የተቃውሞ ፓርቲዎችና የምርጫ ቦርድ እሰጥ አገባ
በመጪው ግንቦት የሚካኼደው የኢትዮጵያው 5ኛው አጠቃላይ ምርጫ የተወሰኑ ወራት ብቻ ናቸው የቀሩት።
በመጪው ግንቦት የሚካኼደው የኢትዮጵያው 5ኛው አጠቃላይ ምርጫ የተወሰኑ ወራት ብቻ ናቸው የቀሩት።
የፈረንሳዩ ምጸታዊ ጋዜጣ «ቻርሊ ኤብዶ» ነብዩ መሐመድ ላይ የሚሳለቅ ምስል በገፁ ላይ በድጋሚ ካወጣ በኋላ በዓለም ዙርያ በሚገኙ የሙስሊም ሃገራት ከፍተኛ ተቃዉሞ አጭሯል። በኒጀር ዚንደር ከተማ በሚገኝ አንድ የፈረንሳይ የባህል ተቋም እና ሦስት አብያተ ክርስትያናት ላይ የእሳት ቃጠሎ ጥቃት ደርሶ አራት ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል።
ለሳምንታት የዘለቀ ደም አፋሳሽ አመፅ መካከለኛው አፍሪቃ የምትገኘው ሀገር፤ ብሩንዲን አጨናንቋል።የሀገሪቱ ጦር ከአማፂያን ጋር እየተታኮሰ በርካታ ሰዎች መሞታቸውም ተረጋግጧል። ከዚህም በተጨማሪ ማንነታቸው ያልታወቁ እና የወታደር የደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች በርካታ የመንግሥት ፓርቲ አባሎችን መግደላቸው ተሰምቷል።
በውነህ ስለሺ ለኪነ ጥበብ ልዩ ፍቅር አለው፤ የተሰማራው ግን በቀለም ሙያ ነው። ለምን? ይገልፅልናል።
በእስር ላይ የሚገኘው የሳውዲ አረቢያው የኢንተርኔት አምደኛ ራይፍ በደዊ ህዝብ በተሰበሰበት ዛሬ ሊገረፍ የተያዘው ቀጠሮ ለሌላ ጊዜ መተላለፉን መንግሥት አስታውቋል ።
ሰዎች በሚገለገሉበትና በሚያዘወትሩት አካባቢ ትምባሆ ማጨስ በበርካታ ሃገራት መከልከል ከተጀመረ ከታራረመ። በኢትዮጵያም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ይህን መሰል ዉሳኔ ማሳለፉ ተሰምቷል ተግባራዊነቱ ቢዘገይም።
እስላማዊ አሸባሪዎች በቤልጂየም የፖሊስና ሌሎች ተቋማት ላይ ሊያደርሱት የነበረዉን ከፍተኛ የተባለ የሽብር ጥቃት የቤልጂየም ፖሊስ ትናንት ማምሻዉን አስታወቀ።
ከአራት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በናይጀሪያ የምክር ቤት አባላትና ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ይካሄዳል ። በአሁኑ ጊዜ በሽብር ማዕበል በምትናወጠው በናይጀሪያ ምርጫ እንዴት ሊካሄድ ይችላል የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል ።በምርጫው ዋዜማ በናይጀሪያ አሳሳቢው የፀጥታ ችግር ብቻ አለመሆኑን የዶቼቬለዋ ሽቴፋኒ ዱክሽታይን ዘገባ ያስረዳል ።
ድርጅታቸዉ ለዕቅዱ ማስፈፀሚያ ከ420 ሚሊዮን ብር በላይ መድቧል።አንጋፋዉ ግብረ-ሠናይ ድርጅት በሙስና ሠበብ ነባር ለጋሾቹ ሸሽተዉታል የሚለዉን ዘገባም ሐላፊዉ አስተባብለዋል
በጀርመን የኤርትራ ማሕበረሰብ አባላት ግፊት ካደረጉ በሕዋላ ግን ወጣቱ በሰዉ እጅ መገደሉን ፖሊስ አምኗል
ከተመሰረተ ከ10 ዓመት በላይ የሆነዉ የ«ኢትዮ ኮለኝ የስፖርትና የባህል ማሕበር» ዓመታዊዉን ባህላዊ መድረክ ሲያዘጋጅ ይህ ለሁለተኛ ግዜ መሆኑ ነዉ። በኖርዝ ራይን ዊስት ፋልያ እንዲሁም አቅራቢያ ግዛቶች ዉስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የተሰባሰቡበትን ባህላዊ መድረክ ቃኝተን በዕለቱ ዝግጅታችን ይዘን ቀርበናል።
ወጣቶች የራሳቸዉን ሕይወት ራሳቸዉ ለመምራት በሚሞክሩበት ጊዜ አንዳንዴ ነገሮች በትክክለኛዉ መንገድ ላይሄዱ ይቻላሉ። ልክ ሽቴፊ እንደሆነችዉ ማለት ነዉ።
የደቡብ ሱዳን የተራዘመ ጦርነት በሀገሪቱ እና በአጎራባች ሃገራት ላይ የሚያስከትለዉን የኤኮኖሚ ወጪ የመዘነ ዘገባ ቀረበ። እንደዘገባዉ የደቡብ ሱዳን የእርስ በርስ ግጭት በዚህ ይዞታ ከአንድ እስከ አምስት ዓመታት ከቀጠለ ከ22,3 እስከ 28 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር አዲሲቱን ሀገር ያሳጣታል።
የዕለቱ ዜና
ሰነዓ-የመን የሚገኘዉ ተባባሪ ዘጋቢያችን ግሩም ተክለ ሐይማኖት እንደሚለዉ ግን ለፓሪሱ ጥቃት ሐላፊነቱን የወሰደዉ የዓረቢያ አል-ቃኢዳ የተሰኘዉ ቡድን እንጂ የየመኑ አይደለም
አመቺ፤ በውጪም፤ ቀለል በሚለው የፀሐይ ኃይል ላይ ያተኮሩ አገሮች ቁጥር በሚያስደንቅ ፍጥነት በማደግ ላይ ይገኛል። እ ጎ አ በ 2014 ዓ ም ብቻ፤ በ 20 ከመቶ ነው ያሻቀበው። ይኸው ታዳሽ የኃይል ምንጭ፣ የወደፊቱ ዋንኛ የሥነ ቴክኒክ ፀጋ ያህል
ቦኩ ሐራም ልጃገረዶችን ለእጥፍቶ ጠፊነት ማዝመቱን መንታ ድል እንደሚያስገኝለት ሥልት ነዉ የሚቆጥረዉ።አንደኛ «ሴቶችም ይዋጋሉ» እያለ ወጣቶች ዓላማዉን እንዲቀበሉ መቀስቀሻ ያደረገዋል።ሁለተኛ ቡድኑን ይበልጥ ተፈሪ ያደርገዋል።
በጀርመኗ ቢለፌልድ ከተማ ዛሬ ማምሻዉን የኢትዮጵያ የባህል የሙዚቃ ድግስ ይካሄዳል። የሙዚቃ ድግሱ WDR በተሰኘዉ የጀርመን ራዲዮ በሀገሩ አቆጣጠር ከምሽቱ ሁለት ሰዓት እስከ አራት ሰዓት በቀጥታ የሙዚቃ ድግሱ ከሚካሄድበት አዳራሽ ይሰራጫል።
የውስጥ ችግሮቻቸውን ጉባኤ ጠርተው እንዲፈቱ ማሳሰቢያ ለሰጣቸው ለመኢአድና ለአንድነት ፓርቲዎች የተባሉትን እንዲያደርጉ ተጨማሪ ጊዜ እንደተሰጣቸው አስታውቋል ።
ባለፈው ሳምንት ፓሪስ ፈረንሳይ ውስጥ የተፈፀመው የሽብር ጥቃት በመላ አውሮፓ የፀጥታ አጠባበቅ ጉዳይ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው አድርጓል ።
የመተንፈሻ አካላትን ከሚጎዱ ሕመሞች አንዱ አስም ነዉ። የበርካቶች የጤና ችግር እንደሆነ የሚነገርለት አስም መንስኤዉ በትክክል ይህ ነዉ ተብሎ እንደማይታወቅ የሕክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ።
በሱዳን የሚኖሩ ስደተኞች የመኖሪያ ፈቃዳቸውን ለማሳደስ አለመቻላቸውን ተናገሩ። በዚህም ምክንያት ለእስር እና እንግልት መዳረጋቸውን በሱዳን በስደተኝነት የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን አስረድተዋል።
የፈረንሳይ ካቢኔ በወሰነዉ መሠረት በመላ ሐገሪቱ የሚገኙ 717 ምኩራቦችና የአይሁድ ትምሕርት ቤቶች ጥበቃ እንደሚደረግላቸዉ ሚንስትሩ አስታዉቀዋል።4700 ወታደሮችና ፖሊሶች ለጥበቃ መሰማራታቸዉንም ሚንስሩ ገልጠዋል።
ፓሪስ ተሸበረች። ዓለም ደነገጠ። ግድያ፤ ሽብሩን አወገዘ። አዘነም፤ ብዙዉ «እኔም ሻርሊ ኤብዶ ነኝ» አለ። ሌሎች ግን «ፍቅር ያሸንፋል።»
የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትና አንድነት ለዴሞክራሲና ፍትሕ ፓርቲ ፣ ትናንት አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አካሄዱ። ምርጫ ቦርድ በጽሑፍም ሆነ በሌላ መንገድ እኛን ሳያሳውቅ ውሳኔዎቹን በመገናኛ ብዙኀን የሚያሳውቅበት አካሄድ ቅር አሰኝቶናል በማለት ቢገልጹም ፤
አትሌቲክስን፣ እግር ኳስን እና የዝውውር ዜናዎችን የሚመለከቱ ዘገባዎች ቅኝት ተደርጎባቸዋል። የፊታችን ቅዳሜ ስለሚጀምረው የአፍሪቃ ዋንጫ ጨዋታዎች እና ፕሬሚየር ሊግን ጨምሮ በአውሮጳ ስለተከናወኑ ግጥሚያዎች ዳሠሣ ይኖረናል።
ፈረንሳይ ውስጥ በሽብር ጥቃት የተገደሉትን 17 ሰዎች ለማሰብ በሳምንቱ መጨረሻ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ በፓሪስ አደባባይ ተገኝቶ ሃዘኑን፤ አንድ መሆኑን አሳይቶአል።
ከአዲስ አበባ እስከ ታንዛኒያዋ አሩሻ ከተማ በዘለቀው የደቡብ ሱዳን የአንድ ዓመት የድርድር ሂደት የተኩስ አቁም ለማድረግ እና የሽግግር መንግስት ለመመስረት የተደረጉ ስምምነቶች ተግባራዊ መሆን አልቻሉም። በምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለ ስልጣን- ኢጋድ የሚመራው ድርድር በዚህ ሳምንት መጨረሻ እንደገና ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።
በፈረንሣይ ዋና ከተማ ፓሪስ ባለፉት ጥቂት ቀናት በሽብር ጥቃት የተገደሉ 17 ሰዎችን ለማሰብ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አደባባይ መውጣታቸው ተዘገበ። ሠልፉ የተጀመረው በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች ቤተሰቦችን ከዓለም ዙሪያ የተሰባሰቡ ፖለቲከኞች ከኋላቸው በፀጥታ በመከተል ነበር።
በአዲስ አበባ የመኪና ጋራዦች፤ነዳጅ ማደያዎች እና ፋብሪካዎች በመበራከታቸው ለከተማዋ ወንዞች ችግር ሆኗል። ተረፈ-ምርታቸውን እና ፍሳሻቸውን ወደ ወንዞቹ በመልቀቅ እንደሚበክሉም ይነገራል።
እቴጌ ጣይቱ ሆቴል የመጀመሪያው ዘመናዊ የኢትዮጵያ ሆቴል ሲሆን የተመሰረተው እ.ኢ.አ. በ ነሐሴ 1898 ዓ.ም ነበር። ይህ ሆቴል ዛሬ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ደረሰበት
ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ የእቃ ማመላለሻ አውሮፕላን ዛሬ ጋና መዲና አክራ ውስጥ ለማረፍ በሚያደርገው ሙከራ የመንሸራተት አደጋ እንደገጠመው የፈረንሳይ ዜና ወኪል ዘገበ።
የሼል ኩባንያ በናይጄሪያ የነዳጅ ማስተላለፊያ ተሸንቁሮ ላደረሰው ጉዳት ለመጀመሪያ ጊዜ ካሳ ለመክፈል ተስማምቷል። በዚሁ ሳምንት ራሱን የጌታ ተከላካይ ጦር (Lord’s Resistance Army ) ብሎ ከሚጠራው የዩጋንዳ አማጺ ቡድን የጦር መሪዎች መካከል ዶሚኒክ ኦንግዌን እጁስ ሰጥቷል።
ከትናንት በስቲያ ፓሪስ ውስጥ፣ በተፈጸመው የሽብር ተግባር ሳቢያ ፣ ድንጋጤ፣ ንዴትና ሐዘን ተፈራርቀዋል። ሻርሊ ኤብዶ የተባለው አሥቂኝ ስዕሎችን («ካርቱንስ»)መሠረት ያደረገ የምፀትና ሥላቅ መጽሔት በሚዘጋጅበት ማዕከል አሸባሪዎች ሰተት ብለው ገብተው
ፓሪስ ፈረንሳይ ውስጥ፤ ሻርሊ ኤብዶ በተሰኘው በአሥቂኝ ስእሎች የታጀበ የምጸትና ሥላቅ መጽሔት ዝግጅት ባልደረቦችና በሁለት ፖሊሶች ላይ የተፈጸመው ግድያ ፣ ምዕራቡን ዓለም ብቻ ሳይሆን የአፍሪቃውን ክፍለ ዓለምም ማሳዘኑ ተነግሯል። የፓሪሱ
አንድነት የተጠየቀውን አሟልቶ ማሳወቁን ሆኖም መልስ ሳያገኝ በመገናኛ ብዙሃን ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ይናገራል። የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አንድነት ለዲሞክራሲና ፍትኅ ፓርቲ (አንድነት) እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በውሳጣቸው ያለውን አለመግባባት በሕጋዊ መንገድ ካልፈቱ ርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠንቅቋል።
በፈረንሣይ መዲና ፓሪስ «ሻርሊ ኤብቶ» የተሰኘው የስላቅ ጋዜጣ ዋና ጽ/ቤትን ፓሪስ ውስጥ በመውረር ግድያ የፈፀሙት ኹለት ወንድማማቾች መገደላቸው ተዘገበ። በፓሪስ ስተምሥራቅ አንድ የአይሁድ ሱፐርማርኬት ውስጥ ዛሬ ሌላ የሽብር ጥቃት በመሰንዘር ቢያንስ ኹለት ሰዎችን እንደገደለ የተጠቀሰው የሽብር ተጠርጣሪም መገደሉ ይፋ ሆኗል።
መምህርት ሰብለ ሽፈራው እና መምህር ታምራት ታደሰ
በፈረንሣይ መዲና ፓሪስ ትናንት የተጣለዉን የአሸባሪዎች ጥቃት ተከትሎ የተለያዩ የዓለም መንግሥታትና ፖለቲከኞች ድርጊቱን በፅኑ ማዉገዛቸዉን ቀጥለዋል።
የአሸባብ ታጣቂ ቡድን ለአሜሪካን፤ ኢትዮጵያና የሶማልያ ደህንነት ተቋም ሲሰልሉ ነበር ያላቸውን አራት ሰዎች መግደሉ ተዘገበ። ታጣቂ ቡድኑ ባርድሬ በተባለችው የሶማልያ ከተማ በአደባባይ አይናቸውን በማሰር መረሸኑን የፈረንሳዩ ዜና ወኪል ኤ.ኤፍ.ፒ ዘግቧል።
በመጭዉ ግንቦት ወር በኢትዮጵያ በሚካሄደዉ ምክር ቤታዊ ምርጫ የአዉሮጳ ሕብረት የምርጫ ታዛቢዎችን የማይልክ መሆኑ እየተገለፀ ነዉ።
በኢትዮጵያዉያን ዘንድ የበዓላት ሁሉ በኩር የሆነዉ የልደት ማለት ገና በዓል ትናንት በደማቅ ተከብሮ ዉሎአል። በኢትዮጵያ የክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች አርባ ቀን ፆመዉ የምሥራች የዓለም ቤዛ ክርስቶስ ተወለደ ሲሉ የልደትን በዓል በምሥራች በደስታ ያከብሩታል ተድላዉ ደስታዉም የተጋነነ ነዉ ሲሉ የሃይማኖት አባቶች ይናገራሉ።