Minilik Salsawi የወያኔው ስርኣት ተናግቶ በመላው አገሪቱ ከፍተኛ ውጥረት መንገሱ እያየን እንገኛለን::ላለፉት ስምንት ሳምንታት በመላው የኦሮሚያ ክልል የተነሳው የሕዝብ ተቃውሞ የሕዝብን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ሕዝብ ከዳር እስከዳር በሕብረት ሆ ብሎ መውጣቱ በቂ ማስረጃ እያለ ጥቂት ነውጠኞች በማለት ማጣጣል የወያኔ አገዛዝ …

ሕዝብን ጥቂት ነውጠኛ ብሎ መፈረጅ የአገዛዙን ድንቁርና ይመሰክራል:: (ምንሊክ ሳልሳዊ‬) Read more »

ከሰሞኑ የተቆሰቆሰዉን ጦርነት ለመከታተልና ለማጥራት በሚል የተንቀሳቀሱ የወያኔ አንጃ ወታደሮች ቡድን ጥቃት እየደረሰባቸዉ ይገኛሉ፡ ወያኔ በአዲግራትና ከማይ ጻይ ተወርዋሪ አየር መንደርደሪያ ሰፈሮች ባሻገር በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች እያለፈና እየዘለለ የሚደርስበትን ጥቃት ለማድበስበስ በየስፍራዉ የመከላከያ ሰራዊቱ ስልጠና ላይ ነዉና የተኩስ ድምጽ ብትሰሙም እንዳትደናገጡ እያለ ከባለፈዉ መጋቢት ወር አንስቶ ወረቀት እየለጤፈና እየደሰኮረ ይገኛል። አንድ ማንነቱን ሊገልጽ ያልፈለገ የወያኔ […]

ሰበር መረጃ “ዛሬ ጠዋት አርበኞች ግንቦት ሰባት ባሳቻ በሰነዘረው ጥቃት ስፍር ቁጥር የሌለው የወያኔ ጋሻጃግሬዎች ሲደመሰሱ ገሚሱ ትግራይ ቦርደር ሆስፒታል እየተባለ ወደ ሚጠራዉ የህክምና ተቋም ቁስለኛ ወታደሮች ለህክምና ሲትም መዋሉን ከስፍራው ያይን ምስክር በተለይም ለ አፈትላኪ ዜና ምንጭ ዘግይቶ አድርሶናል። ይህበንዲህ እንዳለ ማይ ጻይ እየተባለ ከሚጠራዉ አካባቢ የሚነሱ ሄሊኮፍተሮች በአየር መቃወሚያ ወሰን ኢላማ ዉስጥ ገብተዋል።በተያያዘም […]

በተባበሩት መንግሰታት የሰብአዊ ድጋፍ ቢሮ ይፋ ባደረገው አዲስ ሪፖርት በኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር በያዝነው ወር 4.5ሚልዮን መድረሱን ይፋ አድርጓል፡፡ የ2015 ግማሽ አመት የሰብአዊ ድጋፍ ተፈላጊነት ከተገመገመ በኋላ ሪፖርቱ ይፋ ሲደረግ ለጋሽ አገራትና የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዩች በስፍራው መገኘታቸውን መረጃው ጨምሮ ጠቁሟል፡፡ ሪፖርቱ በተጨማሪ ለምግብና ምግብ ነክ ላልሆኑ ነገሮች የሚያስፈልገው የእርዳታ መጠን በጃንዋሪ(ጥር)ወር ተተንብዮ ከነበረው […]

አርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ እንደዘገበው የባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 11 አባይ ማዶ ወጣቶች አንድ አካባቢ ላይ ተሰባስበው በመጫወት ላይ እያሉ ፖሊሶች ድንገት መጥተው “ለምን አንድ ላይ ተሰብስባችሁ ቆማችሁ?” በማለት አምባጓሮ በመፍጠራቸው ነበር ግጭቱ የተነሳው፡፡ ፖሊሶቹ ወጣቶችን ከቆሙበት በኃይል አባረው ወደየቤታቸው ለማስገባት ሲሞክሩ ወጣቶቹ በፖሊስ ላይ የአጸፋ እርምጃ በመውሰዳቸው አንድ ፖሊስ ለከፋ ጉዳት እንደተዳረገ ታውቋል፡፡ የህወሓት […]

የወያኔ መንግስት 3 ሊትር ዘይት በ72 ብር አቀርባለው ቢልም ከእጥረቱ በተጨማሪ ደረጃውን ያልጠበቀና ለምግብነት የማይውል መሆኑን ዘይቱን ያገኙ ሰዎች እየተናገሩ ነው። ከግለሰብ ሱቅ የ1 ሊትር ዘይት በ75 ብር እየተሸጠ ቢሆንም ይህም ከኮሌትሮል ነፃ ያልሆነ እና ለጤና ጠንቅ ነው።ይህ የተበላሸ ዘይት በጉምሩክ በኩል ከወያኔ ባለስልጣናት ጋር በሼር የሚነግዱ ነጋዴዎች እንዳስገቡት ለማወቅ ተችሏል።ይህን ዘይት መጠቀም ለጤንነት ጠንቅ […]

በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ከአየር ሀይል ከ40 በላይ ሰራተኞችና ባለሙያዎች በስልጣን ላይ ያለውን የወያኔ አገዛዝ በመክዳት ወደተለያዩ ቦታዎች መጥፋታቸው ታወቀ:: የአየር ሀይል የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ከደብረዘይት ጠቅላይ መምሪያና ከተለያዩ የአየር ሀይል ምድቦች የጠፉት ባለሙያዎች 14 ቴክኒሺያኖችን የሚጨምር ሲሆን አብራሪዎችም እንደሚገኙበት ታውቋል:: ለአንድ ወር በስራ ገበታቸው ያልተገኙትን እነዚህን ሰራተኞችና ባለሙያዎች ለመያዝ የህወሀት መከላከያ ሚኒስቴር አሰሳ እያደረገ […]

በከድር መሃመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱት ወጣት ወንድሞቻችን እና አንድ እህታችን፣ የቢላል ራዲዩ ጋዜጤኞች ካሊድ ሙሃመድና ዳርሶማ ሶሪን እንዲሁም በሐሰት አልመሰክርም በማለቱ ብቻ በእስር ላይ የሚገኘው ወንድም ሙጂብ አሚኖን ጨምሮ በአጠቃላይ 20 የሚሆኑ ሙስሊሞች ከ 5 ወር በፊት በደህንነት ኃይሎች ታፍነው በቅርቡ ከማዕከላዊ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት መዘዋወራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው ። እነዚህ ሙስሊሞች በቀጠሯቸው መሰረት […]

        በጥብቅና ሙያ የሚተዳደሩት አቶ ተማም አባቡልጉ አባዲኮን ከስነ ምግባር ጋር በተያያዘ በሚል ለ፩ አመት ከሰባት ወር የጥብቅና ፍቃዳቸውን ታግዳል። አቶ ተማም አባቡልጉ በግፍ ለታሰሩት ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጥብቅና በመቆም የወያኔን መሰሪ አሰራር ለአለም በማጋለጥ የሚታወቁ ሲሆን የካንጋሮ ፍርድ ቤት ፍርደ  ገምድልነት ቁልጭ ብሎ እንዲታይ ያደረጉ የሀገር አብት ጠበቃ ናቸው። ይህ ያልተመቸው […]

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና ሌሎች በተመሳሳይ መዝገብ የተካተቱ ተከሳሾች ላይ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለዛሬ ተከሳሾች በነጻ ይሰናበቱ ወይስ ይከላከሉ በሚለው ላይ ብይን ይሰጣል ተብሎ ተጠብቆ የነበር ቢሆንም ብይኑ ሳይሰጥ ተቀጥሯል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ፣ የአንድነት እና የዓረና ትግራይ አመራሮች የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ፣ ሀብታሙ አያሌው እና […]

ዛሬ በጥዋት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ሊሰጥ የተቀጠረውን ውሳኔ ተመልክቼ ለመዘገብ ልደታ በሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አምርቼ ነበር፡፡ 3፡30 ሰዓት ገደባ በታችኛው መግቢያ በር ጋር ስደርስ፣ ቁጥራቸው በዛ ያሉ፣ የሚሊተሪ ልብስ የለበሱ የጸጥታ ሃይሎች እና የአዲስ አበባ ፖሊሶች በፍርድ ቤቴ ቅጥር ግቢ በር ላይ ሆነው ሰዎችን በጥብቅ እየተፈሹ ሲያስገቡ አስተዋልኩ፡፡ በአጋጣሚ ከጠበቃ […]

በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ያስፈልጋቸዋል ወይስ በነጻ ይሰናበቱ የሚለው ላይ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 13/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ ዛሬ ሰኔ 8/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ልደታ ምድብ የቀረቡት ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ጥቁር ለብሰው ችሎት ፊት ቀርበዋል፡፡ መዝገቡ ለዛሬ ተቀጥሮ […]

ዎርልድ ጀስቲስ ፕሮጀክት የተባለው በአለም ላይ ፍትህና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እሰራለሁ የሚል ተቋም የ 102 የአለም ሀገራትን የፍትህና ህግ ስርአት ደረጃ ይፋ አድርጓል፡፡ ከተለያዩ ሀገራት ከ 100 ሺህ የማያንሱ ህዝቦችን መጠይቅ በማድረግ ጭምር የተጠናቀረው ይህ የተቋሙ ሪፖርት በዚህ ረገድ የኢትዮጵያችንንም ደረጃ ይፋ አድርጓል፡፡ … የፍትህና ህግ የበላይነት ጉዳይ ብዙ ጊዜ የህግ ሰዎች ስራ ብቻ ተደርጎ […]

የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ሚያዚያ 1/2007 ዓ.ም በብአዴን ኢህአዴግ ስርዓት የተለጠፈውን የምረጡኝ መቀስቀሻ ፖስተር በማየት ለውጥ ለማያመጣ ስርዓት አንመርጥም እያሉ እየቀደዱት መሆናቸውን ምንጮቻችን ገለፁ፣ በጎንደር ከተማ ቀበሌ 04 በኢህአዴግ የተለጠፈውን የምርጡኝ መቀስቀሻ ፖስተር በማየት ለውጥ ለማያመጣ ስርዓት አንመርጥም በማለት እየቀደዱት መሆናቸውን የገለፀው ይህ መረጃ በህብረተሰቡ ተግባር የተናደዱት የስርዓቱ ካድሬዎች ምንም አይነት ወንጀል ላልፈፀመ ዜጋ አንተነህ የለጠፍነውን […]

ኦህዴድ/ኢህአዴግ ዜጎችን በማሰርና በመደብደብ መጠመዱ ተነገረ የወያኔ /ህወሃት ካድሬዎች እርስ በራሳቸው እንደማይተማመኑ ተገለፀ በሁመራ አከባቢ ህወሀት እስከአሁን ከአንድ መቶ በላይ ኢትዮጵያውያንን ገድሏል የአሜሪካ ም/የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ዌንዲ ሸርማን አዲስ አበባ የተናገሩትን አስተባበሉ ወያኔ ከአቶ አንዳርጋቸው የረባ መረጃ ለማግኘት ባለመቻሉ የስነ ልቦና ጫና በማሳረፍና ህክምና በመከልከል ለመጉዳት ማሳቡን ምንጮች ገለፁ    የኖርዌይ አንባሳደር በኢትዮጵያ ዜጎቻቸውን አስጠነቀቁ የኖርዌይ ኢንባሲ በኢትዮጵያ […]

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኙት የብአዴን ኢህአዴግ አመራሮች ህዝብ አይመርጠንም የሚል ስጋት ስላደረባቸው ለህብረተሰቡ የማደናገርያ ቃል እየገቡለት መሆናቸውን ተገለፀ፣የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው- የብአዴን ኢህአዴግ አመራሮች በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኘውን ህዝብ በማዳበሪያ እዳ ተማርሮ እንደሚገኝ አስቀድመው ስለተረዱ ሱሪያችሁን በጭንቅላታችሁ አውጡ አይነት አስገዳች መመሪያ በመስጠት እያስጨነቁት እንዳልቆዩ አሁን ላይ ደርሰው ከህብረተሰቡ በርካታ ተቃውሞ ስላጋጠማቸው የወሰዳችሁትን […]

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ም/ ቤት የወጣቶች ጉዳይ ሰብሳቢ የነበረው በአሁን ጊዜ ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል በመሆን የወያኔን ስርዓት እየታገለ የነበረው # ስንታየሁ_ቸኮል ከመኖሪያ ቤቱ በር ገንጥለው በገቡ ፖሊሶችና የደህንነት ኋይሎች የፍርድ ቤት ማዘዣ ሳይዙ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመበት ወደ አልታቀቀ ቦታ ተወስዶዋል። ‪ስንታየሁ_ቸኮል‬ ለረጅም ዘመን በተቃውሞው ጎራ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የወያኔን ስርዓት ለመጣል […]

  ማምሻውን ፖሊሶችና ፌድራል ፖሊሶች ጨርቆስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በመግባት በምእምናን ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን ጉዳት የደረሰባቸው  ገለጹ ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የእምነት ቦታዎችን በማርከስ ከዚህ ቀደም በገዳማት በመስጅዶች ውስጥ በመግባት በምእምናን ላይ ድብደባ ሲፈጸም መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው እለት በጨርቆስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ድረስ በመዝለቅ ከፍተኛ ድብደባ መፈጸማቸውን በቦታው ላይ ድብደባ የተፈጸመባቸው  ገልጸዋል፡፡… በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ከሚስቱ ጋር እንደነበር […]

የወያኔ ወታደሮች ስርሀቱን በመክዳት ላይ መሆናቸው ተሰማ የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ለ10ኛ ጊዜ ተመለሰ የወያኔ ሰላዮች በማህበራዊ መገናኛዎች አማራና ኦሮሞን ሊያጋጭ ይችላሉ የተባሉ ክብረነክ ጽሁፎችን እንዲያሰራጩ ታዘዙ። ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳንን ተፋላሚዎች ከማስታጠቅ ጀርባ እጇ አለበት ተባለ የአል-ሻባብ ታጣቂዎች በኬንያ ጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ 147 ተማሪዎችን መግደላቸው ታወቀ በናይጄሪያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አሸነፋ   አሰግድ ታመነFiled under: NEWS Tagged: Addis […]

እርማችሁን አውጡ! ክፍል ሁለት ከባለፈው የቀጠለ ባለፈው ክፍል አንድ ሰፊ ንባባችን ርእሱ ጠብቀው የሚነሱ በርከት ያሉ የተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች እንስተን መወያየታችን የሚታወስ ነው። በዛሬ ዕለትም እንዲሁ ከባለፈው በመቀጠል ዋና ዋና ነጥቦች በማንሳት ጥቂቶቹን የምንዳስስ ሲሆን ከሁለትና ከሦስት ገጽ በላይ ጽሑፍ …

እርማችሁን አውጡ! (ክፍል ሁለት) ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል Read more »

ጉዳዩን ያጠኑ ድርጅቶችና ባለሙያዎች እንደሚሉት ግን ኢትዮጵያ ባጭር ጊዜ ዉስጥ ሙስና በተለይ የባለሥልጣናት ሙስና አለቅጥ ከተንሰራፋባቸዉ ሐገራት አንዷ …

–>ዋኤል ጎኔም የግብጽ ደኅንነት ሰዎች ደብድበው የገደሉትን ካሊድ ሰኢድ ለማሰብ ‹‹እኔም ካሌድ ሰኢድ ነኝ›› የተሰኘ የፌስቡክ ገጽ ከፍቶ ለግብጽ አብዮት ያበቃ ሰው ነው፡፡ የመጀመሪያውን የአደባባይ እንውጣ ጥሪ ያቀረበው ይኸው የፌስቡክ ገጽ ነው፡፡ ዋኤል አደባባይ የወጡበትን የመጀመሪያ ቀን (ጃንዋሪ 25) አንድ ዓመት ለማክበር (Revolution 2.0 የተባለ) መጽሐፍ አሳትሟል፡፡ የመጽሐፉ ገቢ በሙሉ በአብዮቱ ለተጎዱ ሰዎች መደጎሚያ እንደሚውልም ተነግሯል፡፡ አሁን እዚህ ልጽፍላችሁ ያሰብኩት ግን ዋኤል ገጹን እና የግል ማንነቱን አስመልክቶ ለሚቀርብለት ጥያቄ ይሰጥ የነበረውን መልስ ነው (መጽሐፉ ላይ እንዳሰፈረው)፤ ዋኤል ኢትዮጵያዊ ቢሆንና የከፈተው ገጽም ኢትዮጵያዊ ቢሆን ኖሮ… በሚል ምናባዊ ምሳሌ፡፡ ስለዚህ ጽሑፉ በዋኤል የተጻፈው በኢትዮጵያኛ ተተርጉሞ ነው ልትሉት ትችላላችሁ፡፡

ስምህ ማነው?
[1]ስሜ ሽብሬ ደሳለኝ ነው፤
[2]ስሜ ዩሱፍ አብደላ ነው፤
[3]ስሜ እስክንድር ነጋ ነው፤
[4]ስሜ ርዕዮት አለሙ ነው፤
[5]ስሜ አሕመዲን ጀበል ነው፤
[6]ስሜ አንዱአለም አራጌ ነው፤
[7]ስሜ በቀለ ገርባ ነው፤
[8]ስሜ ኦልባና ሌሊሳ ነው፤
[9]ስሜ መስፍን ነጋሽ ነው፤
[10]ስሜ አርጋው አሽኔ ነው፤
ስሜ…. ብዙ ነው፡፡
እኔ በጎዳና ላይ የተገደልኩ፣ ያለወንጀሌ የታሰርኩ፣ ያለሀጢያቴ የተገረፍኩ፣ መብቴን በፍርሐት የተነጠቅኩ፣ ከገዛ አገሬ የተሰደድኩ ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡
ዕድሜህ ስንት ነው?
ዕድሜዬ ይህን ያህል ነው አልልም፤ ነገር ግን ከተወለድኩ ጀምሮ ያለው ያው አምባገነን መሪ ነው፤… ሙስናውም ያው ነው፤…. ጭቆናው ያው ነው፤… እናም በአገሬ የገነነው የፖለቲካ ፓርቲ ‹‹ተስፋ የለም›› ይባላል፡፡
ከጠቀስካቸው ሰዎች ጋር ዝምድና አለህ?
እነዚህ ሰዎች የተኛውን ውስጤን ቀስቅሰውታል… ዕድሜ ለነርሱ አሁን ለውጥ ማምጣት እንደምችል ይሰማኛል፤… ታዲያ በራዕይ አልተዛመድንም ማለት ይቻላል?… አንድም ቀን አግኝቻቸው የማላውቃቸው እነዚህ ሰዎች ወንድሞቼ/እህቶቼ ናቸው፡፡
ይህንን የምታደርገው ለምንድን ነው?
ወገኖቼ ላይ የሚደርሰውን በደል ተመልክቼ ወደጥናት ክፍሌ ስገባ እምባዬን መግታት አልችልም፤… ፍርሐት የተጫናቸው ኢትዮጵያውያን ምን ያህል ውርደትን እንደሚታገሱ አየሁ… ከራሴ በመጀመር በፍርሐት የምሠራውን ስህተት ሁሉ ማረም ጀመርኩ፤ እናም ለዛ ነው ይህንን ገጽ የፈጠርኩት፡፡ ለተበደሉ ወገኖቼ ያለቀስኩት ለሞቱ ዘመዶቼ ካለቀስኩት በላይ ነው… በየዕለቱ ፎቷቸውን ስመለከት ድብታ ውስጥ እገባለሁ፤ ኢ-ፍትሐዊነትን እስከመጨረሻው ለመዋጋትም ለራሴ ቃል እገባለሁ፡፡
ማነው በገንዘብ የሚረዳህ?
ፈጣሪ ይመስገን፣ የገንዘብ ምንጮቼ ብዙ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ንቃተ ሕሊናዬ ነው… ይህ ምንጬ በቀን አራት ሰዓተ ብቻ እንድተኛ እና ጠዋትም ፊቴን ከመታጠቤ በፊት የፌስቡክ ገጼን እንድከፍት ያስገድደኛል፡፡

ሁለተኛው ምንጬ መማሬ ነው፡፡ በመማሬ ደስተኛ ነኝ፤ ዕውቀቴን አገሬን ለማገልገል አውለዋለሁ፡፡
ሦስተኛው ምንጬ የልጆች አባት መሆኔ ነው፡፡ ሁሌም የሚጨንቀኝ ልጆቼ አንድ ቀን ‹‹አባዬ፤ ዜጎች ሲጨቆኑ እያየህ አቅምህ የሚፈቅደውን ለምን አላደረግክም?›› ብለው ይጠይቁኛል ብዬ ነው፡፡
የመጨረሻው ምንጬ የሕዝብ ፍቅር ነው፡፡ አይቶኝ የማያውቅ፤ አይቼው የማላውቀው እና በስም የማንተዋወቀው ሕዝብ ፍቅር… በየዕለቱ የአመሰግናለሁ ማስታወሻ ይደርሰኛል…. የተለያዩ ዲዛይኖች፣ ሎጎዎች፣ ቪዲዮዎች ይልኩልኛል… ገጹ ብዙ ሰዎች ጋር እንዲደርስ ያስተዋውቁልኛል፡፡
ስለዚህ ምንድን ነው የምትፈልገው?
ይህንን ገጽ የፈጠርኩት ራሴን ከአደጋ ለመጠበቅ ብቻ አይደለም.. ነገር ግን አገራችን መልሳ የኛው የሕዝቦቿ እንድትሆን ከመፈለግ በላይ ሌላ ዓላማ የለኝም… አንድ ቀን እንዲህ ይሆናል ብዬ አልማለሁ፡- እርስ በእርስ ዳግም እንዋደዳለን፤ ሁላችንም ኢ-ፍትሐዊነትን እንቃወማለን፤ ከመሐከላችን ማንኛውም ሰው ክፉ ነገር ቢያይ ራሱ ይፈታዋል… እናም የመንግሥት ቅጥረኛ አንድን ዜጋ በጥፊ ከመምታቱ በፊት አንድ ሺሕ ጊዜ ያስብበታል፡፡
አትፈራም?
በጣም እፈራለሁ እንጂ፤… ፍርሐት እኮ የሰው ልጅ ተፈጥሮ ነው… ለተጨቆኑ ዜጎች የሚቆረቆር እንደእኔ እና እናንተ ያለ ሰው ግን ካለ ፍርሐቴ ይከስማል… ዕጣፈንታችንንም የምንወስነው እኛው ራሳችን እንሆናለን… እንዲህ እያልን፡- ‹‹ማንም ያለዕድሜው አይሞትም፣ ማንም ያለወንጀሉ አይታሰርም፣ ማንም አገሩን ለቅቆ አይሰደድም…›› አንድ ዘመዴ በ25 ዓመቱ ሞተ… ቁም ነገር ካልሠራሁበት የኔ ዕድሜ መርዘሙስ ምን ዋጋ አለው?
ብዙ ሰዎች ይህንን ለማመን ይቸገራሉ፤ እውነቱን ለመናገር ቃሉ የወጣው ከልቤ ነው… አገሬን ከልቤ እወዳታለሁ እናም በተሻለ ሁኔታ የምንኖርባት አገር እንድትሆን እፈልጋለሁ፡፡ መፈንቅለ መንግሥት ወይም አብዮት የማቀጣጠል ዓላማ የለኝም… እራሴን እንደፖለቲካዊ መሪም አልቆጥርም… ዋሊያዎችን እና ሉሲዎችን የሚደግፍ፣ ካፌ ደጃፍ ላይ ቁጭ ብሎ ተቆራጭ እየበላ፣ ማኪያቶ እየጠጣ ጋዜጣ የሚያነብ ተራ ዜጋ ነኝ፡፡… የሚከፋኝ ብሔራዊ ቡድናችን በሰው አገር ሲሸነፍ ነው፡፡ … ቁምነገሩ በኢትዮጵያዊነቴ መኩራት እፈልጋለሁ፡፡… ማንም ሰው የዜግነት ክብሩን ተገፍፎ እንዲጨቆን አልፈልግም፡፡ ይኸው ነው ምኞቴ፡፡
—-
[1] – ሽብሬ ደሳለኝ፤ ምርጫ 97ን ተከትሎ በተነሳው ብጥብጥ የመንግሥት ጥይት ሰለባ የሆነች ወጣት ተማሪ፤ [1] – ዩሱፍ አብደላ፤ በተመሳሳይ ወቅት የተገደለ የኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ተማሪ፤
[3] – እስክንድር ነጋ፤ በሽብርተኝነት ተከሶ የተፈረደበት ጋዜጠኛ፤
[4] – ርዕዮ ዓለሙ፤ መረጃ ለሽብርተኞች አቀብለሻል በሚል የተፈረደባት ጋዜጠኛ፤
[5] – አሕመዲን ጀበል፤ በሙስሊሞች የመጅሊስ ይቀየር ጉዳይ የታሰረ፣ ጋዜጠኛ እና ደራሲ፤
[6] – አንዱአለም አራጌ፤ ሽብር አሲረሃል በሚል የተፈረደበት የአንድነት ፓርቲ አባል፤
[7] – በቀለ ገርባ፤ ከኦነግ ጋር ግንኙነት አለህ በሚል የተፈረደበት የኦፌዴን ም/ሊቀመንበር፤
[8] – ኦልባና ሌሊሳ፤ ከኦነግ ጋር ግንኙነት አለህ በሚል 8 ዓመት የተፈረደበት የኦብኮ አባል፤
[9] – መስፍን ነጋሽ፤ በሽብርተኝነት አዋጅ/ክስ ምክንያት ከተሰደዱ የቀድሞዋ አዲስ ነገር ጋዜጠኞች አንዱ፤
[10] – አርጋው አሽኔ፤ የመረጃ ምንጩን እንዲሰጥ በመንግሥት ኃይሎች በግዴታ በመጠየቁ የተሰደደ ጋዜጠኛ፤

የተስፋይቱ ምድር ተስፋ እኛ “ወንድማማቾች ነን”  ውድ ኢትዮጵያዊያንና ይሁዲ ወገኖቻችን እኛ ኢትዮጵያዊ- እስራኤላዊያን ይሁዲዎች በሁሉም ዘርፍ ጠንክረን በብቃት ለመገኘትና በሁሉም አቅጣጫ ያለንን እምቅ ዕውቀትና ኃይል በማስተባበር በአንድነት በመቆም መብታችንን ከማስከበር አልፎ በማናቸውም በአገራችን በእራኤል ባሉ ከፍተኛ የሥራ አመራር መስኮች ላይ …

የተስፋይቱ ምድር ተስፋ እኛ “ወንድማማቾች ነን” Read more »

ርዕዮት ዓለሙ ከዚሕ ቀደም የበታች ፍርድ ቤት አስራ-አራት ዓመት እስራትና የገንዘብ መቀጮ በይኖባት ነበር።ይግማኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ግን ቅጣቱን ወደ አምስት-ዓመታት እስራት ዝቅ አድርጎታል።ርዕዮት ዓለሙ ለሰበር ሰሚዉ ችሎት አቤት ያለችዉ የአምስት ዓመቱ እስራትም የሕግ አተረጓገም ክፍተት አለበት በሚል ነበር የጋዜጣ …

የርዕዮት ዓለሙ ክስና የጠበቃዋ ተቃዉሞ Read more »

እንዲህ ያለ ዘመን ፣ዘመነ ጋንድያ፤ ሰው እንዴት ይሆናል፣ ከርሞ እንዳ ጥጃ፤ በሃገራችን ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ይገለፃል። ይህንንም ለማስቆም በትምህርቱ ዓመት መጀመሪያ ላይ የተመዘገቡትን ተማሪዎች ቁጥር መምህራን ተረክበው በዓመቱ መጨረሻ ማስረከብ እንዳለባቸው ለመፍትሔነት ቀርቧል። መምህራንም የደረጃ እድገት፣ የደመወዝ ጭማሪ ለማግኘት የተረከቧቸውን ተማሪዎች ቁጥር ሳይቀነሱ ማስረከብ እንደሆነ ተገልጿል። ይህን ዓይነት ቁጥጥር በሰሜን ኮሪያ ‘labor […]

በጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ላይ የበታች ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ማፅናቱ ያሣዘናቸው መሆኑን ዓለምአቀፉ የሴቶ

የሰው ልጅ ላይ ሊፍጸም የማይገባው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት የመን ውስጥ ባሉ የተደራጁ አፋኞች ዜጎቻችን ላይ እየተፈጸመ ነው፡፡ ሰኞ ታህሳስ 29 ቀን በዓልን በገመድ ታንቀው ሲደበደቡ ከነበሩ እና ከሞት ተርፈው ሰነዓ ከገቡ ልጆች ጋር አሳለፍኩ፡፡ ሰውነታቸው ላይ በድብደባ ያረፈውን ቁስል እያየን አንገታቸው ላይ ገመዱ የከረከራቸው ምልክት ሰቅጥጦን ከሞት እንዴት እንደተረፉ እያወጉን በእንባ ታጅበን አሳለፍን፡፡ በዓልን ለማክበር ሁሌም […]

እርማችሁን አውጡ! ክፍል አንድ መሪ ጥቅስ: “ትቶአቸውም ከከተማ ወደ ቢታንያ ወጣ በዚያም አደረ በማለዳም ወደ ከተማ ሲመለስ ተራበ በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና። ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች። ደቀ መዛሙርቱም ይህን …

እርማችሁን አውጡ! (ክፍል አንድ) ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል Read more »

ከጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወት በኋላ ባለፈዉ መስከረም ወር አጋማሽ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ስልጣን ሲይዙ ፤ የ

ኢንፍሌሸንን ሊያመጡ ከሚችሉ መንስኤዎች መካከል ፈጣን የ ኢኮኖሚ እድገት ኣንዱ እንደሆነ የሚስማሙ ምሁራን በርግጥ ኣሉ። ኣንዳንድ ምሁራን ደሞ ኢንፍሌሽንን እድገት ሊያመጣው ኣይችልም ብለው ይናገራሉ። የ ሁለቱ ልዩነት ያረፈበት ነጥብ የሚመስለው ኢንፍሌሽን የሚለውን ጽንሰ ሃሳብ ባዩበት ወሰን ላይ ነው። የ መጀመሪያው …

ትዳርን የማሸነፍ ኣቅም ማጣት እድገትን ተከትሎ ኣይመጣም Read more »

በዚህ ጦማር ላይ ከጻፍኩ ሰነበትኩ:: ነገር ግን ብዙዎቻችሁ እንደምታውቁት የጠፋሁት መጻፍ እርም ብዬ ሳይሆን ዞን ዘጠኝ ላይ መጻፍ በመጀመሬ ነው:: ታዲያ ምና

ጋዜጠኛ ጳዉሎስ ኞኞ በህይወት ዘመኑ ለአንባብያን ያበረከታቸዉ ሥራዎች ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ተበረከተ።

ከትናንት ከሰአት በኋላ አንስቶ እስከ ዛሬ ጠዋት በቀጠለው ግጭት ተማሪዎች እንደቆሰሉና በተማሪዎች መኝታ ክፍሎች ላይም ጉዳት መድረሱን የአይን ምስክሮች

ማንን እንመን? ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን በማን እጅ ነች? በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ሳምሶን መኮንን ከዳላስ December 14, 2014 ለሥጋችንና ለነፍሳችን በምሳሌነት የሚጠቅም ስራ ሰርተው ሊያሳዩን ይችላሉ ተብለው የመጨረሻውን የስልጣን ልጓም የጨበጡትን መንፈሳውያንንና  ሥጋውያን መሪዎች  በዚህ ሰሞን የተናገሩትን ሰማን። የተጻፈውንም አነበብን። …

ማንን እንመን? ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን በማን እጅ ነች? Read more »

የሰው ልጅ በባህሪው ንጹሕ ፍጥረት ለመሆኑ ምንም አያጠያይቅም። ከልደት በኋላ ህይወት የማይገኝበት ኃይማኖት ጨምሮ በተለያዩ ውጫዊ ተጽዕኖዎች ራሱ “እኔ” ሲል የሚገልፀው/በሚቀርጸው ማንነት ግን ስብዕናው ከእውነት ይልቅ ሁለመናው ለሐሰት/ለስህተት እጅግ ቅርበት ያለውና በእንግዳ ነፋስ ለመወሰድም ጊዜ የማይፈጅበት ፈጣን ፍጥረት ለመሆኑ አንባቢ …

ጽንስ የሚያጨናግፍ ወረተኛ ምላስ! ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል Read more »

ይህን ኣባባል ስንቀባበል የኖርነው ያለ ምክንያት ኣልነበረም። ሃገራችን ብዙህነቷ የሚገለጸው በ ቋንቋና በ ባህል ብቻ ሳይሆን በ ሃይማኖትም በመሆኑ ነው። ብሂሉ ተቻችለን መኖር እንዳለብን ቃል የምንገባበት፣ የሃይማኖት ነጻነታችን የ ግል ሆኖ ኣገራችን ግን የሁላችን መሆኑዋን የምናጸናበት ኪዳን፣ የ ኣንድነት ጉዟችን …

ሃይማኖት የግል ሃገር የጋራ ነው Read more »

በዳላስ የተካሄደው የሁለቱ የሲኖዶሶች እርቀ ሰላም ውይይት ያለተጨባጭ ውጤት ተጠናቋል በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ ሳምሶን መኮንን ከዳላስ December 9, 2012 ለፓትርያርክነት ዕጩ ተወዳዳሪ በሆኑት በአቡነ ገሪማ የሚመራው የአዲስ አበባው ሲኖዶስ መልዕክተኞች ቡድን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ “በመረጡት ቦታ በጸሎት …

በዳላስ የተካሄደው የሁለቱ ሲኖዶሶች እርቀ ሰላም ውይይት ያለተጨባጭ ውጤት ተጠናቋል Read more »

በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል የዕርቅ ውይይት በአሁኑ ጊዜ በዳላስ ከተማ ውስጥ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ይህንን አስመልክቶ ከወያኔ ከፍተኛ ሹማምንት ደብዳቤ መጻፉ ታውቋል። ይህንኑ እራሱ አስረጅ የሆነውን ደብዳቤ ከዚህ በታች ይመልከቱ። ዝርዝር መረጃዎችንና ትንተናዎችን በቅርቡ አናወጣለን።        

ስለ እውነት፤ እውነት የት ነው? የዛሬን አያድርገውና የጥንታዊቷ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እውንተኛ ሊቃውንት ስለነገረ መለኮት የሰጡት ምስክርነትና እውነት ጊዜና ታሪክ የማይሽረው ዛሬ አንዳንዶች ሊያስተካክሉትና ሊገለብጡት ቢሞክሩም እውነተኛ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ግን አረጋግጠውት ወንጌል የሚያስከፍለውን የደም ዋጋ እየከፈሉ አልፈዋል። የእነኛን እውነተኛ …

ስለ እውነት፤ እውነት የት ነው? Read more »

ጽሁፉን በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።  “እግዚአብሔር የቀባው” “እግዚአብሔር የቀባው” ቀሲስ አስተርአየ ሕዳር ፳፩ ቀን ፪ሽ፭ [email protected] “እግዚአብሔር የቀባው” የምትለውን አነጋገር ብዙ ሰው በተደጋጋሚ ይናገራታል። ከየት መነጨች? ጠቀመች? ወይስ ጎዳች? ሊቃውንቱስ እንዲት ይተረጉሟታል? ነቢዩ ዳዊት ባንድ ወቅት “እግዚአብሄር በቀባው ላይ …

“እግዚአብሔር የቀባው” Read more »

በተጠቃሹ “የዜና” ማሰራጫ ማዕከል ስራዎች ዙሪያ ስጽፍ ይህ የመጀመሪያዬ አይደለም። በተለያዩ ጊዜያት ማዕከሉ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን በተመለከተ የሚያሰራጫቸው ሚዛናቸው የሳቱና ግልጽነት የሚጎድልባቸው ዘገባዎቹንና ሐተታዎቹን በማስመልከት ተደጋጋሚ ጽሑፎች ለንባብ መብቃታቸው የሚታወስ ሆኖ በርካታዎቹ ሃያ አራት ሰዓት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ከስፍራቸው እየተነቀሉ ለአንባቢያን እንዳይደርሱ …

ምን ነው ኢሳት ኸይ! የሚል የጠፋ – ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል Read more »

በ ለምለም ፀጋው ወይ ነውር አይገዛው አምልኮት ዓልነካው፤ የኢትዮጵያን ሰው ሁሉ በቃሊቲ አጎረው። ይድነቃችሁ ብሎ በየሱስ ስም ማለ፤ የመለስን ወንጌል እንደ ክታብ አርጎ በአንገቱ ሰቀለ።         ለሁሉም ለመሆን         አዲሱ ምንስቴር በቃሊቲ ሳይቀር፤         አርብ ሰኞ ሳይል         አለ ዓላህ …

ማን ጸሎት ያሳርግ Read more »

አዲስ አበባ 125ኛ ዓመቷን እያከበረች ነው፡፡ በከተማይቱ ልደት ሰሞን እናትና አባቷ (በመናገሻ ከተማነት የቆረቆሯት አጤ ምኒልክ እና ስሟን ያወጡለት እቴጌ

በዲሲ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ጣሊያንና ቫቲካን ኢምባሲዎች ፊትለፊት በመገኘት እ.አ.አ. በ1930ዎቹ ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ላይ ጭፍጨፋ ለፈጸመው ሮዶልፎ ግራዚያኒ የመታሰሰቢያ ቤተመዘክርና የመናፈሻ ቦታ መሰየሙን በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። ግራዚያኒ በዓለም አቀፍ …

ለግራዚያኒ ሀውልት መቆሙን የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ በዲሲ ተካሄደ Read more »

እስራኤል በርካታ እግዚአብሔር የሚያስከፉ ከጠየቃቸው ጥያቄዎች መካከል ሳሙኤል በሸመገለ ጊዜ ንጉሥ ስጠን በማለት ያቀረቡት ጥያቄ ተጠቃሽ ነው። ይህን የእስራኤል አሳብና ጥያቄም እግዚአብሔር ክፉኛ እንዳሳዘነና ለጥያቄአቸውም በእስራኤል ሁሉ ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ አህያ ፍለጋ የወጣውን የቢንያማዊው የቂስ ልጅ ሳዖል ንጉሥ አድርጎ …

ዓይነ መርፌው የጠፋበት ሲኖዶስና ሴራዎቹ: ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብኤል Read more »

ከህጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ መግለጫውን በሙሉ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ ይህንን ይጫኑ።  የኢ.ኦ.ተ.ቤ. ህጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ

ለቅዱስ ፓትሪያሪክ መርቆሪዎስ በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፥ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል! ቅድመ ሐተታ በይድረስ የተጻፈውን ደብዳቤ ከመልዕክቱ ተቀባይ ከቅዱስ ፓትሪያሪኩ አልፎ ለአንባቢያን በግላጭ ማቅረብ ያስፈለገበት ዋና ምክንያት ቅዱስነታቸው ፊት ለፊት አፍጥጦ የሚጠብቃቸው በሁለቱም የሃይማኖት መሪዎች መካከል ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀውን ቅራኔ …

ለቅዱስ ፓትሪያሪክ መርቆሪዎስ – ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል Read more »

(ሙሉውን ጽሁፍ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

ለሞት እንዳልተኛ ዓይኖቼን አብራ! መጽሐፉ ምንም እንኳን የዛሬ አንድ ዓመት ከሦስት ወራት በፊት ሙሉ ዝግጅቱ ተጠናቅቆ ወደ ማተሚያ ቤት አምርቶ የነበረ ቢሆንም በአንዳንድ ምክንያቶች የሕትመት ሂደቱ ተቋርጦ አንዲዘገይ ግድ ብለዋል። በዚህ ቆይታ መካከል መጽሐፉ በአራት የሥነ መልኮት መምህራን፣ የሥነ ጽሑፍና …

አዲስ መጽሐፍ ከዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል Read more »

በኣረብ ኣገራት ለግርድና የሚሄዱትን እህቶቻችንን የሚደርስባቸውን ስቃይ መናገር መነሻዬ ኣይደለም። ያልፍልኛል፣ እናት ኣባቴን እጦራለሁ እያሉ ወደ ሊባኖስና ሌሎች የኣረብ ገልፍ ኣገራት የሚጎርፉት እህቶቻችን ከሰባዊነት ደረጃ ዝቅ ብለው ሲሰቃዩ ሌላው በተለያየ የኣለም ክፍል ያለው ኢትዮጵያዊ ከንፈሩን ከመምጠጥ ያለፈ ብዙ ነገር ሲያደርግ …

ለ እህቶቻችን ልንደርስ የምንችልባቸው 4 መንገዶች! Read more »