በቅርቡ ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት ሲዘጋጁ የነበሩ 6 ወጣቶች ከተያዙ በሁዋላ፣ የወጣቶቹ ጉዋደኞች ናቸው የተባሉት ሁሉ እየታደኑ በመያዝ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ሰሞኑን በወያኔ ጸጥታ ሃይል ከተያዙት ወጣቶች መካከል 4ቱ በመገናኛ አካባቢ፣ 2ቱ ደግሞ በመርካቶ እንደተያዙና በ እስር ቤት ከተወሰዱ ቦኋላ በሽብረተኛው የመለስ ዜናዊ የጸጥታ ሰራተኞች እጅግ አሰቃቂ የሆነ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ወያኔ አለኝ […]

ወያኔ የአዲስሰ አበባ መስተዳደር  በ2005 ዓ.ም. ለሚያደርገው ምርጫ የቅስቀሳ ሥራ እንዲሠሩ በሚል ሰበብ  በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ሌሎች  ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች  በተለያየ የትምህረት ደረጃ  በመጀመርያ ዲግሪና በሁሉተኛ ዲግሪ መርሐ ግብሮች በማመር ላይ የሚገኙ  አባላቱን፣ ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡና አስፈላጊዉን ቅድመ ምርጫ ዝግጅት እንዲያደረጉ  አሳሰበ። 99 ነጥብ 6% ህዝብ መርጦኛል ከኔም ፍቅር አለዉ እያለ የሚመጻደቀዉ የወያኔዉ ዘረኛ አገዛዝ  ያዲስ አበባን […]

ህዝባችን በሳምንት 3 ግዜ ብቻ መብራት በሚያገኝባት ሀገር የአገሪቱ መብራት ሃይል ኩባንያ ለጅቡቲ መንግስት እስከ 200 ሜጋ ዋት የሚደርስ የኤሌክትሪክ ሃይል ለመሸጥ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ታወቀ። በኢትዮጵያው ሚሊኒየም አከባበር ሥነሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ከአሁን ቦኋላ ሻማ የሚያበራው ለልዴት ቀን  ብቻ ይሆናል ተብሎ በመለስ ዜናዊ የተለመደው የውሽት ተስፋ ቃል የተገባ ቢሆንም ችግሩ እስከዛሬ ተባብሶ እንደቀጠለ ይታወቃል። […]

ህወሀትን ከተቀላቀለበት ከ 1968 ዓመተምህረት ጀምሮ በተሰጠው የአፈናና የግድያ አስተባባሪነት ቦታ በትንሹ ከ 10 ሺህ በላይ ሰዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለውና ያስገደለው ብስራት አማረ ዛሬ ደግሞ አሜሪካ ተመድቦ ውጪ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ እየሰለለ እንደሚገኝ አቶ ገብረመድህን አርአያ አጋለጡ። ቅጥረኛዉ ነፍሰ ገዳይ ብስራት አማረ፤ አክሱም ተወልዶና እስከ ዘጠነኛ ክፍል ድረስ እዚያው ከተማረ በሁዋላ ህወሀትን መቀላቀሉን የጠቀሱት አቶ ገብረመድህን፤ […]

የሥልጣን ዘመኑን እስከወዲያኛው ለማራዘም የሚችል መስሎት የሚቃወሙትን ሁሉ በሽብርተኝነት እየፈረጀ ዘጎችን ወደ እስር ቤት ማጎር የጀመረው የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ያለአገባብ እያሰቃያቸው ያለውን ወገኖቻችንን እንዲፈታ ለመጠየቅ በ እንግሊዝና  በኖርዌዬ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ባለፈው አርብና እሁድ በየሚኖሩባቸው አገሮች ዋና ከተሞች በሎንዶንና ኦስሎ ሰልማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን የግንቦት 7 ዘጋቢዎች ባስተላለፉት ዜና ገለጹ። መለስ ዜናዊ ሽብርተኛ ነው፤ መለስ ዜናዊ ፋሽስት […]

ባለፈው ሳምንት በመኪና አደጋ ህይወታቸውን ያጡትና በከባድ ሁኔታ የቆሰሉት የነባር ህወሀት ታጋይ አርቲስቶች ጉዳይ፤ የትግራይን ህዝብ ክፉኛ እንዳስቆጣ የቀድሞ የህወሃት አመራር አባል የነበሩ አቶ አስገደ ገብረሥላሴ መግለጻቸውን ኢሳት ዘገበ። ታጋይ አርቲስቶቹ በሱዳን ዝግጅታቸውን ለማቅረብ  በመስቀል ዋዜማ በአሮጌ አውቶቡስ ከመቀሌ ተነስተው ጉዞ ቢጀምሩም፤በስተደቡብ 200 ያህል ኪሎ ሜትር ከተጓዙ በሁዋላ ቆቦ አካባቢ ሲደርሱ አውቶቡሱ ተገልብጡ 10 ታጋዮች […]

በሃዲያ ዞን የባዳወቾ ወረዳ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ የአላባ ብሄረሰብ አባላት የሚኖሩበት አከባቢ በአላባ ልዩ  ወረዳ ስር እንዲካለል ቀድም ሲል ያቀረቡት ጥያቄ መልስ ባለማግኘቱ የተነሳ በተፈጠረው ችግር፤ ችግር ፈጣሪ የሆነው የወያኔ ጸጥታ ሰራተኞች በህዝቡ ላይ በከፍቱት የተኩስ እሩምታ ከ20 ሰዎች በላይ በጥይት መመታታቸውና ከመካከላቸው የ4ቱ ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን ዘጋቢያችን ከስፍራው ካስተላለፈው ዜና ለመረዳት ተችሎአል። የአላባ ህዝብ […]

«ድርቅ በተክሎች ላይ የሚያስከትለውን ጫናና የዘሮቹን ውስጣዊ ተፈጥሮ መርምረናል። ገበሬዎች ምን ዓይነት የሰብል ዘር መቼና እንዴት ቢያመርቱ የተሻለ ፍሬ ማግኘት እንደሚያስችላቸው እናረጋግጣለን።» ዶ/ር አንዲ ጃርቪስ

እንደ ላስኪት እየተወጠሩና እየተለጠጡ ቀዳሚና ትክክለኛ ትርጉማቸውን እየለቀቁና እየሳቱ በሰው ልጆች ተፈጥሮአዊ እንዲሁም ሕገ መንግሥታዊ መብቶች ሳይቀር በመጣስ ዜጎች እያሸማቀቁ ከሚገኙ የበላይነትና የራስ ጥቅም ማዕከል ያደረገ ፖሊሲ የሚያራምድ ሀገራትና መንግሥታት ተቀናቃኞቻቸውን ድባቅ ለመምታት ከፈጠራቸው ቋንቋዎች መካከል “አሸባሪ” (ሽብር። ሽብርተኛ) የሚለውን ቃል ተጠቃሽ ነው፣
ቋንቋው ከቋንቋነቱ አልፎ ሁነኛ ፖለቲካዊ ድምጽ አልባ ገዳይ መሳሪያ በመሆን ሲያገለግልም እሄው […]

በዘር ማጥፋት ወንጀል ተከሰው በሞትና በዕድሜ ልክ እስር እንዲቀጡ ከተወሰነባቸው የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል 16ቱ ተፈቱ፡፡
በዘር ማጥፋት ወንጀል ከተከሰሱት 23 ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል 20 ዓመት በእስር ያሳለፉት 16 ባለሥልጣናት በአመክሮ በትናንትናው ዕለት ተፈትተዋል፡፡
ትናንትና የተፈቱት ባለሥልጣናት የቀድሞው የደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ሻምበል ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስ፣ ምክትል ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ፍስሐ ደስታ፣ ሻምበል ለገሰ አስፋው፣ ኮሎኔል እንዳለ ተሰማ፣ ሜጀር […]

‹ያማ ሲያማ፤ያም ሲያማ ለኔ ብለህ ስማ› የሚለውን የተወዳጁን ድምጻዊ የጥላሁን ገሠሠን ጥዑመ ዜማ ለአፍታ ያህል እናስታውስ፡፡ ቀጥየ ከማስቀምጠውም ነጥብ ጋር በማዛመድ ከዐረብ ሕዝባዊ የ‹እምቢ አሻፈረኝ ለአምባገነኖች› የአብዮት እንቅስቃሴዎች አንዳች ነገር ለመማር እንሞክር፡፡
‹ኢንሳይድ ስቶሬ› የትናንት ማታ የአልጀዚራ ዝግጅት ስለትናንትናው የዐርብ ዕለት ውሎ የግብጽ ዳግማዊ አብዮተኞች እንቅስቃሴ ሲዘገብ የራሴ ጉዳይ ያህል በጥሞና ነበር የተከታተልኩት፡፡ በራሳቸው በግብጻውያኑ ባለሙያዎችና […]

በታረቀኝ ሙጬ ‹ያማ ሲያማ፤ያም ሲያማ ለኔ ብለህ ስማ› የሚለውን የተወዳጁን ድምጻዊ የጥላሁን ገሠሠን ጥዑመ ዜማ ለአፍታ ያህል እናስታውስ፡፡ ቀጥየ ከማስቀምጠውም ነጥብ ጋር በማዛመድ ከዐረብ ሕዝባዊ የ‹እምቢ አሻፈረኝ ለአምባገነኖች› የአብዮት እንቅስቃሴዎች አንዳች ነገር ለመማር እንሞክር፡፡ ‹ኢንሳይድ ስቶሬ› የትናንት ማታ የአልጀዚራ ዝግጅት …

ከግብጻውያንና ከሌሎች ምን እንማራለን? Read more »

የመን መንግስት ይውረድ በሚሉ ተቃዋሚዎች ከተናወጠች ጀምሮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና የወያኔ መንግስት ያላሰለሰ ጥረት የሚያደርጉት ቅጥፈታቸውን ለማስተጋባት ነው። አንዳንዴ በመጠኑ መዋሸትም ጥሩ ነው። ባለፈው ረቡዕ ዕለት በዶቺቬሌ ቃላቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቃል አቀባይ አቶ አምደሚካኤል አሳፈሩኝ። ኣሳፈሩን። ብለዋል።
የመን ያለን ኢትዮጵያዊያንን በአባባላቸው ግራመጋባት ብቻ ሳይሆን የተለያየ መላምት እንድንሰጥ አድርጎናል። አንዳንዶች […]