በኢትዮዺያ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፃቸው በዲስክ የተቀረፀው የምኒሊክና የጣይቱ ነው::

( የአባ ዳኘውን ድምፅ ከታች ያገኙታል)
በሸክላ (ዲስክ) እየተቀረፀ የሚጫወተው መሣሪያ ( ግራሞፎን) ወደ ኢትዮዺያ የገባው በምኒልክ ዘመነ ምንግስት ነው:: የመጀመሪያው ግራማፎን በ1889 ዓ.ም ሄንሪ ደ ኦርሊንስ እና ኒኮላስ ሊዎንቲቭ ለምኒልክ አመጡላቸው::

ይህም እነሊዎንቲቭ ያመጡት ግራማፎን መጫወት ብቻ እንጂ ድምፅ የማይቀዳ ነበረ:: በኃላ በአመቱ በ1890 ዓ.ም ከንግስት ቪክቶሪያ የተላኩ የእንግሊዝ መልክተኞች በመጡ ግዜ ግራማፎኑንና ድምፅ መቅጃውን ይዘውላቸው መጡ:: እነኚህ መልክተኞች የእንግሉዝን ንግስት የንግስት ቪክቶሪያን ሰላምታ በዲስክ ቀርፀው አምጥተው ስለነበር ምኒልክና ጣይቱ ባሉበት መልክተኞቹ ዲስኩን አሰሙ:: ጣይቱም ስማቸውን ዲስኩ ውስጥ ሲሰሙ ‘እረ የኔንም ስም ትናገራለች’ አሉ::

በኃላም የምኒልክና የጣይቱ ድምፃቸው (ሰላምታቸው) ተቀድቶ ለንግስት ቪክቶሪያ ተላከ::

እንግዲህ በኢትዮዺያ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፃቸው በዲስክ የተቀረፀው የምኒሊክና የጣይቱ ነው::

*ዻውሎስ ኞኞ – አጤ ምኒልክ ገፅ 340

 

[youtube http://www.youtube.com/watch?v=7qV27-OT5IE&w=650&h=355]