የፓሪሱ ጥቃትና የዓለም መሪዎች አስተያየት
አወዛጋቢ ምፀታዊ ምስሎችን በሚያወጣው ሻርሊ ኤብዶ በተባለው የፈረንሳይ ጋዜጣ የፓሪስ ቢሮ ውስጥ ትናንት በታጣቂዎች የተፈፀመው ግድያ በአብዛኛው የዓለም ክፍል እየተወገዘ ነው ።
አወዛጋቢ ምፀታዊ ምስሎችን በሚያወጣው ሻርሊ ኤብዶ በተባለው የፈረንሳይ ጋዜጣ የፓሪስ ቢሮ ውስጥ ትናንት በታጣቂዎች የተፈፀመው ግድያ በአብዛኛው የዓለም ክፍል እየተወገዘ ነው ።
ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ሙስሊም ያልሆኑ ጀርመኖች እስልምና እንደሚያሰጋቸው ይኽው የዳሰሳ ጥናት አሳይቷል ። ይህም ከሶስት ዓመት በፊት ከነበረው ሁኔታ ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ መሆኑ ተዘግቧል ።
ፈረንሣይ መዲና ፓሪስ ውስጥ «ቻርሊ ኤብቶ» በተሰኘው፥ ምፀታዊ ምስሎችን በሚያወጣ ሣምንታዊ መፅሔት ዋና ጽ/ቤት ላይ በተጣለ ጥቃት 12 ሰዎች ተገደሉ። ፈረንሳይ ዛሬ የሃዘን ቀን አዉጃለች። በርካታ ተጠርጣሪዎችም እየተያዙ ነዉ።
የገና በዓል ልዩ ዝግጅት በተመለከተ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ የአውሮጳ ሃገራት የሚገኙ ወኪሎቻችን የላኩት ዘገባ በተለይ በአውሮጳ የሚገኙ ስደተኞች በዓሉን እንዴት እንዳከበሩት ያስቃኛል። ዘገባዎቹ ከኢትዮፕያ፣ ከፈረንሣይ፣ ከጀርመን እና ከጣሊያን የተላኩ ናቸው።
በአሜሪካን የማሳቹሴትስ ግዛት የሞት ፍርድ ለመጨረሻ ጊዜ ተግባራዊ የተደረገው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1947 ዓ.ም. ነበር። በግዛቲቱ ፊሊፕ ቤሊኖ እና ኤድዋርድ ጌርትሰን ላይ ብያኔው ተግባራዊ ከሆነ በኋላ የሞት ፍርድ እንዲቀር ተድርጎ ቆይቷል።
ለአውሮፓ ገበያተኞች የዩሮ መቀነስ አስደሳች ዜና ሆኖ ሳለ ፤ አውሮፓ ተቀምጠው ከሌላው የአለማችን ክፍል ለሚሸምቱ ደግሞ ሁኔታው አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል። የዩሮ መቀነስ ጠቃሚ ወይስ ጎጂ ይሆን?
ፔጊዳ የተባለውን በአውሮፓ ፀረ እስልምና ንቅናቄን ዓላማ ና እንቅስቃሴ በመቃወም ትናንት ማምሻውን በበተለያዩ የጀርመን ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል ። በተመሳሳይ ጊዜ የንቅናቄው አባላትና ደጋፊዎቻቸውም በአንዳንድ የጀርመን ከተሞች አደባባይ ወጥተዋል ።
በናይጀርያ የሚንቀሳቀሰዉ ቦኮሀራም የሚባለው እስልምና አክራሪ ቡድን ጥቃት በጎረቤት ሃገራት በመዛመቱ በምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት ሥጋት ፈጥጥሯል። ቡድኑ ታኅሣሥ 26 ቀን፤ 20017 መጨረሻ በናይጀርያ የሚገኘዉን የአህጉሪቱን የጥምር ወታደራዊ ጦር ሰፈር በቁጥጥሩ ሥር ማድረጉ ይታወቃል።
የዕለቱ ዜና
የወቅቱ የአፍሪቃ ሕብረት መሪና የሞሪታንያዉ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ኡልድ አብዱል አዚዝ፤ በኤቦላ ተሐዋሲ ክፉኛ የተመቱትን ሶስት የምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት መጎብኘታቸዉ ተመልክቶአል።
የአሸባብ ታጣቂ በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ የአውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በሚገኝ የደህንነት ጽ/ቤት ላይ በፈጸመው ጥቃት አምስት ሰዎች ተገደሉ።
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዓለም ዙርያ ከሚገኙ ሃገራት የተዉጣጡ 20 ጳጳሳትን ፤ ካርዲናል ብለው ትናንት ሰይመዋል።
ባለፈው ሳምንት ኀሙሰ ያባተው 2015 አዲሱ ጎረጎሪዮሳዊ ዓመት ለዩክሬይን
ሕዝብ የባሰ የፈተና ጊዜ እንጂ የብልጽግና ዘመን ይሆናል ብሎ የሚያስብ
አንድም ያገሪቱ ዜጋ የለም። ኤኮኖሚው ተንኮታኩቷል። ከሩሲያ ጋር መፋጠጡም
ለድቀቱ የበኩሉን ድርሻ
ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም ለሚካሄደው የኢትዮጵያ አገር አቀፍ ምርጫ እስካሁን 60 የፖለቲካ ፓርቲዎች በተሳታፊነት የምርጫ ምልክቶቻቸውን መውሰዳቸውን እና ከጥር 1 እስከ የካቲት 12 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ ባሉት 42 ቀናት ከ33 ሚሊዮን በላይ መራጮች ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ዘላቂ ውጤት ያጣበት ምክንያቱ ምንድን ነው?ብሔራዊ ቡድኑ በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ዘላቂ ውጤት ከራቀው ቆይቷል። በእርግጥ ቡድኑ እጎአ በ1962 ዓም የአፍሪቃ ዋንጫ አሸናፊ ለመሆን የበቃ ነበር።
ግሪክ ከዩሮ ሸርፍ ተጠቃሚ ሃገራት አባልነትዋ መውጣት ከፈለገች እንደምትችል የጀርመን ፊደራል መንግሥት ማስታወቁን በጀርመንኛ ቌንቌ የሚታየው «ሽፒግል» የተሰኘዉ የዜና መፅሔት ዛሬ ዘገበ።
የጋምቢያ መንግሥት ባለፈዉ ማክሰኞ መፈንቅለ መንግሥት ከሞከሩ የጦር መኮንኖች ጋር ግንኙነት አላቸዉ ብሎ የጠረጠራቸዉን የጦር መኮንኖች ማሠሩን ጥሎአል።
በአንዳንድ የውጭ መገናኛ ብዙኀን እንደተዘገበውና የኢትዮጵያ መንግሥትም እንዳረጋገጠው Mi-35 በሚል መለያ በሚታወቅ አንድ ተዋጊ ሄሊኮፕተር ፣ 3 ኢትዮጵያውያን የአየር ኃይል ባልደረቦች፤ ከድሬዳዋ ኮብልለው ኤርትራ ገብተዋል። ይህ የሆነው ከ
ከትናንት በስተያ በተሰናበትነው እጎአ በ2014 ፣ዓለም በተለያዩ ጂኦ ፖለቲካዊ ቀውሶችና በወረርሽኝ ብትጠቃም ኤኮኖሚዋ ግን በ3 በመቶ ከማደግ አልተገታም ። ሐሙስ አንድ ባልነው በ2015ስ ምን ይጠበቅ ይሆን ?
የርስ በርስ ግጭት በየጊዜው በሚያገረሽባት በደቡብ ሱዳን ከጥቂት ወራት በኋላ አጠቃላይ ምርጫ እንደሚካሄድ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ትናንት አስታውቋል። መንግስት በዚሁ ምርጫ ብዙዎች እንዲሳተፉ ለአማፅያን ምህረት እንደሚያደርግም ተናግሯል።
2014ን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ፓን ጊ ሙን የተስፋ አድማስ የጨለመበት ነበር ያሉት-ባለፈዉ መስከረም።
ሁለቱ አንጋፋ ሙዚቀኞች ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸዉ ከተሰማ በኋላ በአዉሮጳ በተለይም በጀርመን ሙዚቃዎቻቸዉ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃኖች ከፍ ብለዉ መሰማት ጀምረዋል፤ በተወዳጅ ሙዚቃ መጠይቅ መዘርዝርም የአንደኝነቱን ቦታ ይዘዋል። ኦስትርያዊዉ ሙዚቀኛ ኡዶ ዮርገንስና፤ ብሪታንያዊዉ ሙዚቀኛ ጆ ኮከር!
ባለፉት ዓመታት ከኢትዮጵያ የሚሰደደዉ ጋዜጠኛ ቁጥር በእጥፍ መጨመሩን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት «CPJ» ገለፀ። እንደ ድርጅቱ ዘገባ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የጀመረዉን የእስራት ዘመቻ በመፍራት ባለፉት 12 ወራቶች ብቻ ከኢትዮጵያ ከሰላሳ በላይ ጋዜጠኞች ተሰደዋል።
የኢጣሊያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂ ጦር ቃል አቀባይ ፊሊፖ ማሪኒ እንደሚሉት ባልደረቦቻቸዉ ባይደርሱ ኖሮ ዓለም በሌላ የባሕር ላይ ጥፋት ባዘነ ነበር።አብዛኞቹ ስደተኞች የሶሪያ ዜጎች ናቸዉ።
የመልዕክተኞቹ ቡድን ሳዑዲ አረቢያ ከሚኖሩ ከተመረጡና የተወሰኑ ኢትዮጵያዉን ጋር መነጋገሩም ተሰምቷል።
የሳዑዲ አረቢያ ቀጣሪዎች ወይም አሰሪዎች ችግር ያደርሱብናል የሚሉ አብዛኛዎቹን ኢትዮጵያዉያንን ግን አላነጋገረም።
የአዉሮጳ የቀዉስ እንብርት በምትባለዉ ግሪክ ከመደበኛዉ የምርጫ ጊዜ ቀደም ብሎ በሚቀጥለዉ የጥር ወር አጋማሽ ላይ ጠቅላላ ምርጫ እንደሚደረግ ተነግሯል።
አንዳድ አጥኚዎች እንደሚሉት አራቱ መንግሥታት በጋራ ከመቆም ይልቅ አንዱ ሌላዉን ለማጥቃት አሸባሪዉን ቡድን እንደመሳሪያ እየተጠቀሙበት ነዉ
አምና ሊባል አንድ ቀን የቀረዉ ጎርጎሪዮሳዊዉ 2014ዓ,ም በጤናዉ ረገድ ዓለም ያደናገጡ በሽታዎች የተከሰቱበት ነበር። በዚህ ዓመት ከታዩት በሽታዎች ሳርስ፣ ማርቡርግ እና የወፍ ጉንፋን በየተቀሰቀሱበት አካባቢ ሲወሰኑ፤ ኤቦላ ግን መነሻዉ ምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት ቢሆንም የተሐዋሲዉ ስርጭት በርካታ ቦታዎችን ነካክቷል።
አንዳድ ዘገቦች እንደጠቆሙት የኢትዮጵያ መንግሥት የኮንትራት ሠራተኞችን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመላክ አዲስ ሕግ አርቅቋል።
አድርያቲክ ዉቅያኖስ ዉስጥ መስጠም ከጀመረችዉ መርከብ ተሳፋሪዎችን የማዳኑ ተግባር መጠናቀቁን የጣሊያን መንግሥት አስታወቀ።
«ዓለም ከሁለተኛዉ ያዓለም ጦርነት ወዲሕ የዘንድሮን ያክል ሕዝብ ተሰዶ፤ተፈናቅሎባት አያዉቅም።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለበርካታ ሕዝብ አስቸኳይ እርዳታ እንዲያቀርብ የዘንድሮን ያክል ተጠይቆ አያዉቅም።»
የአፋር ነፃ አዉጪ ግንባር (ALF) ከአፋር መስተዳድር ገዢ ፓርቲ ከአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ)ጋር ያካሄደዉ ዉህደት ህገ ወጥ ነዉ በሚል በዶቼ ቬለ የተላለፈዉ ቃለ መጠይቅ ከሃቅ የራቀ ነዉ ሲል አስተባበለ።
የሶማልያ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብ የመረጃ ኃላፊ እንደሆኑ የተነገረላቸዉ ግለሰብ ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ ቅዳሜ በሶማልያ ለሚገኝ የአፍሪቃ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ኃይልና ለሶማልያ መንግሥት ጦር እጃቸዉን ከሰጡ በኋላ ግለሰቡ ከዓመት በፊት ቡድኑን ጥለዉ መዉጣታቸዉን አሸባብ ዛሬ አስታወቀ።
2014 ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ሊሰናበት የቀናት እድሜ ቀርተዉታል። ዓመቱ እንደቀዳሚዎቹ ዓመታት ሁሉ የማይዘነጉ ጉዳዮችን ጥሎ ማለፉ ግድ ነዉ።
ከኢንዶኜዢያ ወደ ሲንጋፑር ሲበር የተሰወረው የኤር ኤዢያ የአየር መንገድ አውሮፕላን አሁንም የደረሰበት አልታወቀም። 155 መንገደኞችን እና 7 የበረራ ሠራተኞችን አሳፍሮ የነበረው አውሮፕላን በገጠመው መጥፎ የአየር ሁኔታ ምናልባትም ሳይከሰከስ እንዳልቀረ ተገምቷል። የአውሮፕላኑ ፍለጋ ለጊዜው ተቋርጧል።
የአልሸባብ ከፍተኛ መሪ እንደሆነ የሚነገርለት ዛካሪያ ኢስማይል አህመድ ሔርሲ ሶማሊያ ውስጥ መማረኩን ዛሬ አንድ የሶማሊያ የደኅንነት ሹም አስታወቁ።
ለመሆኑ ወጣቶች በተለይ ልጃገረዶች ከቤት ሲወጡ፤ በሰላም ስለመመለሳቸው ምን ያህል አስተማማኝ ነው? በዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት ርዕስ አድርገንዋል።
የሶማሊያ አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብ ትናንት መዲና ሞቃዲሾ የሚገኘዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጦር ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ተረጋግጧል። በዚሁ ጥቃት ከአፍሪቃ ሕብረት ወታደሮች ጋር በተከፈተ የተኩስ ልውውጥ ሶስት ወታደሮችን ጨምሮ ቢያንስ 9 ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል።
ሊቀመንበሩ እንደሚሉት የግንባሩ አባላት በቅርቡ ባደረጉት ጉባኤ የፓርቲያቸዉ ሕልዉና እንዲከስም ወስነዋል።የአፋር ነፃ አዉጪ ግንባር (ALF) አመራር አባላት ነን የሚሉ የአፋር ፖለቲከኞች ግን ዉሕደቱን እንደማይቀበሉት አስታዉቀዋል።