾች አንዱ ሲሆኑ እስከ1971 በሊቀመንበርነት፣ እስከ1978 ደግሞ በወታደራዊ መሪነት ያገለገሉ ሲሆን፤ የማርክሳዊ ሌኒናዊ ሊግ ትግራይ(ማሌሊት) ምሥረታን ተከትሎ ከተደረገው የአመራር ሽግሽግ በኋላ ድርጅቱን ለቅቀው በአውሮፓ ነዋሪ ናቸው፡፡ ጄ/ል ጻድቃን ገ/ትንሳዔ ደግሞ ከ1971 ጀምሮ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል፣ ከ1978 ጀምሮ ደግሞ የማሌሊት የፖሊት ቢሮ አባል እና የህወሓት ሠራዊት ቺፍ ኦፍ ስታፍ በመሆን እስከትጥቅ ትግሉ ማብቂያ አገልግለዋል፡፡ —- (ዶ/ር አረጋዊ በርኸ) ባለፉት ሳምንታት ህወሓት የተመሰረተበት 40ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የህወሓት መሪዎች ብቻ ሳይሆኑ የኢህኣዴግ ባጠቃላይ መጀመርያ በመቀሌ ቀጥሎ በኣዲስ ኣበባ ተሰባስበው ለኣንድ ወር ሙሉ የሃገሪቱን ሃብት ሲያባክኑና ሲዝናኑበት እንደከረሙ ተገንዝበናል። መቸም የኣምባገነኖች ጭንቀት ማስተንፈሻ ነው መሰለኝ፣ ህዝብ በረሃብና በስራ-ኣጥነት ሲጠቃ፤ ሃገርን በዴሞክራሲያዊ ስርዓት እጦት ስትታፈን ሁሉም ኣምባገነኖች ማስተዳደር ሲያቅታቸው ምክንያት እየፈጠሩ በሃገርና በህዝብ ንብረት እንዲህ መቀለዳቸው የተለመደ ለመሆኑ ሩቅ ሳንሄድ የደርግ ኢሰፓና የነፃድቃን ማሌሊት ምስረታ ፌስታ ማስታወሱ በቂ ነው። ኣሁንም ሃገር በቀልና ዓለምኣቀፍ ጥናቶች እንደሚያስረዱት፣ ኢትዮጵያ የተጠመደችበትን ዙርያ-መለስ ቀውስና ህዝቡ እየደረሰበት ያለው ስቃይ መረኑ ኣልፎ ሃገሪቱ ጭራሽ ስርዓት-ኣልባ ወደ እምትሆንበት ደረጃ እያሽቆለቆለች መሆንዋን በጥናት የተደገፈ መረጃ ቢያቀርቡም፣ ግብዞቹ የኢህኣዴግ መሪዎች መራር ሓቁን ከመጋፈጥ ይልቅ፣ ሃገሪቱ የበለፀገች – ህዝቡ የደላው ይመስል፣ ኣሸሼ-ገዳሜ ሲሉ ይገኛሉ። ህወሓት/ኢህኣዴግ 40ኛ ዓመት-በዓል ብሎ ቅጥ ያጣ ድግስ በጣለበት […]

(አዲስ ከድሬዳዋ) በሶሻል ሚዲያ(በተለይ በፌስቡክ) ብዙ ጊዜ አስተማሪና ምክንያታዊ የሆኑ ፅሑፎችን በመፃፍ የሚታወቀው ዶክተር ብርሀነ መስቀል አበበ ሰኚ ሰሞኑን ከአማርኛ ጎን ለጎን ኦሮምኛም የፌደራል መንግስት፣ እንዲሁም የድሬዳዋ እና የአዲስአበባ አስተዳደሮች የስራ ቋንቋ እንዲሆን የሚጠይቁ ፅሑፎችን በተከታታይ እያወጣ ሰፊ ውይይትም እየተደረገ ነው፡፡ ሀሳቡንም በግሌ እደግፈዋለሁ፡፡ነገር ግን በምን መልኩ ነው የስራ ቋንቋ የሚሆነው , እንዲሁም በአተገባበር ሒደት ምን ሊያጋጥም ይችላል የሚለው ግን የታሰበበት አይመስልም፡፡ ኦሮምኛን የስራቋንቋ ይሁን ስንል የሀገሪቱ የቋንቋ አጠቃቀም ፖሊሲ ምን ይመስላል የሚለውን በጨረፍታ ማየት የሚያስፈልግ ይመስለኛል፡፡ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ የላትም፡፡ በሀገሪቱ የሚነገሩ ቋንቋዎች ሁሉም እኩል ናቸው፡፡ በርካታ ወይም አነስተኛ ተናጋሪ ስላለው አንድ ህዝብ በአፍ መፍቻ ቋንቋው እንዳይማር፣ አገልግሎት እንዳገኝ፣ እንዳይዳኝ፣ . . . . አይከለከልም፡፡ሆኖም ከኢኮኖሚ አቅም እና የተማረ የሰው ሀይል ውስንነት ጋር ተያዞ በመማሪያነት እያገለገሉ ያሉ ቋንቋዎች ከ30 አይበልጡም(በርግጥ ይህ ከ90 ፐርሰንት በላይ ኢትዮጵያውያንን ይሸፍናል)፡ ስለዚህ ሁሉም ቋንቋ እኩል ከሆኑ አንድን ቋንቋ የፌደራል የስራ ቋንቋ አድርገህ ሁሉም ክልሎች በትምህርት ቤቶቻቸው እንዲስተምሩት፣ በጋራ መግባቢያነት እንዲጠቀሙት፣ . . ለመወሰን የተለየ መነሻ ያስፈልጋል፡፡በዚህ ረገድ አማርኛ በ ታሪክ አጋጣሚ በብዙ ቦታዎች በሁለተኛ ቋንቋነት፣ በጋራ መግባቢያነት ( lingua franca) ና በመንግስት ቋንቋነት ሲያገለግል ስለቆዬ በሚል መነሻ የፌደራሉ መንግስት የስራቋንቋ እንዲሆን በህገ መንግስቱ ተወስኗል፡፡ ኦሮምኛስ ኦሮምኛ በሀገሪቱ በርካታ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋ ነው፣ ሆኖም ቋንቋው ከኦሮሚያ ውጪ በሁለተኛ ቋንቋነት እምብዛም አገልግሎት አይሰጥም፣ ልክ እንደ ትግርኛና […]

የቀድሞው ጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት አፈጻፀም ሂደት ላይ የነበራቸው አቋም በወቅቱ ከነበረው የጋራ አመለካከት ሊከሰት የሚገባው ተፈጥሮአዊ ክስተት ነው እንጂ አገር ለመጉዳት በማሰብ አይደለም በማለት ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ገለጹት፡፡ ጄኔራሉ ይህንን የተናገሩት፤ በጦርነቱ ወቅት መለስ ለጦር መሣሪያ ግዥ በሚወጣው ገንዘብ መጠን ላይ ተቃውሞ ነበራቸው የሚለውን ስሞታ በመጥቀስ ላቀረብንላቸው በሰጡት ምላሽ ነው፡፡ አንዳንዶቻችን ኤርትራ ልትወረን ትችላለች ብንልም ሌሎች አትወረንም የሚል አመለካከት እንደነበራቸውም ጠቅሰዋል፡፡ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ኤታማጆር ሹም የነበሩት ጄኔራል ጻድቃን፡- ጦርነቱ ድንገት የመጣ ቢሆንም የመከላከያ ሀይሉን የማደራጀት ሥራ ሲሠራ የነበረ መሆኑን የገለጹት ጄኔራል ጻድቃን፤ በዚህም ረገድ በአንድ ሚሊየን ፓውንድ ክፍያ የእንግሊዝ ኤክስፐርቶችን በመቅጠር የአየር ሀይል እና የአየር መከላከያ ሲስተም ጥናት መሠራቱን፣ የመካናይዝድ፣ ፓራኮማንዶና ኮማንዶ ሀይሎች ስልጠና እና የመሳሰሉ እንዲሁም የአዲስ ምልምል ወታደር የትምህርት ደረጃ 10ኛ ክፍል እንዲሆን እና የነባሩንም ትምህርት የማሳደግ ተግባራት መካሄዳቸውን አውስተዋል፡፡ እነዚህ ይህም በጦርነቱ ወቅት የሠራዊታችንን ብዛት ከ55,000 ወደ 350,000 ሲያድግ ያንን ሊሸከም የሚችል አቅም እንዲኖር ማስቻሉን አስረድተዋል፡፡ በጦርነቱ ወቅት የሴንትራል ኮማንድ አባል የነበሩት ጄኔራል ጻድቃን፡- መለስ ዜናዊ ለጦር መሣሪያ ግዥ በሚወጣው ገንዘብ መጠን ላይ ተቃውሞ እንደነበራቸውና ‹‹ሌሎች ፕሮግራሞችን ሳናፋልስ ባለው በጀት ጦርነቱን እንፈጽም›› የሚል አቋም እንዳራመዱ ያረጋገጡ ቢሆንም፤ ያ አቋም ግን ሁሉም አመራር ይጋራው ከነበረው ለኢኮኖሚ ቅድሚያ ከመስጠት አመለካከት የሚመነጭ አድርገው እንደሚረዱት እንጂ፤ ‹‹አንዱን ለመወንጀል ሌላውን [ለማመስገን] አልጠቀምባቸውም›› ብለዋል፡፡ የጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ሙሉ አስተያየት […]

የደርግ ሥርዐት መገርሰስን ተከትሎ የቀድሞው ሠራዊት እንዲበተን ቢደረግም 9,000 ገደማ ወታደራዊ ኤክስፐርቶች የአዲሱ መከላከያ ሠራዊት አካል ሆነው እንዲቀጥሉ መደረጉን ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ አወሱ፡፡ ሰሞኑን ከሆርን አፌይርስ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ የቀድሞውን ሠራዊት የመበተን ውሳኔ ድህረ-ምክንያት (rationale)፤ ከአብዮታዊ ለውጥ ርዕዮተ-ዓለማዊ አመለካከት እና ከሠራዊቱ የደርግን ወንጀሎች ፈጻሚ የነበረ ከመሆኑ የመነጨ መሆኑን ጄኔራሉ አብራርተዋል፡፡ የቀድሞ ሠራዊት በመሰናበቱ የተጎዳ ቤተሰብ እንዳለ እንዲሁም የአፈጻጸም ሂደቱን በተመለከተም የሚቀርብ ትችት ሊኖር እንደሚችል እንደሚረዱ ከጠቀሱ በኋላ ውሳኔው በመሠረቱ ግን ትክክል ነበር ብለዋል፡፡ አሁንም መለስ ብለው ሲያስቡትም፤ የቀድሞው ሠራዊት ከአዲሱ የታጋይ ሠራዊት ጋር ተቀላቅሎ ይቀጥል ቢባል ሀገር ሊከላከል የሚችል፣ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ዋዜማ ላይ የነበረውን ሠራዊት ያህል ብቃት ያለው ሠራዊት አይሆንም ነበር፡፡ ይልቁንም የተለያዬ የፖለቲካ ሀይሎች የሚጎትቱት ሀይል ይሆን ነበር ብለዋል፡፡ በሌላ ሀገር ሄደው ያጋጠማቸውም ተሞክሮ ያንን አመለካከት እንዳጠናከረላቸው ነው የጠቆሙት፡፡ ይሁን እንጂ ከቀድሞ ሠራዊት ‹‹ክሬም›› የሆነውን ክፍል ወደአዲሱ ሠራዊት እንዲመለስ መደረጉን ጠቅሰው፤ ይህ ተቺዎች የሚዘሉት ሀቅ ነው ብለዋል ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ፡፡ የሽግግር መንግስቱ ሠራዊት ቺፍ ኦፍ ስታፍ የነበሩት ጄኔራል ጻድቃን፤ ከቀድሞ ሠራዊት አባላት መሀል ከደህንነት እና ከኢሠፓ መዋቅር ግንኙነት ያልነበራቸው፣ ራሺያ ሄደው የሰለጠኑ፣ 9,000 ወታደራዊ ኤክስፐርቶች – 7,000 ከእግረኛ እና 2,000 ከአየር ሀይል – በአዲሱ ሠራዊት እንዲቀጥሉ ተደርጓል ብለዋል፡፡ በ1983 የህወሓት ታጋዮች ብዛት 85 ሺህ ገደማ የነበረ ሲሆን አዲሱ ሀገራዊ ሠራዊት ሲደራጅ ከ32-35ሺህ የሚሆኑት እንደተሰናበቱም አስታውሰዋል፡፡ የስልጠና፣ የጥናት እና […]

(ራማቶሀራ ዴርቶጋዳ) ፅንፈኛው ወንድሜ! የልቤን ልንገርህ፤ ለዛሬ እንኩዋን ልብ ብለህ አድምጠኝ! ሕመሜ ይመምህ፤ሃሳቤ ያሳስብህ፤ስጋቴ ስጋትህ ይሁን፤ጭንቀቴም ይጭነቅህ፡፡ እባክህንማ አንዴ ዦሮህን ስጠኝ፤ህሊናህን አንዴ ከነጎደበት የማንአለብኝነት፤የትዕቢትና የትምክህት ዓለም ላንዴም ቢሆን ገታ አርገህ መልሰውና እኔን እህትህን ስማኝ፡፡ምናልባት ዛሬ ባትሰማኝ ነገ በሚፈጠረው ሁኔታ ዕድሜ ልክህን ሊፀፅትህ የሚችል ከፍተኛ ችግር ሊከሰት ይችላልና ግድ የለህም ስማኝ! አዎን! እኔም አንተም የአባቶቻችንን ታሪክና አገር እናውቃለን፤ባለፉት ስርዓቶች የኔም ያንተም ወገኖች የደረሰባቸውን ሁሉ እናውቃለን!!! እስኪ ስለዚህ ጉዳይ በግልፅ እናውራ:: ታድያ እኔ መሰረታዊ ናቸው የምላቸውን በገዢ መንግስታት ደረጃ በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሱትን ሰብዓዊ ግፎች በወፍ በረር አስቃኝሃለው፤በዚህም ከውስጤ ያለው ቁስል ምን ያህል ያመረቀዘ እንደ ሆነ ላሳይህ እውዳለሁና ከቻልክ አንተም በኔ ቦታ ሆነህ ላፍታም ቢሆን አስበው! የታሪክን ሰበዝ ስንመዝ ግዜ ላለመፍጀት እንዲሁም የዚህ ፅሁፍ ዓላማው የኔን የእህትህን ስሜት በተቻለ መጠን ትጋራ ዘንድ ስንቅ የሚሆንህን መረጃ ማስጨበጥ ነውና ለውይይት ያህል ከሃ/ስላሴ ጀምሮ እስከ ደርግ ድረስ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀሙትን ዘግናኝ መንግስታዊ ግፎችን አንድ ሁለት እያልኩኝ አነሳልሃለው፡፡ ታድያ ወንድሜ! የምፅፈው ከልቤ ነውና አንተም ከልብህ አንብበህ ተረዳኝ፤የምፅፈው ለክርከርና ለሂሳብ ውርርድ አይደለምና! እስኪ ወንድሜ! አንተን በመጠየቅ ልጀምር! እውነት ስለ አፄ ሀ/ስላሴ ያለህን ስሜት ምንድን ነው? በጎ ወይስ መጥፎ? ስለ ደርግስ? እውነቱን እንነጋገርና አንተና መሰሎችህ እኮ ሀ/ስላሴን ሞዓ አምበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ፤መንግሰቱን ደግሞ ጉዋዱ፤ቆራጡ፤አገር ወዳዱ፤ጀግና እያላችሁ የሌላቸውን የዘር ሃረግና መለኮታዊ ስልጣን ሰጥታችሁ ስታወድሱዋቸው ነው የምትኖሩት! ወንድሜ እኔና ወገኖቼ […]

በግንቦት ወር በሚካሄደው 5ኛ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሰማያዊ ፓርቲ ለማወዳደር ያዘጋጃቸው አንዳንድ ዕጩዎች ዕጣ ስላልደረሳችው በዕጩነት እንዳይቀርቡ መደረጋቸውን ፓርቲው ገለፀ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በዌብ ሳይቱ እና በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው ዘገባ ስሞታውን እንደሚከተለው አሰምቷል፡፡ ——— አዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 5 ለመጭው ምርጫ ለተወካዮች ምክር ቤት ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ሊቀርቡ የነበሩት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ከቀረቡት 17 ዕጩዎች መካከል በተጣለ ዕጣ ወድቀዋል›› በመባላቸው ለመጭው ምርጫ በዕጩነት እንዳይቀርቡ መደረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል በዕጩነት በቀረቡበት ወረዳ 5 የምርጫ ጣቢያ ኢህአዴግ፣ የትግስቱ አንድነት፣ ቅንጅትን ጨምሮ ሌሎች ስድስት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ያለ ምንም ዕጣ አልፈዋል የተባለ ሲሆን ‹‹የሚያልፉት በዕጣ ነው›› የተባሉት ሰማያዊን ጨምሮ 11 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መካከል ሰማያዊና ሌሎች አራት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ‹‹ዕጣ አልወጣላቸውም፡፡›› ተብሏል፡፡ ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ሰማያዊ ህዝብ ውስጥ በሰፊው እየገባና እያንቀሳቀሰ ያለ ግንባር ቀደም ፓርቲ ነው፡፡ እንደ ኢህአዴግ ያሉን ጨምሮ ዕጣ ውስጥ አይገቡም፡፡ ሰማያዊ ደግሞ ይህ ነው የሚባል እንቅስቃሴ ከማያደርጉት ፓርቲዎች ጋር ዕጣ ውስጥ ገብቶ ወደቀ መባሉ ዴሞክራሲ ከጅምሩ ጀምሮ የህዝብ ድምጽ ሆኖ እያለ በእኛ አገር ሎተሪ ሆኗል ማለት ነው፡፡›› ብለዋል ሊቀመንበሩ አክለውም ‹‹ሂደቱ ምንም ይሁን ምን አንድን ፓርቲ ወይንም ተወካይን ህዝብ ነው መምረጥ ያለበት፡፡ ህዝብ የሚፈልገውና የሚመረጥ ፓርቲ ነው ለምርጫ መቅረብ ያለበት፡፡ አሁን ግን እየተባለ ያለው በአንድ በኩል ህዝብ የማይፈልገው ያለ ዕጣ […]

Highlights: * “አንድ ቋንቋ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ሕዝብ የሚሉ ሁሉ ህወሓትን ይጠሉታል።” * “ከአሜሪካንና ከእሥራኤል ጋር ያጣላን ፕሮግራማችን ነው።” * “ተወልደ የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር፤ ስዬም የመከላከያ ሚኒስትር እያሉ ኤርትራ ነፃነቷን ስታገኝ የአሰብ ጉዳይ ያለቀለት ጉዳይ ነው። ወንበር ፍለጋ ነው እንጂ የኤርትራ ጉዳይ ሰበብ ሊሆን አይችልም።” * “ህወሓት…… ለስድስት ወር ያህል ዝብርቅርቅ ያለ ፕሮግራም ተቀምጦ ነበር። ኢትዮጵያዊነትም አለ። ትግራይነትም አለ። ይሄ ጉዳይ በስድስት ወር ውስጥ እንዲጠራ ተደረገ።” (ጌትነት ምህረቴ) የመምህርነት ሙያቸውን ትተው ነበር በ1967 ዓ.ም ወደ ትግል የተቀላቀሉት። ከህወሓት ነባር ታጋዮች መካከል አንዱ ናቸው፤ አቦይ ስብሃት ነጋ። ህወሓት የተመሠረተበትን 40ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ዝግጅት ክፍላችን በህወሓት አመሠራረት፣ ዓላማና የትግል አግባብ ዙሪያ ከአቦይ ስብሃት ነጋ ጋር ያደረግነውን ቃለ- ምልልስ የመጀመሪያ ክፍል ይዘን ቀርበናል። አዲስ ዘመን፡- የንጉሡ ሥርዓት ተገርስሶ ወታደራዊ ሥርዓት ሲመጣ የነበረው የፖለቲካ አሰላለፍ ምን ይመስላል? አቦይ ስብሃት፡- የአፄ ኃይለሥላሴን መንግሥት የጣለው ሕዝቡ ነው። የጣለው ደግሞ መውደቅ ስለነበረበት ነው። ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁኔታው የከፋ ነበር። በሌላው ሀገር ኢንዱስትሪው ማቆጥቆጥ ጀምሯል። የአፄው ሥርዓት በጣም ያከረረ ፊውዳል ስለነበር በሀገሪቷ ልማት የሚባል ነገር አልነበረም። ትምህርትም ቢሆን እንደ ጠበል የሚንጠባጠብ በጣም የተወሰነ እንጂ የሰፋ አልነበረም። ሕክምናም እንደዚሁ። ሀገሪቷ ለማንኛውም አደጋ የተጋለጠች ነበረች። ሕዝቡ በረሃብ እየሞተ «ኢትዮጵያ የአፍሪካ የዳቦ ቅርጫት ናት» ይባል ነበር። ሕዝቡ ኑሮው አስከፊ ሆኖ ሳለ በወቅቱ የሚነገረው ግን ኢትዮጵያ ሀገራችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ያደገች ናት […]

(ምህረት ሞገስ) በመጪው ግንቦት 2007 ዓ.ም በሚካሄደው አምስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ በአዲስ አበባ ብቻ 25 የፖለቲካ ፓርቲዎች 328 ዕጩ ተወዳዳሪዎችን አስመዝግበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ)፣ መላው ኢትዮጵያ ብሔራዊ ንቅናቄ (መኢብን) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፣ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ)፣ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት)፣ የኢትዮጵያ አዲስ ትውልድ ፓርቲ (አትፓ) እና ሰማያዊ ፓርቲ ለአዲስ አበባ የምርጫ ክልል ለተዘጋጁ 23 ወንበሮች እያንዳንዳቸው 23 ዕጩዎችን አቅርበዋል፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ ደግሞ በአገር አቀፍ ደረጃ ሃምሳ ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከስድስት ሺ በላይ ዕጩዎችን አስመዝግበዋል፡፡ ይሀ ሁኔታ ካለፉት ምርጫዎች አንጻር ሲታይ እንግዳ ነገር ነው። በተሻሻለው የምርጫ ህግ መሰረት በአንድ የምርጫ ክልል ውስጥ መወዳደር የሚችሉት ዕጩዎች ቁጥር 12 ብቻ ናቸው። በተጨባጭ ግን በአሁኑ ወቅት በአንድ የምርጫ ክልል እስከ 19 የሚደርሱ ዕጩዎች መመዝገባቸውን የምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ይህ እውነታ ከምርጫ ህጉ አንጻር እንዴት ይታያል? መፍትሄውስ ምን ይሆን? የተመዘገቡት ሁሉ በምርጫው ይወዳደራሉ? ወይንስ ሌላ አማራጭ ይኖራል? በማለት በምርጫ ቦርድ የአገልግሎቶችና ግንኙነት ዘርፍ ምክትል ዋና ኃላፊ አቶ ወንድሙ ጎላን አነጋግረን ቀጣዩን መረጃ ይዘን ቀርበናል፡፡ አዲስ ዘመን፡- ዘንድሮ በሚካሄደው በአምስተኛው አገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩ ምዝገባ ላይ የተለየ ነገር መከሰቱ ተሰምቷል። ጉዳዩን ቢያስረዱኝ? አቶ ወንድሙ፡- በዘንድሮው ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩ ማስመዝገብ ላይ የተከሰተውና ለየት ያለው ነግር በምርጫ ክልሎች ዘንድ የዕጩዎች ቁጥር መብዛቱ ነው፡፡ በ1999 ተሻሽሎ በወጣው የምርጫ ሕግ […]

(አዲስ – ከድሬዳዋ) ድሮ ድሮ የአዲስአበባ ዙሪያ ገበሬዎች ራሳቸው መሬታቸውን እየሸጡ ነበር ከተማ የሚስፋፋው፡፡ ከ15 አመት ወዲህ ደግሞ መንግስት ካሳ እየከፈለ መሬታቸውን በሊዝ ለባለሀብት(ቤተሰሪ) ይሰጥ ነበር፡፡ በመጀመሪያዎቹ አመታት ታዲያ ለመሬቱ የሚከፈለው ክፍያ እዚህ ግባ የማይባል ስለነበር የብዙዎችን ህይወት ያበላሸ ነበር፡፡ በ1990ዎቹ አጋማሽ ካዛንቺስ ቶታል አካባቢ እዚህ ግበ የማይባል ካሳ ተሰትቶት የንግድ ተቋሙን የተነጠቀ ሰው ራሱን እንዳጠፋ መስማቴን አስታውሳለሁ፡፡ ቆይቶ የካሳው መጠንም በሽያጭ የሚገኘውን ያህል ባይሆንም መመሪያ ተዘጋጅቶለት የተሸለ መልክ እየያዘ እንደነበርም አስታውሳለሁ፡፡ እንዲያውም ለልማት የሚፈለግ ቦታ ላይ ተነሺ ሰዎች አስቀድሞ ከ2 አመት በፊት ሁሉ እየተነገራቸው ቅድመ ዝግጅት ያደርጉ እንደነበረና በዚህ መሀል የመሬት ካሳ የተቀበሉ ገበሬዎች መሬቱን በርካሽ ዋጋ አትርፎ መሸጥ ለሚፈልግ የከተማ ስግብግብ ሁለተኛ ዙር ሸጠውለት በፋራ ሙድ ጉድ እንዳደረጉት ሁሉ ሰምቻለሁ፡፡ አሁን ባለፈው አመት የአዲስአበባና አጎራባች የኦሮሚያ ወረዳዎች የተቀናጀ እቅድ ሲወጣ የኦሮሚያ ወረዳዎችን ወደአዲስአበባ የሚጠቀልል ነው በሚል ተቃውሞ ሲሰማ ነበር፡፡ መንግስት ደግሞ አዲስአበባና አጎራባች ወረዳዎች በመሰረተልማት፣ በተፋሰስ፣ እና በፕላን የተቀናጁ እንዲሆኑ እንጂ አንዱ ሌላውን እንዲውጥ የታሰበ ነገር የለም ነው የሚለው፡፡ በርግጥም ይህንን የሚያስተባብል ማስረጃ እስከዛሬ አላጋጠመኝም ፡፡ ማንም ተራ ሰው መገመት እንደሚችለው የአዲስአበባ ፕላን ላይ የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ቢኖር የዚያ አጎራባች የሆነ የኦሮሚያ ወረዳ በፕላኑ እዚያ አካባቢ የመኖሪያ ሰፈር ሳይሆን የቆሻሻ ማስወገጃ ቢያቅድ ተጠቃሚ ይሆናል፤ ይህ ሊሆን የሚችለው ደግሞ አጎራባች ወረዳዎቹ ከአዲስአበባ ጋር የተናበበ እቅድ ካላቸው ብቻ ነው፡፡ በግሌ […]

በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስር የምትታተመዋ ዘመን መፅሄት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ የኑስን እንግዳ አድርጋ ዘርዘር ያሉ መረጃዎችን ይዛ ወጥታለች። ከእነዚህ ነባርና አንጋፋ ታጋዮች መካከልም ጄኔራል ሳሞራ ለመጽሄትዋ ከሰጡት መረጃ የተወሰኑትን በመምረጥ እንዲህ አቅርበነዋል። ዘመን፡- እናመሰግናለን ጄኔራል ሳሞራ እንደሚታወቀው የህወሀት 40ኛ ዓመት መከበር ጀምሯል። እርስዎ ደግሞ በትግሉ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነዎትና እንደ ግለሰብ ትግሉን እንዴት ያስታውሱታል፤ ዛሬ ላይ ሆነው ሲያስቡት? ጀኔራል ሳሞራ፡- አርባ ዓመት ረጅም ጊዜ ነው። የትግሉ ሂደትም አንድ ዓይነት አልነበረም። የመጀመሪያዎቹ አስራ ሰባት ዓመታት ጨቋኙን ፋሽስት የደርግ ስርዓት ለማስወገድ የተደረገ የትግል ጊዜ ነበር። ይሔ ትግል ደግሞ በርካታ መስዋዕትነት የተከፈለበት ነው። ብዙ ወጣት ኢትዮጵያውያን የተሰዉበት የትግል ሂደት ነው። ደርግ ከተሸነፈ በኋላ ደግሞ የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ትግሉ ነው የቀጠለው። እንዳልኩት የመጀመሪያው አስራ ሰባት ዓመት የትግል ዓላማ ጨቋኙን ሥርዓት የማስወገድ ቢሆንም የመጨረሻው ዓላማ ግን ዴሞክራሲን፣ ልማትንና ፍትህን ማረጋገጥ ነበር። እና ትግሉ የመላው ኢትዮጵያ ህዝቦችን ድጋፍ አግኝቶ በተሳካ ሁኔታ ነው የተጠናቀቀው። በትግሉ ውስጥ ትልቁና ወሳኙ ነገር የደርግን ኃይል መደምሰስ ቢሆንም ከዚያ በመቀጠል ለግጭት፣ ለድህነትና ለሰላም እጦት ይዳርገን የነበረው ሁኔታ በ1987 ዓ.ም በፀደቀው ህገ መንግሥታችን መፍትሔ አግኝቷል። በዚህም ያ የተደመሰሰው ሥርዓት ዳግመኛ እንደማይመለስ እርግጠኛ የተሆነበት ሁኔታ ነበር የነበረው፡፡ ለአሁኑ ልማትና ዴሞክራሲያችን መሰረት የሆነውም ይሄው ህገ መንግስታችን ነውና በትግሉ የደርግ ሥርዓትን መደምሰስ አንዱ ጉዳይ ሆኖ ሁለተኛው ደግሞ ህገ መንግስቱ መጽደቁ ነው፡፡ ከዚህ […]

የተከበሩ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ በጥርስ ህክምናው ዘርፍ የተሠማሩ ባለሀብት ሲሆኑ በ2002 ምርጫ ተወዳድረው በማሸነፍ በፓርላማ ብቸኛ የግል እጩ ሆነዋል፡፡ ዶ/ር አሸብር በፓን አፍሪካ ፓርላማ ውስጥ በም/ፕሬዚዳንትነት እያገለገሉም ይገኛሉ፡፡ በግንቦቱ ምርጫ ዙሪያ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር የሚከተለውን ቆይታ አድርገዋል፡፡ አዲስ አድማስ:- በግንቦቱ ምርጫ በእጩነት ይወዳደራሉ? ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ:- በምርጫው ለመወዳደር ጓደኞቼ ፊርማ አሰባስበውልኝ ለቦርዱ አስገብተናል፡፡ ሙሉ ለሙሉ ተወዳዳሪነቴን የማረጋግጠው የእጩነት ደብተሬን ስወስድ ነው፡፡ ከእኔ የሚጠበቀውን ሁሉ አድርጌያለሁ፡፡ አዲስ አድማስ:- የት ነው የሚወዳደሩት? ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ:- በከፋ ዞን፣ ቦንጋ ዲንቦ ጓታ ምርጫ ጣቢያ ነው የምወዳደረው፡፡ አዲስ አድማስ:- የግል ተወዳዳሪ የመሆን ጥቅሞችና ፈተናዎች ምንድን ናቸው? ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ:- አብዛኛው ጊዜ ፓርቲዎች ሚዲያ ተጠቅመው ራሳቸውን የማስተዋወቅ እድል አላቸው። ቴሌቪዥን፣ ራዲዮ ይጠቀማሉ፤ ለምርጫው ከመንግስት በጀት ያገኛሉ፡፡ ለግል ተወዳዳሪዎች ግን እነዚህ ሁሉ የሉም፡፡ እኛ የግል ተወዳዳሪዎች በራሳችን ወጪ መቀስቀስ፣ በራሳችን የቅስቀሳ አውታር መጠቀም ስለሚጠበቅብን ብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያለነው፡፡ አንድ ግለሰብ ለመወዳደር ሲፈልግ፣ በዚህ ደረጃ ራሱን ማዘጋጀት አለበት፡፡ አዲስ አድማስ:- ጥቅሞቹስ? ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ:- ራሱ ኢህአዴግን ብትወስድ አባላቱ ከ10 ሚሊዮን አይበልጡም፡፡ ከህዝቡ 70 እና 80 በመቶው የፓርቲ አባል አይደለም ማለት ነው። ስለዚህ ህዝቡ እኛን በቀላሉ መረዳት ይችላል፡፡ ከየትኛውም ፓርቲ ገለልተኛ መሆን ለአስተያየትም ለፍርድም ይጠቅማል፡፡ ብዙ ሰው ወደ ፓርቲ አይጠጋም፤ለዚህም ምክንያቱ ገለልተኛ መሆን ስለሚፈልግ ነው፡፡ የግል ተወዳዳሪ መሆን ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ ግለሰቡ ራሱ በራሱ ነው ወሳኝ የሚሆነው፡፡ […]

* የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ለሻዕቢያ አሉታዊ የሆነ አቋም ያለማቋረጥ ይይዙና ይወተውቱ ነበር * የህወሓት/ኢህአዴግ ሠራዊት አዲስ አበባ ሲገባ አብሮ የመጣው የሻዕቢያ ተዋጊ ብዛት 300 ገደማ ነበር በሕወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) የትግል ታሪክ እንደ ወሳኝ ምዕራፍ ተደርጎ የሚወሰደው የ1981ዱ የሽረ ጦርነት ከመካሄዱ ጥቂት ወራት በፊት ሻዕቢያ በትጥቅ ትግሉ ስኬት ላይ ተስፋ አጥቶ እንደነበር ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ገለጹ፡፡ በሽረ አካባቢ የነበረውን የቀድሞ ሠራዊት 604ኛ ኮር በጋራ የመምታት ሀሳብ ከህወሓት በቀረበ ግዜ፤ ከሻዕቢያ የተሰጠው ምላሽ ‹‹12 ክፍለሀገር ለ2ክፍለሀገር ሞቢላይዝ እያደረገ መቼ ድል እንምናደር አናውቅም – በረጅም ተነል ውስጥ የድል ጭላንጭል አይታየንም›› የሚል እንደነበር አውስተዋል፡፡ ጄኔራሉ ይህንን የተናገሩት ባለፈው ሳምንት ባደረግንላቸው ቃለ-መጠይቅ በሕወሓት እና በተለምዶ ሻዕቢያ ተብሎ በሚጠራው (ያኔ ሕዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ (ሕግሓኤ) አሁን ሕዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲ ለፍትሕ) በሚባለው የኤርትራው ገዢ ፓርቲ መሀል ስለነበረው ግንኙነት በሰጡት ምላሽ ላይ ነው፡፡ ከሻዕቢያ ጋር የነበረው ግንኙነት ሚዛኑን የሳተ ነው የሚለውን ክስ የማይጋሩት ጄኔራል ጻድቃን፤ ህወሓት ከአልጀሪያ እስከ ቬትናም፣ ከኩባ እስከ ቻይና ከነበሩ የትጥቅ ትግል ታሪኮች ልምድ ለመውሰድ ይሞክር የነበረ ከመሆኑ አንጻር ከጎረቤቶቹ ከሻዕቢያና ጀብሀ ልምድ መውሰዱ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡ ስለግንኙነቱ እንደማሳያ ሁለት ክስተቶች እንዲጠቀሱ ተጠይቀው ሲመልሱ፡- በ1973 ገሩ ስርናይ፣ በማርዲ፣ ኡናሽሀቅ፣ ወዘተ በሚባሉት የድንበር አካባቢዎች (ዛሬ አህፈሮም ወረዳ) ለገበሬው መሬት የማከፋፈል ጉዳይ አወዛግቦ የነበረበትን ታሪክ አስታውሰዋል፡፡ በወቅቱ ጻድቃን በማዕከላዊ ኮሚቴ ተመድበው በአካባቢው ያስተባብሩ የነበረ […]

ከ1971 ጀምሮ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት የህወሓት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ‹‹እኔ የማውቀው ከደርግ ከሚገኘው ንብረት አብዛኛውን ከሕዝብ ስንካፈል እንጂ ከውጭ ለእርዳታ የመጣውን ገንዘብ ከሕዝብ ቀምተን ለጦር መሣሪያ ስናውል አይደለም›› አሉ፡፡ ጄኔራሉ ይህን ያሉት ባለፈው ሰኞ ጥር 30-2007 ባደረግንላቸው ቃለ-መጠይቅ ላይ፡- ለ1977ቱ ረሀብ የመጣው ዕርዳታ ለድርጅት ሥራ እንዲውል ተደርጓል ስለሚለው የዶ/ር አረጋዊ በርኸ ስሞታ ላቀረብንላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ነው፡፡ ዶ/ር አረጋዊ ከቀደምት የህወሓት አመራሮች አንዱ ሲሆኑ የማርክሳዊ ሌኒናዊ ሊግ ትግራይ(ማሌሊት) ምሥረታን ተከትሎ ከድርጅቱ ለቅቀው በአውሮፓ የሚኖሩ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ዶ/ር አረጋዊ ለዕርዳታ ከመጣው ገንዘብ 50 በመቶ ለማሌሊት ማጠናከሪያ፣ 45 በመቶ ለወታደራዊ ወጪ ተመድቦ 5 በመቶ ብቻ ለሕዝብ እንዲውል በማዕከላዊ ኮሚቴ ተወስኖ ተግባራዊ ተደርጓል የሚሉ ሲሆን፤ በወቅቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ ግን የዛሬ 5 ዓመት በአሜሪካ ራዲዮ አማርኛ ፕሮግራም ላይ በሰጡት አስተያየት እንደዚያ ዓይነት ውሳኔ አልተወሰነም በማለት መቃወማቸው ይታወሳል፡፡ በሌላ በኩል በቅርቡ ሌላው የቀድሞ የድርጅቱ አመራር ገብሩ አሥራት በቅርቡ ባሳተሙት መጽሐፍ፡- በወቅቱ ድርጅታዊ ድጋፍ የሚያደርጉ መንግስታት የሚጠቀሙት መሥመር ያንኑ የሰብዐዊ ዕርዳታ የሚመጣበትን መሥመር በመሆኑ እና ሁሉም ገንዘብ አንድ ቋት ውስጥ የሚገባ በመሆኑ ስሞታው የወቅቱን አሠራር ካለመገንዘብ የሚመጣ ነው የሚል አጭር አስተያየት አስፍረዋል፡፡ እነዚህን አስተያየቶች በመጥቀስ ጥያቄ ያቀረብንላቸው በወቅቱ የማለሌሊት/ህወሓት ፖሊት ቢሮ አባል እና የሠራዊቱም ቺፍ ኦፍ ስታፍ የነበሩት ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ስሞታውን አጣጥለውታል፡፡ በወቅቱ በተለይ በረሀቡ […]

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በትግል 10 ዓመታ ካስቆጠረ በኋላ፤ በ1977ዎቹ የፖለቲካ አመራር የሚሰጥ አደረጃጀት ማርክሳዊ ሌኒናዊ ሊግ ትግራይ(ማሌሊት) በሚል ስያሜ እንደመሠረተ ይታወሳል፡፡ ያ አደረጃጀት ዓለም-አቀፋዊውን የአሰላለፍ ለውጥ ተከትሎ ከ1983 በኋላ እንዲቀር መደረጉ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በአብዛኛው ሕዝብ እምብዛም አይታወቅም፡፡ ይሁን እንጂ ህወሓት ከ1970ዎቹ አጋማሽ በኋላ ላሳየው የወታደራዊ እና ድርጅታዊ እመርታ ምክንያቱ የማሌሊት ምሥረታ ያስከተለው የርዕዮተ-ዓለም ጥራት ነው ብሎ ያምናል፡፡ በአንጻሩ የቀድሞው የድርጅቱ አመራር ገብሩ አሥራት በቅርቡ ባሳተሙት መጽሐፍ፡- በወቅቱ የተገኙት ለውጦች ያለማሌሊት ሊከሰቱ የሚችሉ የአደረጃጀት ለውጥ ውጤቶች ናቸው የሚል ሀሳብ አንስተዋል፡፡ ባለፈው ሰኞ ጥር 30-2007 ቃለ-መጠይቅ ያደረግንላቸው ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሰኤ ካቀረብነው ጥያቄዎች አንዱ ማሌሊትን የተመለከተ ነበር፡፡ ከ1971 ጀምሮ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት እና ማሌሊት ሲቋቋም ከመጀመሪያዎቹ 9 የፖሊት ቢሮ አባላት አንዱ የነበሩት እንዲሁም የህወሓት ሠራዊት ቺፍ ኦፍ ስታፍ የነበሩት ጻድቃን፤ * የማሌሊት ምሥረታን እና በሕወሓት መዋቅር ላይ የነበረውን ፋይዳ ያብራሩ ሲሆን አያይዘውም * የህወሓትን ወታደራዊ ስትራቴጂ ጽንሰ-ሀሳቦች፣ * ከደርግ 603ኛ ኮር ጋር በሽረ የተደረገውን ውጊያና ተዛማጅ ታሪካዊ ሁነቶችን እንደሚከተለው አብራርተዋል፡፡ [እስከ 1993 የሀገር መከላከያ ሠራዊት ኤታማጆር ሹም የነበሩት ሌፍተናንት ጄኔራል ጻድቃን፤ የህወሓት-ሻዕቢያ ግንኙነት፣ የ1977ቱ ረሀብ፣ በኤርትራ ወረራ ወቅት የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ሚና፣ የቀድሞው ሠራዊት መበተን እና ሌሎች ዐብይ ርዕሰ-ጉዳዮች እንዲሁም ስለራሳቸው ለቀረቡ ጥያቄዎች የሰጡትን ምላሾች በተከታታይ እናቀርባለን] —— Watch Video below.   ************* More from Horn Affairs AmharicVideo […]

(አዲስ ከድሬዳዋ) የቀድሞ ዩጎዝላቪያ አካል የነበሩት ክሮሺያና ሰርቢያ (የቦስኒያ ሙስሊሞችን እና ሞንቴኔግሮዎችን ጨምሮ) ሶሻሊዝም ሲንኮታኮት ከተበታተኑት የዩጎዝላቪያ ሪፑብሊኮችና ራስገዝ አስተዳደሮች መካከል ናቸው፡፡ እነኚህን ሪፑብሊኮች ቀድሞዉኑ ምን አንድ አደረጋቸው፣ በኋላስ ለምን መለያየት ፈለጉ የሚለው ትንሽ ግራ ያልተለመደ የሚመስል ነገር አለው፡፡ ከዩጎዝላቭ ሪፑብሊኮች በህዝብ ብዛትና ተፅዕኖ የመፍጠር አቅም ቀዳሚ የነበሩት ሰርቦች እና ክሮአቶች ቋንቋቸው የዲያሌክትን(ቀበሌኛን) ያህል እንኳ የማይለያይ ተመሳሳይ ነው፡፡የቋንቋ ምሁራንም ለየብቻ ማስቀመጥ ከብዷቸው ሰርቦክሮአት ይሉት ነበር ቋንቋውን(አሁን ለየብቻ ነው ብዙ ቦታ ላይ የሚፃፈው)፡፡ ዘራቸውም እንደስማቸው ሁለቱም ዩጎ ስላቮች(የደቡብ ስላቮች) ናቸው፡፡ ታሪካቸውን ያየን እንደሆነም ብዙ ነገሮችን ይጋራሉ፡፡ ኢኮኖሚያቸውን ያየን እንደሆነም ከአውሮፓ ድሀ እና በአንፃራዊነት ኋላቀር ከሚባሉ ህዝቦች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ታዲያ በምንድን ነው የሚለያዩት – በሐይማኖት- አለቀ፡፡ በሀይማኖት ብቻ፡፡ ሰርቦች ኦርቶዶክስ ናቸው፣ ክሮአቶች ደግሞ ካቶሊኮች ናቸው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሰርቦች የኦሮቶዶክሱ ቅዱስ በፈጠረው ሲርሊክ ፊደል ይፅፋሉ፣ ካቶሊኮቹ ክሮአቶች ደግሞ ሮማዊ በሆነው ላቲን ፊደል ይፅፋሉ፡፡ እነዚህ ህዝቦች የደቡብ ስላቭ አንድነት አቀንቃኝ በነበረው ቲቶ አንድ ሆነው ሲኖሩ ቆይተው(አንድነቱ ግን ወደህዝቡ ያልሰረጸ እና በቲቶ ተሰሚነት ላይ የተመሰረተ ስለነበረ) ማርሻል ቲቶ ሲሞት አንደኛው ህዝብ ከሌላኛው ብሔር በወጣ መሪ ለመተዳደር ዝግጁ ስላልነበር ዩጎዝላቪያ በእቁብ መመራት ጀመረች፤ ዘንድሮ ከሰርቢያ፣ ቀጥሎ ከሞንቴኔግሮ፣ ከዚያ ከክሮሺያ፣ ከዚያ ከሜቄዶኒያ፣ ከዛ ከስሎቬኒያ፣ . . .እያሉ በየአመቱ በፈረቃ ዩጎዝላቪያን ሲያስተዳድሩ ቆዩ፡፡ ያው አስተዳደራቸው ራሱ ምንያህል አንድነት እንደሌላቸው የሚያሳይ ነውና ጊዜው ሲደርስ ሁሉም ሪፑብሊኮችና ራስገዝ […]

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ በተመለከተ መግቢያ በቦርዱ ዕዉቅና ያገኘዉና በስራ ላይ ያለዉ የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ የ2001 ዓ.ም ስለመሆኑ፣ ደንቡ የፓርቲዉ አመራሮችም ሆነ አባላት መብትና ግዴታቸዉን አዉቀዉ በእንቅስቀሴዉ ዉስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል እንደሆነ፣ በአመራሩ/በበታች አካሎችና አባሎች መካከል ዴሞክራሲያዊ የሆነ መከባበር ላይ የተመሰረተ አሰራር ለመፍጠር እንደሆነ በግልጽ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ መኢአድ በአሁኑ ጊዜ በሁለት ቡድን በመከፈሉ የፓርቲዉ የስራ እንቅስቃሴ ተገቷል በሚባል ደረጃ ያለ ስለመሆኑ እንረዳለን፡፡ አሁን ተመርጠናል በሚሉት በእነ አቶ ማሙሸት አማረ ቡድን የተፈጸሙ የህግ ጥሰቶችን እንደሚከተለዉ ማንሳት ይቻላል፡፡ 1ኛ. የፓርቲዉ ፕሬዚደንትን ከጠቅላላ ጉባኤ አባላት መካከል መመረጥ እንዳለበት፣ የፓርቲዉ ተ/ምክትል ፕሬዚደንት ደግሞ የጠቅላላ ጉባኤ አባል መካከል ከመሆኑ ባሻገር የማዕከላዊ ምክር ቤት አባል መሆን እንዳለበት የፓርቲዉ ደንብ በአንቀጽ 7.4 እና 4.2.2 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ይሁንና አሁን የተመረጡት ግለሰቦች በ2003 ዓ.ም ከፓርቲዉ አባልነት የተሰረዙ ከመሆኑም በላይ ለሶስት ተከታታይ ወራት የአባልነት መዋጮ ያልከፈለ አባልነቱ ቀሪ እንደሚሆን ስለሚደነግግ ለዚህ ኃላፊነት መስፈርቱን የማያሟሉ ሰዎች በመመረጣቸዉ የህግ ጥሰት ተፈጽሟል፡፡ 2ኛ. ፓርቲዉ አካሂጃለሁ የሚለዉን የጠቅላላ ጉባኤ ዉጤት ሪፖርት፣ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ጥቆማ ሲያደርግ እና ሌሎች የፓርቲዉን ወሳኝ ክንዉኖችን ሲያሳዉቅ በፓርቲዉ ማህተም የተረጋገጠ ሰነድ ማቅረብ እንዳለበት የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 አንቀጽ 20/1/ በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ ይሁንና ፓርቲዉ በዚህ አግባብ አረጋግጦ ሊያቀርብ አልቻለም፣ ይባስ ብሎ ህጋዊ ማህተም በሌሎች የፓርቲዉ ቡድን እጅ መኖሩ እየታወቀ ተመሳሳይ […]

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ /አንድነት/ በተመለከተ የፓርቲዉ የቦርድ ዕዉቅና ያለዉ መተዳደሪያ ደንብ የ2004 ዓ.ም ስለመሆኑ፣ ቦርዱ የrፓርቲዉን እንቅስቃሴ ከዚሁ የቦርዱ ዕዉቅና ካለዉ ደንብ አንጻር ሲመረምር እንደቆየና አሁንም ከዚያዉ አኳያ የመረመረ ስለመሆኑ ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል፡፡ ከፓርቲው ውስጠ ደንብ መግቢያ ስንነሳ፡- መግቢያ አንዱና ዋነኛዉ የህግ አዉጭዉን አካል ሃሳብ የምንረዳበት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከፓርቲዉ መተዳደሪያ ደንብ መግቢያ መረዳት እንደሚቻለዉ መተዳደሪያ ደንቡ የፓርቲዉ አመራሮችና አባላት የሚመሩበትና የሚገዙበት እንደሆነ፣ በፓርቲዉ አደረጃጀት መሰረት የተለያዩ አካላት ጤናማና ዴሞክራሰያዊ የሥራ ግንኙነት እንዲኖራቸዉ የሚያስችል፣ የስራና ኃላፊነት ክፍፍል የሚፈጥር እና ግልጸኝነትና የተጠያቂነት መርህ የሚፈጥር እንደሆነ በግልጽ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ይሄንን የህግ አዉጭዉን ሃሳብ ተከትሎ ስራዎች ሲተገበሩ አይታዩም፡፡ ደንብ የሚያወጣዉ የፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ነው፡፡ ሌላ አካል ቦርዱን ጨምሮ ማንም ሊያወጣላቸዉ አይችልም፣ አይገባምም፡፡ ነገር ግን ደንብ ከወጣ እና ለቦርዱ ቀርቦ ዕዉቅና ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ የፓርቲዉ አመራርም ሆነ አባላት ለደንቡ ተገዥ መሆን ይጠበቅባቸዋል፤ ቦርዱም በተሻሻለው የኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም. እና በተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2ዐዐዐ ዓ.ም. መሠረት ይሄንን ደንብ የማስከበር ኃላፊነት አለበት፡፡ አሁን ተመርጠናል በሚሉት በእነ አቶ በላይ ፈቃዱ ቡድን በኩል የተፈጸሙ ዋና ዋና የህግ ጥሰቶች የሚከተሉት ናቸዉ፡፡ 1ኛ. የፓርቲዉ ፕሬዝዴንት ጨምሮ ኃላፊዎች አመራረጥ በተመለከተ በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 572/2000 አንቀጽ 8/2/ረ/ እና በፓርቲዉ ደንብ አንቀጽ 13.3.1 መሰረት በጠቅላላ ጉባኤ መመረጥ […]

(ሠመረ ሞገስ) የብሄራዊ ስታዲየም ፕሮጀክት ዝርዝር የዲዛይን ስራዎች በመጪው የካቲት ወር አጋማሽ እንደሚጠናቀቅ የፕሮጀክቱ አማካሪ አስታወቀ፡፡ በስታዲየሙ ዙሪያ የሚታጠረው የአጥር ግንባታ 91 በመቶ ደርሷል። በአዲስ አበባ ቦሌ ገርጂ አካባቢ በመገንባት ላይ ያለው ብሄራዊ ስታዲም 60 ሺህ ተመልካች የመያዝ አቅም ሲኖረው ለግንባታው 2 ቢሊዮን ብር ወጪ ተይዞለታል። የስታዲየሙ ግንባታ በሁለት ዓመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። የፕሮጀክቱ አማካሪ ሜ.ኤች ኢንጂነሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዶክተር ኢንጂነር መሰለ ኃይሌ እንደተናገሩት ”የቅድመ ዲዛይን ስራዎች ተጠናቆ የዝርዝር ዲዛይን ስራዎች በመሰራት ላይ ናቸው”:: ዝርዝር ዲዛይኑ የኤሌክትሪክ ዝርጋታ፣ የሜዳ ስፋት፣ የመሬት ጥናት፣ በጦር ውርወራ ጊዜ ርቀቶችን መለካት የሚያስችሉ ዘመናዊ መሳሪያዎችና የሽብር ጥቃት ለመከላከል የሚያስችሉ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችና ሌሎች ዲዛይኖች ያካተተ ነው። የመጨረሻ ዝርዝር ዲዛይን ስራ በመጪው የካቲት ወር እንደሚጠናቀቅ ነው ዶክተር ኢንጀነር መሰለ የተናገሩት። ስለሆነም ግንባታውን ለማስጀመር በመጪው መጋቢት ወር ጨረታ ይወጣል። 60 ሄክታር ላይ የሚያርፈው አዲሱ ብሄራዊ ስታዲየም የመሬት ጥናቱ በመጠናቀቅ ላይ ነው፡፡ እንደ ኢንጂነሩ ገለጻ ስታዲየሙ ዓለም አቀፍ ደረጃን ጠብቆ የዓለም ዋንጫና የኦሎምፒክ መክፈቻና መዝጊያ ውድድሮችን እንዲያስተናግድና የተጀመሩ ዝርዝር ዲዛይን ስራዎች ጥራታቸውን ተጠብቆ እንዲሰሩ ለማድረግ ከኮሪያ፣ ከአውስትራሊያ እና ከእንግሊዝ አገር አማካሪዎችን አካትቷል፡፡ ድርጅቱ የመጨረሻ ዝርዝር ዲዛይን እየሰራ ያለው ከፌዴራል ስፖርት ኮሚሽንና ከከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስተያየት ከተሰጠው በኋላ ነው። በፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን የግንባታዎች ፋሲሊቲ የስራ ሂደት ዳይሬክተር አቶ ጥበበ ጎርፉ በበኩላቸው እንደተናገሩት በስታዲየሙ ዙሪያ […]

(ሔኖክ ሰለሞን) በእነ አቶ በላይ የሚመራው የአንድነት ፓርቲ ቡድን በህገ ወጥ መንገድ ሊያካሂድ የነበረው ሰልፍ መበተኑን የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ጉዮች ቢሮ አስታወቀ አዲስ አበባ፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) በእነ አቶ በላይ ፈቃዱ የሚመራው አንድነት ለዴሞክራሲና  ለፍትህና ፓርቲ ዛሬ በህገ ወጥ መንገድ ሊያካሂድ የነበረው ሰልፍ መበተኑን የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ጉየዮች ቢሮ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታወቀ ፓርቲው ለሰልፉ ከከተማ መስተዳደሩ በህጋዊ መልኩ ፈቃድ ሳያገኝ ነው፣ ሰልፉን ቀበና አከባቢ በሚገኘው ቢሮው ለማድረግ መሞከሩን ነው ቢሮው የገለፀው። ፖሊስ ህጉን በተከተለ መንገድ ሰልፉን ለማስቆም ቢሞክርም አንዳንድ የፓርቲው አበላት በፖሊስ ላይ  አምባጓሮ ለማስነሳት ሞክረው ነበር ብለዋል የቢሮው ሃላፊ ወይዘሮ ፍሬሀይወት አያሌው። ይሁንና ፖሊስ በትአግስት ሰልፉን ለመበተን መቻሉን ገልፀዋል። በሰልፉ ለመሳተፍ ከሞከሩት ውስጥ የታሰረ የፓርቲው አባል እንደሌለም አስታውቀዋል። የአስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ባሳለፍነው ሳምንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ቡድኑ ሰላማዊ ሰልፉን እንዳያካሂድ የተከለከለው ሰለማዊ ሰልፍ ሲካሄድ መሟላት ያለበትን አስፈላጊ ቅጽ ባለሟሟላቱ መሆኑ ተገልዖ ነበር። ቅፁ የሚጠይቃቸው በሰልፉ ላይ የሚያዙ መፈክሮችን እና ሰልፉ ከየት ተነስቶ የት እንደሚጠናቀቅ የሚገልፁ መረጃዎችን ጨምሮ ሌሎች መሟላት የሚገባቸውን የሰላማዊ ሰልፍ ማካሄጃ መስፈርቶችን አንዳላማላም በመግለጫው መጠቀሱ የሚታወስ ነው። ********* ምንጭ፡- ፋና፣ ጥር 17፣ 2007 — — More from Horn Affairs Amharic‘የእነበላይ ፍቃዱ አንድነት’ መግለጫ:- ‹‹የምርጫ ቦርድ ታሪካዊ ወንጀል እየፈፀመ ነው››መኢአድ – ቦርዱ የሰጠኝን የቤት ስራ የጨረስኩ በመሆኔ የምጠራው ጉባኤ የለምየነትዕግስቱ አወል የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ ተካሄደየአንድነት […]

በአቶ ትእግስቱ አወሉ የሚመራው የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤውን ባለፈው ቅዳሜ በቶፕ ቪው ሆቴል አካሂዷል። በጠቅላላ ጉባኤው 239 አባላት ተጠርተው 193ቱ ተገኝተዋል። ይህም ከግማሽ በላይ በመሆኑ ጠቅላላ ጉባኤ ማካሄዳቸውን በጉባኤው ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ ትዕግስቱ አወሉ ተናግረዋል። ሶስት የፓርቲው አባላት ማለትም አቶ ትዕግስቱ አወል፤ አቶ ጋሻው አሰፋና አቶ ደረጄ ሚሊዮን ለፓርቲው ፕሬዝዳንትነት በእጩነት ቀርበዋል፡፡ ከአዳማ የፓርቲውን ቅርንጫፍ በመወከል የተገኙት አቶ ጋሻው አሰፋ ከውድድሩ ራሳቸውን ያገለሉ ሲሆን ሁለቱ እጩዎች በሚስጥር በተካሄደ የድምፅ አሰጣጥ ተወዳድረዋል፡፡ አቶ ትዕግስቱ አወል ከተሰጠው ድምፅ 136 ሲያገኙ አቶ ደረጄ ሚሊዮን ደግሞ 48 ድምፅ በማግኘታቸው አቶ ትዕግስቱ ፓርቲውን በፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ ዳግመኛ ተመርጠዋል፡፡ ጠቅላላ ጉባዔው ለኦዲትና ኢንስፔክሽን የቀረቡለትን 10 እጩዎች አወዳድሮ 7 አባላትን መርጧል፡፡ በተመሳሳይ ለብሔራዊ ም/ቤት አባልነት 57 ዕጩዎች ቀርበውለት በ55ቱ ላይ ድምፅ ሰጥቷል፡፡ የጠቅላላ ጉባኤውን እና አጠቃለይ ውሳኔዎቹን ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እንደሚያቀርቡም አቶ ትዕግስቱ ተናግረዋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዚህ ጉባኤ ላይ ተወካዩን አልላከም፡፡ በሌላ ወገን ያለው የአቶ በላይ ፈቃዱ ቡድን ደግሞ ምንም አይነት ጠቅላላ ጉባኤ አላካሂድም በሚለው አቋሙ እንደፀና ነው። ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሁለቱ የፓርቲው አመራር ነን የሚሉ ቡድኖች ችግራቸውን በጠቅላላ ጉባኤ ፈተው እንዲመጡ የሰጠው ተጨማሪ የሁለት ሳምንት ጊዜ የፊታችን ማክሰኞ ይጠናቀቃል። ****** More from Horn Affairs Amharicመኢአድ – ቦርዱ የሰጠኝን የቤት ስራ የጨረስኩ በመሆኔ የምጠራው ጉባኤ የለምየነበላይ ፍቃዱ አንድነት ሊያካሂድ የነበረው ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ […]

በአንድነት ፓርቲ ውስጥ በተፈጠረው ውዝግብ ግንባር ቀደም ሚና ያላቸው አቶ አየለ ስሜነህ የአሰላለፍ ለውጥ አደረጉ፡፡ የእነትእግስቱ አወልን ቡድን በማደራጀት ቀዳሚ ሚና የነበራቸው አቶ አየለ፤ ሰልፋቸውን ቀይረው የነበላይ ፈቃዱን ቡድን መቀላቀላቸውን ትላንት የአንድነት ልሳን ለሆነው ለ‹‹ፍኖተ-ነፃነት›› በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል፡፡ አቶ አየለ የቅሬታቸው መነሻ የሆኑት ጉዳዮች ያልተመለሱ ቢሆንም ወቅቱ የምርጫ በመሆኑ እና ፓርቲውን ከአደጋ ለማዳን ሲሉ የአሰላለፍ ለውጥ እንዳደረጉ ገለጸዋል፡፡ ‹‹ፍኖተ-ነፃነት›› የለቀቀውን የአቶ አየለ ስሜነህ መግለጫ ቪዲዮ ከታች ይመልከቱ፡፡ *********** More from Horn Affairs AmharicAudio| የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አመራር በአዲሱ ማስተር ፕላን ላይ የሰጡት መግለጫበደቡብ ሱዳን ያሉ ኢትዮጵያዊያን መንግስታቸው እንዲታደጋቸው ይሻሉAudio | በኦሮሞ ተማሪዎች ስለተካሄዱት ተቃውሞዎች የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘገባVideo | ዳንኤል ብርሃነ እና ፋኑኤል ክንፉ የትግራይ ጉብኝትን አስመልክቶ በኢቢሲ የሚዲያ ዳሰሳ ፕሮግራም ላይኢ/ር ይልቃል:- የብሔር ብሔረሰብ መብት የሚባለው በጥራዝ ነጠቅ ያመጡት ነገር ነውምርጫ 97 ነፃ ነበር ከአሁኑ ይሻላል የሚለው ተቀባይነት የለውም – ፕ/ር መርጋ በቃና

የብረታ ብረት ማቅለጫን ጨምሮ 15  የማምረቻ ፋብሪካዎችን በተለያዩ አካባቢዎች ለማስገንባት ዝግጅት ማጠናቀቁን የትግራይ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ   አስታወቀ። ለግንባታው 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ካፒታል መድቧል። የኢትዮጵያ ብረት ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በበኩሉ የተለያዩ ክብደት ያላቸው ብረት ብረት ማቅለጥ የሚችሉ ስድስት ፋብሪካዎችን በ6 ወራት ውስጥ ገንብቶ ለማስረከብ ከክልሉ ጋር መስማማቱን አስታውቋል። በክልሉ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሓላፊ አቶ ጥላሁን ታረቀኝ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳሉት የክልሉን የተፈጥሮ ሃብት ነባራዊ ሁኔታ መሰረት በማድረግ  የማምረቻ ፋብሪካዎቹ  በዘንድሮ ዓመት ይገነባሉ። ”ፋብሪካዎቹ የግብርናውን ምርት ለማቀነባበር የሚያስችሉና ለኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ መደላድል የሚፈጥሩ ናቸው”ብለዋል። የክልሉ የተፈጥሮ ሃብት መሰረት በማድረግ ትልልቅ አራት የማምረቻ ፋብሪካዎች በአላማጣ፣ መቀሌ፣አድዋና ሁመራ ይገነባሉ ሲሉም ተናግረዋል። ባለፈው በጀት ዓመትም ክልሉ በ223 ሚልዮን ብር ወጪ በማምረቻ ኢንዱስትሪ ፣ፋብሪካዎች የፕሮዳክሽን ስራዎች ሊያሰሩ የሚችሉ ማሽኖች ያቀፉ አምስት የማምረቻ ፋብሪካዎች መገንባት መቻሉንም አስታውሰዋል። ከአምስቱ የማምረቻ ፋብሪካዎች በተገኘ ተጨባጭ ልምድና  በተፈጠረ ፍላጎት መነሻነት ከክልሉ በተገኘ የገንዘብ ምንጭ እነዚህ ትልልቅ የማምረቻ ፋብሪካዎችን ለመገንባት ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን አስታውቀዋል። ከግንባታ እስከ አጠቃላይ የቴክኖሎጂ ሽግግር ያሉት ስራዎች በዋናነት በኢትዮጵያ ብረት ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን  እንደሚከናውን የገለፁት አቶ ጥላሁን  የገንዘብ  አቅርቦቱን ታዛ በተባለው የክልሉ የካፒታል ዕቃ የፋይናንስ አክስዮን ማሕበር እንደሚሸፈን ገልጸዋል። የአክስዮን ማሕበሩ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ አማኑኤል ገብረ ትንሳኤ በበኩላቸው አገሪቱ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለማሰለፍ በክልሉ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ […]

(ጥላሁን ካሳ) በአቶ በላይ ፍቃዱ ቡድን የሚመራው የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ/አንድነት/ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የምጠራው ጠቅላላ ጉባኤ የለም አለ። ጠቅላላ ጉባኤ አካሂጄ የፓርቲውን መሪ መርጫለሁ ሌላው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የከፈተብኝ ዘመቻ ነው ሲልም ነው የገለፀው። ይህንንም የቦርዱን ዘመቻ ለመቃወም ለእሁድ ሰልፍ ጠርቻለው ብሏል። ሆኖም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሁለት የተከፈሉት እና በእነ አቶ በላይ ፈቃዱ የሚመራው የአንድነት ቡድን ከነገ በስቲያ እሁድ አካሂደዋለሁ ያለውን ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ እንደማይችል ነው ዛሬ የገለፀው ። የአስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ ቡድኑ ሰላማዊ ሰልፉን እንዳያካሂድ የተከለከለው ሰለማዊ ሰልፍ ሲካሄድ መሟላት ያለበትን አስፈላጊ ቅጽ ባለማሟላቱ ነው ብለዋል። እንደ ሀላፊው ቅፁ የሚጠይቃቸው በሰልፉ ላይ የሚያዙ መፈክሮችን እና ሰልፉ ከየት ተነስቶ የት እንደሚጠናቀቅ የሚገልፁ መረጃዎችን ጨምሮ ሌሎች መሟላት የሚገባቸውን የሰላማዊ ሰልፍ ማካሄጃ መስፈርቶችን አላሟላም። ከዚህ ቀደም መንግስት አስፈላጊውን የሰላማዊ ሰልፍ መመሪያዎች ተከትለው ለተንቀሳቀሱ ሰላማዊ ሰልፎችን የማካሄድ ፍቃድ መሰጠቱን የተናገሩት ሃላፊው፥ በእነ አቶ በላይ ፈቃዱ የሚመራው ቡድን የፊታችን እሁድ ለማካሄድ ያሰበው ሰላማዊ ሰልፍ ግን የወጣውን መመሪያ ያልተከተለ በመሆኑ ከተማ አስተዳደሩ ፈቃድ የማይሰጠው መሆኑን ገልፀዋል። ሌላኛውን የአንድነት ቡድን ወክላለው የሚሉ ግለሰቦች የእሁዱ ሰልፍ በአንድነት ፓርቲ ስም ሊካሄድ አይገባም ብለው በመቃወም ተፈራርመው ለአስተዳደሩ ማስገባታቸውንም ነው ሀላፊው የጠቆሙት። ሌላኛውን የአንድነት ፓርቲ ቡድን በአሁን ወቅት በፕሬዚዳንትነት እየመሩ የሚገኙት አቶ ትእግስቱ አዎሎ በአቶ በላይ ፍቃዱ […]

(ጥላሁን ካሳ) በአቶ ማሙሸት አማረ የሚመራው የመላው ኢትዮዽያ አንድነት ድርጅት/መኢአድ/ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሰጠኝን የቤት ሰራ ቀደም ሲል አጠናቅቂያለሁ ከዚህ በኋላ የምጠራው ጠቅላላ ጉባኤ የለም አለ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ማክሰኞ ጥር 19 ከአመራር ምርጫ ጋር ያሉበትን ችግሮች ፈቶ ሪፖርት እንዲደረግለት ነበር ከሁለት ሳምንታት በፊት አስገንዝቦ የነበረው። የቦርዱ ጥቅል መልዕክት ፓርቲው ላወጣው ህግ ይገዛ የሚል ይዘት ያለው ነው። ፕሬዝዳንትና ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳነት ሆነው በጽህፈት ቤት የቀረውን ፓርቲ የሚመሩት አቶ ማሙሸት አማረ እና ዶክተር ታዴዎስ ቦጋለ ከፓርቲው የተባረሩ እና በፓርቲው ደንብ መሰረት መዋጮ ያልከፈሉ መሆናቸውን በቀዳሚነት ተጣሰ ለተባለው ህግ ምክንያት ናቸው በማለት ጠቅሷል። ምክትል ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት ናቸው የሚባሉት ዶክተር ታዴዎስ ቦጋለ የማዕከላዊ ምክር ቤት አባል ያልነበሩ በመሆናቸው ራሱ ፓርቲው እገዛበታለሁ ብሎ ለቦርዱ ካሳወቀው አንቀጽ 7 ነጥብ 4 እና 4 ነጥብ 2 ውጪ መሆናቸውንም ቦርዱ ቀደም ሲል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቆ እንደነበር ይታወሳል። ፓርቲው በጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ሌላ ደንብ መጣሱንም የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና በጋዜጣዊ መግለጫቸው ማስታወቃቸው አይዘነጋም። ፕሮፌሰሩ ፓርቲው ቀደም ሲል የጣሳቸውን ደንቦች አስተካክሎ ለየብቻ የተከፋፈሉ ክንፎች አንድ ላይ ሆነው እንደገና ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተው የውስጥ ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ ተጨማሪ ጊዜ መሰጠቱንም በድጋሚ አብራርተዋል። በተሰጣቸው የሁለት ሳምንታት ጊዜ የመኢአድ ሁለቱም ክንፎች አንድ ላይ ሆነው የውስጥ ችግሮቻቸውን በመፍታት፥ እንደገና ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራትና ውጤቱን ሪፖርት […]

(ዳዊት መስፍን) የቀድሞው የአንደነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ ዋና እና ተቀዳሚ ፕሬዝዳንቶች የፓርቲው አባላት የቡድን ፓለቲካ የወለደውን የአንድነት መከፋፈል በጋራ ጉባኤ እንዲፈቱት ጥሪ አቀረቡ። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው በሴራ ፓለቲካ ህልውናው አደጋ ውስጥ የወደቀውን ፓርቲ ሊያድኑ የሚችሉት ህጋዊ አባላቱ ናቸው ብለዋል። አሁን ፓርቲውን እያመሰው ያለው የቡድን እና ዝምድና ፓለቲካ ነው የሚሉት ኢንጅነር ግዛቸው፥ የፓርቲው አባላትም የአንድነትን የቀደመውን ልዩነትን በዴሞክራሲያዊ መንገድ የመፍታት ስልት ተጠቅመው በሰከነ መንፈስ ችግራቸውን በመፍታት የፓርቲውን ህልውና እንዲታደጉት ጠይቀዋል። የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ኢንጀነር ዘለቀ ረዲም የፓርቲው አባላት በሁለቱም ጎራ በቆሙት ህገወጥ አመራሮች ላይ ጫና በመፍጠር ወደ ውይይት መድረኩ እንዲያመጧቸው ነው ጥሪ ያቀረቡት። የፓርቲው የ2000 እና የ2004 ውስጠ ደንብ ለአንድ ወር ፓርቲው በምክትል ተቀዳሚ ፕሬዝዳንቱ ይመራ ይላል። በወቅቱ ወንበሩ ላይ እንዲቀመጡ ደንቡ ይፈቅድላቸው የነበረው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ኢንጅነር ዘለቀ ረዲ ይህ እንዳልሆነ አንስተዋል። ከአንድነት ፓርቲ የስልጣን ወንበር ጀርባ ያለውን ሹክቻም ፕሬዝዳንቱን አስለቅቆ ቀጠለ ያሉት ኢንጅነር ዘለቀ፥ የእሳቸውም በምክትል ተቀዳሚ ፕሬዝዳንትነት መዝለቅ በደባ ተገዝግዞ እንዳጋደለ ተናግረዋል። በፓርቲው ውስጥ ያለው ሴራና ሽኩቻ እጅግ ስላሳዘነኝም ስልጣኔን በይፋ ልለቅ ችያለሁ ነው ያሉት ኢንጂነር ዘለቀ። ኢንጅነር ግዛቸው በፕሬዝዳንትነት ዘመኔ ለፓርቲው ድጋፍ ከውጭ ሀገራት የሚመጣው ገንዘብ በግለሰብ የሂሳብ ቁጥር መሆኑ ቀርቶ በፓርቲው የባንክ ደብተር ይሁን ማለታቸውንም አውስተዋል። የቀድሞቹ አመራሮች የተጎነጎነው ሴራ ከእኛ አልፎ ፓርቲውን ጠልፎ እንዳይጥለው ስንል ቀዳሚውን እና ተከታዩን የፓርቲውን የስልጣን […]

የአንድነት ለዴሞክራሲ እና  ለፍትህ ፓርቲ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ግዛቸው ሽፍራው የአንድነት አባለት ለፓርቲው ህልውና ሲሉ የተፈጠረውን ችግር በሰከነ መንፈስ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ:: የፓርቲው የቀድሞ ፕሬዝዳንት በእነ አቶ በላይ ፈቃዱ በሚመራው ቡድን ምክትል ፕሬዝዳንት ግርማ ሰይፉ በኩል ከፓርቲው  መሪነት የተነሱት ፓርቲውን የመምራት እና ጫናን የመቋቋም አቅም ስላልቻሉ ነው መባላቸውን በታህሳሱ ምርጫ ፕሬዝዳንታዊ ውድድር አቶ ግርማን  በከፍተኛ የድምፅ ልዩነት ማሸናፋቸውን በማንሳት ኃሳቡን አጣጥለውታል። በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ቀን ተሸናፊው አቶ ግርማ ራሴን ያየሁበት ውድድር ነው። ውጤቱም እንኳንስ ፓርቲ ወረዳ  መምራት የማልችል መሆኔን የሚያሳይ ነው ማለታቸውን ያስታወሱት ኢንጅነር ግዛቸው ስልጣኔን ያስረከብኩት ፓርቲው በቡድን ፓለቲካ እንዳይፈርስ ለህልውናው በማሰብ ነው ብለዋል። አሁን ፓርቲውን እያመሰው ያለው የቡድን እና ዝምድና ፓለቲካ ነው የሚል አስተያየት የሰነዘሩት ኢንጅነር ግዛቸው የፓርቲው አባላትም የአንድነትን የቀደመውን ልዩነትን በዴሞክራሲያዊ መንገድ የመፍታት ስልት ተጠቅመው በሰከነ መንፈስ ችግራቸውን መፍታት የፓርቲውን ህልውና እንዲታደጉት ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለሁለት የከፈሉት አመራሮች ችግራቸውን በጋራ በውይይት እንዲፈቱ የሁለት ሳምንት ግዜ መስጠቱ ይታወሳል። ********* ምንጭ፡- ፋና፣ ጥር 09-2007 More from Horn Affairs Amharic‘የእነበላይ ፍቃዱ አንድነት’ መግለጫ:- ‹‹የምርጫ ቦርድ ታሪካዊ ወንጀል እየፈፀመ ነው››ሰንደቅ ጋዜጣ:- ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ በሠነዘሩት አሉባልታ ሊከሰሱ ነውAudio| የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አመራር በአዲሱ ማስተር ፕላን ላይ የሰጡት መግለጫበኦሮሚያ ክልል በዩንቨርስቲዎች ስለተከሰቱት ግጭቶች ከመንግስት የተሰጠ መግለጫየመኢአድ ውዝግብ በድጋሚ አገረሸበመጪው ምርጫ ከፖለቲከኞቻችን፣ ከፖለቲካቸው እና ከህዝቡ ምን ይጠበቃል?

የመድብለ ፓርቲ ስርዓት እንዳይፈጠር የምርጫ ቦርድ ታሪካዊ ወንጀል እየፈፀመ ነው፡፡ ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ/አንድነት/ የተሰጠ መግለጫ የአንድንታ ፓርቲ በኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዲፈጠር በምንም መለኪያ በገለልተኝነት የማንጠብቃቸውን የዲሞክራሲ ተቋማት በተግባር ለመፈተን እንዲቻል የሁለት ሺ ሰባት ምርጫን በሁሉም ሂደቶች ህዝቡን በማሳተፍ እንደሚወዳደር እና ህዝብን የስልጣን ባለቤት ለማድረግ እና የኢህአዴግ አገዛዝ የመጨረሻ እንዲሆን በቁርጠኝነት እንደሚሰራ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ይህን ስንወስን እነዚህ ተቋማት ገለልተኝነታቸውን አረጋግጠው ታሪክ የሚሰሩበት እድልም ያገኛሉ የሚል ተሰፋ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ምርጫ ቦርድ ይህን እድል ከመጠቀም እና በህግ የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት ከመወጣት ይልቅ ለገዢው ፓርቲ ያለውን ወገንተኝነት በምርጫው ሂደት ዋዜማ በይፋ እያረጋገጠ ይገኛል፡፡ አሁንም ቦርዱ ወሰነ ተብሎ በሚዲያ የተገለፀው እንዲሁም ለፓርቲያችን በፅሁፍ የተሰጠው “በአስራ አምስት ቀን ውስጥ በጋራ ጉባዔ አድርጉ” የሚል ትዕዛዝ፤ ቦርዱ በተደጋጋሚ ፓርቲያችንን ደንብ እንዲያከብር እየጠየኩ ነው በማለት ከደንብ ውጭ እንድንሰራ የአዛኝ ቂብ አንጓች ሆኖዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ የመጥራት ኃላፊትን ያለበት የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ወይም ደግሞ በአባላት ጥያቄ የጠቀላላ ጉባዔ አባላትን አንድ ሶስተኛ ፊርማ አስባስበው በኦዲትና ኢንስፔክሽን ትዕዛዝ መሆኑ በግልፅ እየታወቀ ከፓርቲያችን መተዳደሪያ ደንብ ውጭ በ15 ቀን ውስጥ ጉባዔ ጥሩ የሚል ትዕዛዝ፤ ቦርዱ ከገዢው ፓርቲ ጎን ተሰልፉ እየተጫወተ አንድነትን ከጫወታ ለማስወጣት ካለሆነ ሌላ ምንም ትርጉም ልንሰጠው አንችልም፡፡ ይህ ደግሞ ቦርዱ እየሰራ ያለውን ታሪካዊ ወንጀል ይፋ የሚያደርግ ነው፡፡ ይህ በማን አለብኝ ሰሜት የተሰጠ ውሳኔ ሳይታረም ቢቀርና ገዢው ፓርቲ […]

(ፋኑኤል ክንፉ) ታህሳስ 28 ቀን 2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሳባ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የፈጸማቸውን የሕግ ጥሰቶች በመመርመር እስከ ጥር 4 ቀን 2007 ዓ.ም ድረስ በሕጉና እና በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት አሟልቶ እንዲያቀርብ በደብዳቤ ማሳወቁ ይታወቃል። ይህን የቦርዱ ጥያቄ ባይሟላ ቦርዱ የመጨረሻ ሕጋዊ እርምጃ በፓርቲው ላይ እንደሚወስድ በደብዳቤ ቁጥር አ/573/ፓ4/ጠ405 በተፃፈ ደብዳቤ መግለጽን ለማወቅ ተችሏል። የቦርዱን ማሳሰቢያ ከግምት በመውሰድ አንድነት ፓርቲ ጥር 1 ቀን 2007 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ የሕግ እና የውስጥ ደንብ ሁኔታዎችን የመመርመር ሥልጣን ያለው ጠቅላላ ጉባኤ መሆኑን ጠቅሶ፣ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን ጥር 3 ቀን 2007 ዓ.ም ቀበና መድሐኒዓለም አጠገብ በሚገኘው ጽ/ቤት ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ጀምሮ ለማድረግ መወሰኑን ለምርጫ ቦርድ በደብዳቤ አስታውቋል። በሌላ መልኩ ምርጫ ቦርድ ግልባጭ እያለ ለሚያሳውቃቸው “የእነአቶ አየለ ስሜነህ” የአመራር ቡድን በበኩላቸው፣ ታህሳስ 30 ቀን 2007 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤውን ጥር 3 ቀን 2007 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በሳሬም ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚያደርጉ በደብዳቤ ለቦርዱ አስታውቀዋል። ከላይ የሰፈሩት ሁለቱ አካሎች በተለያየ ቦታዎች ጉባኤ እንደሚያካሂዱ ማሳወቃቸውን አግባብነት የሌለው መሆኑን ገልፃ፣ ምርጫ ቦርድ በሁለቱም ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ታዛቢ ሳይልክ ቀርቷል። ዝግጅት ክፍላችን ከላይ የሰፈረው ውዝግብ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመገኘት ያጠናከረውን ዘገባ እና በእነአየለ ስሜ ጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡትን ፕሬዝደነት ቃለ ምልልስ ይዞ ቀርቧል። ዘገባው […]

* ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ለጉዳቱ መባባስ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያን ተጠያቂ አድርገዋል * “ቃጠሎው ከጃዝ አምባ አልተነሳም” የጃዝ አምባ ዋና ሥራ አስኪያጅ * እሣቱ ከጣይቱ ኪችን አለመነሳቱን አረጋግጣለሁ – አቶ አያሌው ታደሰ የጣይቱ ሆቴል ሥራ አስኪያጅ * አጋጣሚው ምትክ የማላገኝላቸውን ነገሮች ያጣሁበት ክፉ አጋጣሚ ነው – የፊልም ፕሮዳክሽን ባለቤት ባለፈው እሁድ ማለዳ ላይ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ከባድ ጉዳት የደረሰበት ታሪካዊው የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል እሣት መነሻ እያወዛገበ ነው፡፡ ፖሊስ እሳቱ የተነሳው በጃዝ አምባ አዳራሽ ውስጥ በተዘረጉ የኤሌክትሪክ መስመሮች መጠላለፍ ምክንያት የተከሰተ እንደሆነ ቢገለፅም እሳቱ ከጃዝ አምባ አለመነሳቱን የጃዝ አምባ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤርምያስ ፋንቱ ገልፀዋል፡፡ የጃዝ አምባ የኤሌክትሪክ ሲስተም አዲስና ደረጃውን የጠበቀ በመሆኑ ለእንዲህ አይነት አደጋ የሚጋለጥበት ምንም ምክንያት እንደሌለና ላለፉት አራት ዓመታት ምንም ዓይነት ችግር አጋጥሞ እንደማያውቅ የተናገሩት አቶ ኤርሚያስ፤ ፖሊስ እሳቱ የተነሳው ከጃዝ አምባ ነው ማለቱ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡ “ከሙዚቃ መሳሪያ ጋር በተገናኘ እሳቱ ተነስቷል እንዳይባል እንኳን እሁድ ጠዋት የጃዝ አምባ ሰራተኛ የሆነው ልጅ ገብቶ መድረኩን ለቴአትር ዝግጁ ለማድረግ ሁሉንም የሙዚቃ መሳሪያ አነሳስቶ ነበር” ብለዋል፡፡ ሌላው እሳቱ ከጃዝ አምባ እንዳልተነሳ እርግጠኛ የሆኑበትን ምክንያት አቶ ኤርሚያስ ሲናገሩ፤ የህብረት ባንክና የጃዝ አምባ ሲስተም አንድ መሆኑን ጠቁመው፣ እሳቱ ተነስቶ ከጀርባ በኩል ጭስ ሲታይ ሰዎች ከኤቲኤም ማሽን ብር እያወጡ እንደነበር አስታውሰው፣ እሳቱ ከጃዝ አምባ ቢነሳ ኖሮ ኤቲኤም ማሽኑ አይሰራም ነበር  ሲሉ እሳቱ […]

*የደም ናሙናው ለተጨማሪ ማረጋገጫ ወደ አሜሪካ በዛሬው ዕለት ተልኳል፡፡ በትናንትናው ዕለት አንድ ከሴራሊዮን የመጣ ግለሰብ በኢቦላ ሕመም ተጠርጥሮ ምርመራ ቢደረግለትም ከቫይረሱ ነፃ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ አስታወቁ፡፡ ታማሚው በሴራሊዮን በአንድ የአለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጀት በኩል ተቀጥሮ የአካባቢ ቁጥጥር ባለሙያ በመሆን  ይሠራ የነበረ  ሲሆን፥ ከሴራሊዮን ከተመለሰ በ15ኛ ቀኑ በትኩሣት ራሱን በመሳቱ በተደረገለት የደም ምርመራ ፋልሲፓረም የተባለ የወባ በሽታ የተገኘበት በመሆኑ ለዚሁ አገልግሎት ባዘጋጀችው ላብራቶሪ ለኢባላ የደም ምርመራ ተደርጎለት ውጤቱ ከበሽታው ነፃ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በላብራቶሪ ውጤቱ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ብንሆንም ታካሚው ሴራሊዮን ደርሶ ከመመለሱ አንፃር የደም ናሙናው ለተጨማሪ ማረጋገጫ ወደ አሜሪካ በዛሬው ዕለት መላኩንና ከ48 እስከ 72 ሰዓታት ውስጥ ውጤቱ እንደሚታወቅ ነው የተመለከተው። በውጤቱ ላይ ለውጥ የሚኖር ከሆነ በቀጣይ ሚኒስቴሩ እንደሚያሳውቅ ዶክተር ከሰተብርሃን ገልጸዋል፡፡ ታካሚው በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ረፋድ ላይ ሕይወቱ ማለፉንም ነው ያስታወቁት፡፡ የተላከው ናሙና ውጤት እስከሚመጣ ድረስ ከተጠርጣሪው ጋር ቀጥታ ግንኙነት የነበራቸው ጓደኞቹና ቤተሰቦቹ ላይ የባለሙያ ክትትል በመደረግ ላይ መሆኑም ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ ኢቦላን ለመከላከል የምታደርገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ አረጋግጠዋል፡፡ ******** ምንጭ፡- ፋና – ጥር 6፣ 2007 More from Horn Affairs Amharicበአሶሳ ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ ተከሰተ – ክልሉ ኢቦላ አይደለም ይላልየኬሚካል ክምችትና የአደጋ ስጋት በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶችዓለማየሁ አቶምሳ – ኪራይ ሰብሳቢነትን አምርሮ የታገለና ያታገለኢትዮ-ቴሌኮም በ75 የአዲስ አበባ አካባቢዎች የኔትወርክ ችግር ፈታሁ […]

ላለፉት 28 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ያገለገሉት ዶ/ር መረራ ጉዲና ከኮንትራት ቅጥር አፈፃፀም ጋር በተያያዘ ከዩኒቨርሲቲው ጋር አለመስማማታቸው ታወቀ። ዶ/ር መረራ ስለጉዳዩ ከሰንደቅ ጋዜጣ ተጠይቀው ካለፈው ሐምሌ ወር 2006 ዓ.ም ጀምሮ ጡረታ እንዲወጡ እንደተጠየቁና ጥያቄውን እንዳልተቀበሉት ተናግረዋል። ለዚህም የሰጡት ምክንያት አንድ ለጡረታ የደረሰ ሰው ሦስት ዓመት እንዲራዘምለት መጠየቅ የሚችልበት የሕግ አግባብ ስላለ ነው ብለዋል። ከሐምሌ 2006 ዓ.ም ጀምሮ የዩኒቨርሲቲው የሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ በኮንትራት እንዲሰሩ የቀጠራቸው መሆኑን አስታውሰው ሆኖም የዩኒቨርሲቲ ፐርሶኔል ክፍል ቅጥሩን አልቀበልም በማለቱ እስካሁን ጉዳዩ በእንጥልጥል ላይ መሆኑን ገልፀዋል። በዩኒቨርሲቲው የሴኔት ሕግ መሠረት ኮሌጆቹ የሚፈልጉትን መምህር የመቅጠር መብት እንዳላቸው በማስታወስ የፐርሶኔል ክፍሉ በማያገባው ገብቶ ቅጥሩን ከልክሏል ብለዋል። ከዚሁ አለመግባባት ጋርም ተያይዞ ላለፉት ስድስት ወራት ደመወዛቸው መቋረጡን ጠቅሰው፤ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ያላቸውን ሁኔታ ተከታትለው መፍትሄ ከጠፋ መብታቸውን በሕግ ለማስከበር ማሰባቸውን ጨምረው ገልፀዋል። በጉዳዩ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። ዶ/ር መረራ ጉዲና ከዩኒቨርሲቲው መባረራቸውን ሰሞኑን በአንዳንድ ማኅበራዊ ድረገጾች መዘገቡም አይዘነጋም። ******* ምንጭ፡- ሰንደቅ፣ ታህሳስ 22-2007 More from Horn Affairs Amharicዶ/ር መረራ ጉዲና – ለ6 ወር ደሞዝ አልተከፈለኝም፣ ፕሮፌሰርነት እስካሁን ድረስ አልተሠጠኝምሰንደቅ ጋዜጣ:- ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ በሠነዘሩት አሉባልታ ሊከሰሱ ነውዶ/ር መረራ ጉዲና፡- ኢሳት ጠመንጃ የለውም፣ የትጥቅ ትግልም እያካሄደ አይደለምኢትዮ-ቴሌኮም በ75 የአዲስ አበባ አካባቢዎች የኔትወርክ ችግር ፈታሁ አለዓለማየሁ አቶምሳ – ኪራይ ሰብሳቢነትን አምርሮ የታገለና ያታገለየኢዴፓ መግለጫ – “በሽብርተኝነት ስም […]

(አለማየሁ አንበሴ) ባለፈው ሳምንት በማህበራዊ ድረ-ገጽ በተሰራጨ መረጃ፣የፖለቲካል ሣይንስ መምህርና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና፤ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጡረታ እንደተባረሩ ቢነገርም መረጃው እውነት አለመሆኑን ከአንደበታቸው ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ሆኖም ከዩኒቨርሲቲው ጋር የተፈጠረ ችግር እንዳለ ይናገራሉ – ዶ/ር መረራ፡፡ ችግሩ ምን ይሆን? ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ፤ይሄንንና ሌሎች ከመምህርነት ሙያቸው ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ጠይቋቸው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ አዲስ አድማስ:- ከዩኒቨርሲቲው ጋር የተፈጠረው ችግር መነሻው ምንድን ነው? ዶ/ር መረራ ጉዲና:- ሁሉንም ሲያልቅ መናገር ይሻላል፡፡ ነገር ግን ለ6 ወር ያስተማርኩበት ደሞዝ አልተከፈለኝም፤ መነሻው ይሄ ነው፡፡ ፓርላማ በቆየሁባቸው ጊዜያትም ደሞዝ አይከፈለኝም ነበር፤ የዩኒቨርስቲው ይበቃሃል ተብዬ፡፡ እዚህም እንግዲህ ለ6 ወር በነፃ እያገለገልኩ ነበር ማለት ነው፡፡ አዲስ አድማስ:- ምክንያቱ ተነግርዎታል ? እርስዎስ አልጠየቁም ? ዶ/ር መረራ ጉዲና:- የቅርብ አለቆች እየተነጋገሩበት ነው የሚል ምላሽ ነው የተሰጠኝ፡፡ ግን ማስተማሬን አላቆምኩም፤ በነፃ እያገለገልኩ ነው ማለት ነው፡፡ ምናልባት መፍትሄ ካልተገኘ መብቴን ለማስከበር ወደ ፍ/ቤት ላመራ እችላለሁ፡፡ አዲስ አድማስ:- በዩኒቨርሲቲው ምን ያህል ጊዜ አስተማሩ? ዶ/ር መረራ ጉዲና:- እሱ የአደባባይ ሚስጥር ነው፤ ለ28 አመት ፖለቲካል ሣይንስ አስተምሬያለሁ፡፡ አዲስ አድማስ:- በዩኒቨርስቲው በሃላፊነት የመስራት እድል አጋጥሞት ያውቃል? ዶ/ር መረራ ጉዲና:- አዎ! በሦስት የተለያዩ ጊዜያት የፖለቲካል ሣይንስ ትምህርት ክፍል ተጠሪ ነበርኩ፡፡ ለምን ያህል ጊዜ እንደሆነ በትክክል ባላስታውስም ለመጨረሻ ጊዜ በኃላፊነት የሠራሁት ከሦስት ዓመት በፊት ነው፡፡ ኢህአዴግ ከገባ በኋላ ሦስት ጊዜ ሃላፊ ሆኜ ሰርቻለሁ፡፡ አዲስ አድማስ:- የተቃዋሚ ፓርቲ […]