ቃለ አዋዲና ፍልሰታን አስመልክተው ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በነጻነት ለኢትዮጵያ ሬዲዮ የሰጡት ቃለ-መጠይቅ

Kesis Asteraye Nigatu
በአቡነ ቴውፍሎስ  ተረቅቆ በግ. ቀ. ኃይለ ሥላሴ ዘመን ጊዜ ታውጆ በደርግ ዘመን ሥራ ላይ የዋለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መተዳደሪያ ደንብ (ቃለ አዋዲ) ዛሬ የሚታየውን የሰበካ ጉባኤ የተጀመረበት ነበር። ይህንን ታላቅ ተግባር ጫንቃቸው ላይ አርፎ  ከነበሩት አባቶች መካካለ  ከጥቂት ዓመታት በፊት  ከዚህ ዓለም የተለዩን አባ አበራ በቀለና አብረዋቸው እንዲሰሩ ከጠቅላይ ቤትክህነት የተመደቡት ሁለት ሊቃውንት ይገኙበታል። ከነዚህም አንዱ ቀሲስ አስተርአየ  ጽጌ  ነበሩ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰበካ ጉባዔ ተዘዋዋሪ አደራጅ አስተማሪ  የነበሩት ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  ስለ ቃለ አዋዲና  የፍልሰታ መንፈሳዊና ታሪካዊ ትስስር እግረ መንገዳቸውን በዚህ ቃለ መጥይቅ ይዳስሳሉ። ሙሉውን ቃለ መጠይቅ የሚቀጥለውን ሰንሰለት  በመጫን  ያዳምጡ።
ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ከነጻነት ለኢትዮጵያ ሬዲዮ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ

6 Comments on “ቃለ አዋዲና ፍልሰታን አስመልክተው ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በነጻነት ለኢትዮጵያ ሬዲዮ የሰጡት ቃለ-መጠይቅ”

  1. ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል:በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል says:

    እዎድሽ የነበር እንደ መቀነቴ:ሸርሙጣ ነሽ ቢሉኝ ተቆረጠ አንጀቴ:

  2. Wow, I did not know that Qale Awadi started 40 years a go and we have someone who could tell us the story of the bylaw. I hope Qesis Asteraye would tell us more.

  3. እንደ ቀሲስ አስተኣየ ጽጌ ዓይነት ታላላቅ ሊቃውንት ያፈራች አገር እጅግ የሚያሳዝነው “ጅብ በማያውቁበት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል” እንደሚባለው ተዝቆ የማያልቀውንና ከ30 ና 40 ዓመታት ትምህርትና ጥናት በኋላ እንኩዋን ሊገባደድ የማይችለውን የአብነት ትምህርት በአቋራጭ ነጥቀው የመጡ የዘመናችን መምህራን ተብየዎች እየፉዋለሉብን ነው። ውስጣቸው ባዶ ስለሆነና ግብረገብ ስለሌላቸው እንደ ባዶ ቆርቆሮ መጮህ ብቻ ነው የሚቀናቸው። በተለይ የግዕዝ ቋንቋ እነሱጋ ማንሳት ጫጩት ፊግ ስለ ፈንግል አይወራም እንደሚባለው ነው። እነዚህ ዘመን አመጣሾች የኢ/አ/ተ/ቤ/ክ አያውቋትም፤ ግን በስሟ ይነግዱባታል፣ ይዘሙቱባታል፣ ያተፉባታል። እነዚህ እፍረተ ቢሶች በባዶ ማዕረግና ክብርን ሊያገኙ ቢፈልጉም በአገራችን ሁሉም ነገር ሲስተካካል እራሳቸውን ዋርካ ቢያሳክሉም ቁጥቋጦና የመንገድ ሙጃ መሆናቸው ህዝብ ያሳያቸዋል።

  4. ለጉንጭ አልፋ ፍሬከርስኪ አውርቶ አደር EliAss Kifle

    Berhanu Nega ill from food poisoning
    Post a reply
    Postby elias » 04 Aug 2015, 21:27

    Our sources in Eritrea have informed us that AG7 chairman Dr Berhanu Nega is currently recovering from food poisoning. If his condition doesn’t improve he will travel to Europe for treatment, the sources added. Coalition talks between AG7 and TPDM continue but agreement may be delayed. Also stay tuned for U.S. Government’s official statement pertaining to Dr Berhanu’s move to Eritrea and related issues. Yosef Haimanot, a young Ethiopian-British national who went to Eritrea to visit the Ethiopian opposition group, EPPF, is still missing and presumed to be in jail or killed. His friends in London have informed ER that the London police is processing a report for investigation by the Interpol.

    [Caption: Dr Berhanu Nega at the AG7 office in Asmara]
    Reported by EliAss kifle
    ከጉንጭ አልፋ ፍሬከርስኪ አውርቶ አደሮች መንደር

    ውሻ ጮኸ ተብሎ ድንጋይ አይወረወርም

    July 22, 2015

    ቹቸቤ ነኝ አማን ነው? የሰሞኑን ነገር ለመግለጥ የሚሆን መንደርደርያ ፍለጋ ስባጅ ቆየሁ። ዛሬ ሁሉም ተናጋሪ ቢሆንም የነገር ድግግሞሽ አታክቶናል። ገና የተተነፈሰው እንደሰሚው ተወላግዶ ወይም ጣፍጦ የበሬ ግንባር በምታክለው ፌስ ቡክ ይለጠፋል። ወሬ ብርቅ አይደለም። እንዲያውም በርካታ ተግባር አልባ የወሬ ቤቶች ተከፍተው ወሬ ሲወቁ ነገር ሲሰልቁ ቡና ቤት መለወጥ እንደሚወድ ጠጪ ከአንዱ ፓልቶክ ወደ ሌላው እየዞሩ በጉንጭ አልፋ ፍሬከርስኪ የሚያደነቁሩን አውርቶ አደሮች በዝተውብናል። ከሁሉ የሚያሳዝነው ደግሞ ከፈር ቀዳጅ ታጋዮቹ መንደር ነበርንና አንቱ በሉን የሚሉ እድሜ ጠገቦቹ ከተማሪ ረብሻ ወዲህ አርባ አመት ያስቆጥሩም ቢሆን ዛሬም እንኳ የአስተሳሰብ ጨቅላነታቸውን አለመጨረሳቸውና አሁንም በረብሻ መተዳደርን የመረጡ በሚያስመስል አፍራሽ ተግባር ተጠምደው ማየታችን ነው።

    በእድሜ ዘመናቸው አንድም ሚዛን የሚደፋ ቁምነገር ሰርተው አያውቁም። በተለይ ደግሞ ወያኔ ወደስልጣን ከመጣ በሁዋላ ከኛ በላይ የወያኔ ተቃዋሚ ለአሳር እያሉ ሽንጣቸውን ገትረው የሚውረገረጉም ቢሆን የዚህን አረመኔ ወያኔ እድሜ የሚያረዝም እንጂ የሚያሳጥር ምንም ሰርተው አያውቁም። እንዲያውም ከእድር ለየት ባለ የፖለቲካ ቡድንነት የተሰባሰቡ መሆናችው ትዝ የሚላችውና ነገር ጣል ለማደረግ የሚባንኑት ሌላው ወገን የሰራው ነገር መኖሩን ሲሰሙ ነው። ያኔ አይናቸው ደም ይለብሳል እንደ ወያኔ ተለጣፊ ወይም ተመሳሳይ ነገር ሰርተው የተሰራውን ለማፍረስ ይጣደፋሉ። ገና አልባነነ ይሆናል እንጂ ጋዜጠኛውም ከፍርስራሾቹ አንዱን እየሆነ ነው። እንዲያውም ቆመጥ አድርገውት የራሱን ኢሳትን ይደበድቡበታል። እርሱም ዝናዬን ቀሙኝ ኩርፊያ የያዘ ይመስል አጓጉል መሄዱን መርጧል። ብቻ አጎቶቻችን ለማፍረስ ሲሆን እንደ ተኩላ ናቸው በጩኸት ይጠራራሉ ሳይነጋገሩ ይግባባሉ። ድርጅት በአይነት በአይነት ያቋቁሙና የመጥለፍ ጥማታቸውን ለጊዜውም ቢሆን ያረካሉ። የጀመሩትን ከምን እንዳደረሱት የሚጠይቅ ስለሌለ አዲስ ባቆሙት ላይ ያወራሉ። ትግል የሚለውን ቃል በግርድፉ እንዲያው ቃል በቃል ወስደው ነው መሰል አድማ እየመቱ ከሁሉም ሲታገሉና ሲያፈርሱ እድሜ ራሱ አፈራርሶ ሊጨርሳቸው ነው።

    በመጨረሻ አንደርዳሪ ብልጥ ሃሳብ አገኘሁ እነሆ የብልህ ሰዎች ማህደር ከዊንስተን ቸርችል አባባል ላይ ወስዶ የለጠፈው ቃል ማረከኝ። “ውሻ በጮኸብህ ቁጥር ድንጋይ እያነሳህ የምትወረውር ከሆነ ካሰብክበት አትደርስም” የሚል ነው። አዎ ሩቅ ለመሄድ አልመው ድንጋይ ወርዋሪና ማዶ ለማዶ ቆሞ ተሳዳቢነትን የመረጡ ያሰቡበት አይደርሱም። ሰሞኑን የሚነፍሰው ንፋስ ግምኛ ነው ይሰነፍጣል። በርግጥ እነዚህ ሰዎች ነጻነትን ይፈልጋሉ ወይንስ እኛ ካላረግነው ሁሉም አፈር ይብላው የሚሉ ናቸው? እውን እነዚህ ሰዎች ለአፍራሽ ተልዕኮ የሚሰጣቸው ፍርፋሪ ኖሮ ነው ወይንስ ኑሮአቸው ይኸው ግርግር የመፍጠር ሆኖ ነው? ያስብላል። በተለይ የተማሩትና የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል እያሉ የሚጽፉት ምሁራኖች እነሱ ባሉብት መድረክ ላይ በጠንካራ ታጋዮችና መሪ ድርጅቶች ላይ ተራ ስድብ ሲደረደርና ትግሉን የሚጎዳ ግርድፍ ሀሳብ ሲዥጎዶጎድ በዝምታ ማለፋቸው ምን ይባላል? እኔን አንቱ እስካላችሁኝ ድረስ ሌላውን ድባቅ ብታስገቡትና ትግሉን ብትጎዱት እኔ ምን ገዶኝ ብለዋል ማለት ነው? ይሄ ከሆነ ስሌቱ ፍላጎታቸው መድረክ ላይ መኮፈስ እንጂ ሀገርን ማዳን አይደለም ብለን እኛም ለእንደዚህ አይነቶቹ የሚቸረውን አክብሮት እንሰጣቸዋለን።

    በተግባራዊ ትግል የተጠመደው ወገን ደግሞ እነ ሰው ከንቱን ቁም ነገር አድርጎ አቧራ ማጨሱን ተወት አድርጎ ጊዜውን ተግባራዊው ትግል በሚፈልገው እንቅስቃሴ ላይ ቢያተርኩር ይሻላል። የእነኚህ አፍራሽ ወሬኞች ፋይል መዘጋት አለበት። እነርሱን ሰምቶ ከመንጫጫት ከግንቦት ሰባት አመራር ተምረን ለወሬኞች የምናባክነው ሰአት የለንም ብለን ወደተግባሩ እንመለስ። የግንቦት ሰባት አመራሮች ለርካሽና ተልካሻ ነገር መልስ ለመስጠት ደፋ ቀና ሲሉ አናያቸውም። ስራው ላይ በማተኮራቸው የእምነት ጽናትም በማሳየታቸው መሬት ላይ የሚታይ ስራ እየሰሩ ነው። ‘በርገር’ እየበሉ ግፋ በለው ብቻ እንደማይሉ ደግሞ በተግባርም እያሳዩ ነው። የሚበልጠው ለእናት ሀገር ለመዋደቅ የቆረጡ ወጣቶችንና አርበኞችን መደገፍና ትግሉን ማፋፋም ወይንስ የአሽሙር ጧፍ እያበሩ የእርግማን አዝማች ያለው የስድብ መዝሙር መዘመር?

    ምርጫችንን ልናውቅ ልንበስልና ልንበቃ የሚገባን ጊዜ ላይ ነንና ከአመት አመት ራሳችንን እዚያው የነበርንበት ላይ ማግኘት ደካማ አቅማችንን ፀሀይ ማስሞቅ ይሆናል። ለዚህ ነው እነ ስም አይጠሬን ከቁም ነገር መድረክ ላይ ቆልለን በጮሁ መጠን ቃላት የምንወራወር ከሆነ መቼም ቢሆን ካሰብንበት አንደርስም ለማለት የወደድኩት። እንዲያውም ተጋብቶብን ቀንደኛ ተሳዳቢና አለክላኪ ተጓዥ ሆነን እርስበርስ የመነካከስ ባህርያትንም እየወረስን ነውና እነሱን ከመሆን ያድነን እንበልና ወደፊት እንገስግስ። ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር የሚል መፈክር ትዝ የሚለው ማነው? አዎ ያኔ ያለቀ ቢሆን ዛሬን ባልዘመትን ነበር።
    ድል የማይቀር እውነት ነውና ዱር ቤቴ ላሉት ደጀን መሆን ምርጫችን ይሁን!

    የአፍራሾች ዋይ ዋይታ (ደነባ ጉልላት)

    July 25, 2015

    ደነባ ጉልላት

    ስንሰማ የነበረው ወያኔን በትጥቅ ትግል የሚፋለም ጠፋ ነበር ። ስንሰማ የነበረው የሕዝባዊ ሀይሉ መሪ ዶክተር ብርሃኑ በግንባር አልተገኙም የሚለውን ነበር ። ሁለቱም ቅሬታ ሲወገድ ግን ዋይ ዋይታና ኡ ኡታ የሚያሰሙ ከየስርቻው ብቅ አሉ ።

    ከማንም በፊት ወደ ሻዕቢያ ሂዶ የነበረው ኤልያስ ክፍሌ የዚሁ ፊታውራሪ ሆኖ ብቅ አለ ። ወዳጅ ሲለው የነብረውን ሻዕቢያን ጠላት ብሎ ሰይሞ ተጀመረ የተባለውን የትጥቅ ፍልሚያ ሀሰት ሲል ኮነነ ። ሕዝባዊ ሀይሉን ቁጥር ከ ፲ ወደ መቶ ቢያደርሰውም የትም አልተንቀሳቀስም ብሎ አስተባበለ ።ይኽው ግለሰብ ግን የዴምህት ሀይል በኤርትራ ፵ ሺ ደርሷል ይለናል ። ለዚህ ያህል የማይንቀሳቀስ ጦር ምን ያህል ወጪ ይጠይቃልን አላሰበበትም ።ኢሳያስም የሌላ ህገር ዜጎች ያሉበት ይህን ያህል ጦር ማስተናገድስ ለደህንነቱ ይበጀዋል? ምን ገዶት ለኤልያስ!የኢትዮጵያ ረቪው የኢንተሊጀንስ ክፍል ባገኘው መረጃ መሰረት እያለ ውሸት መጠረቅ ልምዱ ነው ። ኤርትራና ሻዕቢያ ጠላት ከሆኑን ኢሳያስን የዓመቱ የኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ያለ ኤልያስ ሊወገዝ የሚገባው ይሆናል ። ኾለኔል ፍጹም ያን ሁሉ ወጣት ከረሸነ ለምን ይህንን ለማጋለጥ ዓመታት ፈጀበት ብንል መልሱ ራሱ ጠቋሚ ነው ።ኤልያስ ክፍሌ ለመሆኑ አለሁ አለሁ ማለት ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ የማንን አጀንዳ ነው በስራ ላይ እያዋለ ያለው ጥያቄ እንዳለ ሆኖ ዋናው ተል እኮእ ግን አርበኛ ሀይሉን/ታጋዮችን መበጥበጠ መሆኑን ታሪኩ ይመስክራል ።

    ሌላው ዋይ ዋይታ አሰሚ አቶ መልኬ ሲሆኑ ወደ ኤርትራ የዘለቁት በዚያ ዋሾና ተራ ሌባ አብርሃም ያዬህ ተወስደው ነውና ያጋጠማቸው መጥፎ ተመክሮ ካለ ቅሬታቸው ቢገባንም ስለ አርበኞች ግንባር ያላቸው ዕውቀት ግን ጊዜ ያለፈበት መሆኑ የሚታይ ነው ። ደምስ የሚባለው በበኩሉ የመኢሶን ገራፊነት ታሪኩን እያነሱ ቀልቡን የሚገፉት እንዳሉ ሲታወቅ እሱም ቢሆን አርበኞች ግንባርን ደጋፊ መስሎ በተደጋጋሚ ወደ ኤርትራ የዘለቀ ነው ።ለምን መሄድ እንዳቆመ ኮለኔል ፍጹምን መጠይቅ አንገደድም —እናውቀዋለን ምክንያቱንና ነው ። እስካዛሬ ድምጹን አጥፍቶ ተደብቆ ከርሞ አሁን በግንቦት ፯ና አርበኞች ግንባር ላይ ምን አስነሳው ? በሻዕቢያም ሆነ በአርበኞች ግንባር መሪዎች ግፍ ተፈጸመ ካለስ ለምን እስካሁን ዝምታን መረጠ ብለን ስንጠይ

  5. ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል:በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል says:

    @ጉንጭአልፋ-ድሮም ከዝንብ ማር አይጠበቅም:አንተ ዋነኛው ፍልጥ በመሆንህ እንደ ጎሽቱ ጠላ ነገር ትደጋግማለህ:ነገር ከመድገም ዳዊት ድገም በዚያውም…

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*