የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የፍርድ ቤት ውሎ – የካንጋሮ ፍርድ ቤቱ ድራማ – ቀጠሮ ለ36ኛ ጊዜ ጳጉሜ 2 2007

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የፍርድ ቤት ውሎ – የካንጋሮ ፍርድ ቤቱ ድራማ – ቀጠሮ ለ36ኛ ጊዜ ጳጉሜ 2 2007

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የፍርድ ቤት ውሎ (Update) #Freezone9bloggers

በዛሬው እለት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የወያኔ ካንጋሮ ፍርድ ቤት ቀርበዋል::አራቱ ጦማርያን በፍቃዱ:ናትናኤል:አቤል:እና አጥናፍ በጥቁር ሱፍ ደምቀው በፍርድ ቤቱ ተገኝንዋል::ንጽሕናቸውን በተለያየ መንገድ እየገለጹ ያሉት እና የፍርድ ቤቱን ነጻ አለመሆን በተግባር ያሳዩት ጦማርያን በራስ መተማመን ከፊታቸው ይነበባል::ወደ ችሎቱ 84 ሰዎች ገብተዋ የፍርድ ሂደቱን እየተከታተሉ ነው::

ዳኞቹ አርፍደዋል:: በችሎቱ ውስጥ ዝምታ ሰፍኗል:: የፍርድ ቤቱ ጠባቂ ፖሊስ ከችሎቱ መግቢያ ጠረጴዛ ላይ ጣፋጭ እንቅልፍ ተኝቷል::በችሎቱ ውስጥ ያሉ የጦማሪያኑ ደጋፊዎች ዲፕሎማቶች እና ጋዜጠኞች ዳኞቹ እስከሚመጡጡ በሚል ይመስላል በዝግታ እያወሩ የችሎቱን ጸጥታ በንግግር ትንሽ ሞቅ አድርገውታል::

ዳኞቹ አልገቡም ::የዞን ዘጠኝ ጦማርያን ጠበቆቻቸው ወደ ቢሮ ተጠርተው ገብተዋል:: ጦማርያኑ ከጀርባ በር በኩል እንዲቀመጡ ተደርገዋል:: ዳኞቹ ችሎት ሳይሰየሙ ከጀርባ ሆነው የሚሰሩት ድራማ ሰዉን አስጨንቆታል::የካንጋሮ ፍርድ ቤቱ ድራማ ቀጠሮ ለ36ኛ ጊዜ ጳጉሜ 2 2007 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።