በኢትዮጵያ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር 4.5ሚልዮን መድረሱ ተገለጠ
በተባበሩት መንግሰታት የሰብአዊ ድጋፍ ቢሮ ይፋ ባደረገው አዲስ ሪፖርት በኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር በያዝነው ወር 4.5ሚልዮን መድረሱን ይፋ አድርጓል፡፡ የ2015 ግማሽ አመት የሰብአዊ ድጋፍ ተፈላጊነት ከተገመገመ በኋላ ሪፖርቱ ይፋ ሲደረግ ለጋሽ አገራትና የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዩች በስፍራው መገኘታቸውን መረጃው ጨምሮ ጠቁሟል፡፡ ሪፖርቱ በተጨማሪ ለምግብና ምግብ ነክ ላልሆኑ ነገሮች የሚያስፈልገው የእርዳታ መጠን በጃንዋሪ(ጥር)ወር ተተንብዮ ከነበረው […]![]()