በአዲስ አበባ ከተማ እየተቀጣጠለ የመጣውን የህዝብ ተቃውሞ ለማምከን በመማር ላይ ያሉ የወያኔ አባላት ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ ትዕዛዝ መተላለፉ ተዘገበ። ምክንያት ለምርጫ 2005፣ ከወዲሁ መሰናዶ ለማድረግ ነው ተባለ

ወያኔ የአዲስሰ አበባ መስተዳደር  በ2005 ዓ.ም. ለሚያደርገው ምርጫ የቅስቀሳ ሥራ እንዲሠሩ በሚል ሰበብ  በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ሌሎች  ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች  በተለያየ የትምህረት ደረጃ  በመጀመርያ ዲግሪና በሁሉተኛ ዲግሪ መርሐ ግብሮች በማመር ላይ የሚገኙ  አባላቱን፣ ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡና አስፈላጊዉን ቅድመ ምርጫ ዝግጅት እንዲያደረጉ  አሳሰበ።

99 ነጥብ 6% ህዝብ መርጦኛል ከኔም ፍቅር አለዉ እያለ የሚመጻደቀዉ የወያኔዉ ዘረኛ አገዛዝ  ያዲስ አበባን ህዝብ ቀብሮትም ቢሆን እንደማያምነዉ በሚገልጽ መንገድ በከተማዋ ያሉትን ሆድ አደር ካድሬዎቹን ሰብስቦ ተቃዋሚዎች በ2004 ኢህ አደግን ከሥልጣን እናስወግዳለን በማለት እያደረጉ ያሉትን እንቅስቃሴ ለማክሸፍ የሞት የሽረት ትግል እንዲያደርጉ ትዕዛዝ ማስተላለፉ ታወቀ።

ወያኔ ለካድሬዎቹ በሰጠው በዚህ ትዕዛዙ ተቃዋሚዎች 2004ን እንደምርጫ 97ቱ ወቅት የአዲስ አበባን ህዝብ ሙሉ በሙሉ በጸረ ኢህአደግ ዘመቻ ሊያሳትፉ እየተራወጡ ስለሆነ፤ እያንዳንዳችሁ ይህንን ለማክሸፍ በሙሉ ጉልበታችሁና ሃይላችሁ መንቀሳቀስ የግላችሁን  ህይወት ለመሻሻል ከጀመራችሁት ትምህርት የበለጠ ዋስትና የሚሰጣችሁ ነው በማለት እያስፈራራ እንደነበረ ለማወቅ ተችሎአል። ት ዕዛዙን የሰጡ ሹሞች ደጋግመው ”ዘንድሮ የሞት የሽረት ዓመት ነዉ፤ ባሁኑ ሷአት በአዲስ አበባ ከተማ  ህዝብ ላይ የ97ቱ ዓይነት ስሜታዊ መነቃቃት እየተስተዋለ ነው”  በማለት ሲናገሩ ከመሰማታቸው በተጨማሪ በአጠቃላይ በአሁኑ ሰአት የሚታየውን የህዝብ ብሶት ምሬትና በቃኝ ባየነት አገዛዙን ምን አይነት ፍርሃትና ድንጋጤ ላይ እንደጣለው አመልካች ነው ተብላኦል ምንጮች።

ወያኔ በመላው አገሪቱ እያየለ የመጣው ህዝባዊ ጥላቻ በአባላቱ ውስጥ ምን ያህል እንደሰደደ ለማወቅ  ካለፈዉ መስከረም 10ቀን ጀምሮ እስከ ትላንት ድረስ ከሚኒስትሮች  እስከ የበታች ሠራተኞች  የዘለቀ ወያኒያዊ ግምገማ እንዳካሄደ የታወቀ ሲሆን ፤ በዚህም ግምገማ በዋነኛነት «፡”የአመራር ሚናችሁ ምንድነው? በከተማው ውስጥ ቅሬታ የሚያቀርቡ የኅብረተሰብ ክፍሎች በዝተዋል፤” ያዲሳባ የምርጫ ችግር የህልዉናችን ችግር ነዉ ።|» በሚሉ ጉዳዮች ሲብጠላጠሉ ከቆዩ በሗላ ወያኔ የራሱን ዉሳኔም አሳዉቋቸዋል። በዚህመወ መሰረት ፡ በህዝብ ሀብትና ንብረት በየ ዩኒቨሪስቲዎችና ኮሌጆች የሚማሩ ካድሬ አባላቱ በሙሉ ካሁን ጀምሮ እነዚህን 2 ዓመታት ትምህርታቸውን  እንዲያቋርጡና ካድሪያዊ ተግባራቸዉን በትጋት እንዲጀምሩ ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ሆኖም  ዘጋቢያችን ካነጋገራቸዉ ካድሬዎች እንደተረዳወ ካድሬዎቹ በ እዉነትም ያዲሳባን ህዝብ እንኳን አሁን ነጻነቴ በሚልበት ሰዓት ይቅርና በ97ቱም እናዉቀዋለን ሁሌም በሰቀቀን ነዉ ያለነዉ ስለዚህ «ትምህርታችንን አቋርጠን በምርጫ ብንሸነፍ ምን ልንሆን ነው?” የሚል ጥያቄ እርስ በርሳቸው በማንሳት በከፍተኛ ጭንቀት ላይ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ ወያኔ ድሀረ ምርጫ 97 ቁጥራቸውን ወደ 5 ሚሊዮን አድርሶአቸው ከነበሩት አባላቱ መካከል በርካቶችን ለመቀነስ እቅድ እንዳለውና ይህንኑ ለመተግበር እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ዘጋቢያችን ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ያገኘውን መረጃ ዋቢ በማድረግ ገልጾአል። ወያኔ የአባላቱን ቁጥር ለመቀነስ የተገደደው፤  በኑሮ ዋጋ መናርና አገዛዙ በሚከተለው ዘረኛ ፖሊሲ ምክንያት “ኢህአደግ” በተባለው ስብስብ ውስጥ የትግራይ የበላይነት የፈጥረው ጥላቻ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያየለ በመምጣቱ፤ የአገዛዙን ዕድሜ ለማሳጠር የሚችል ትልቅ አደጋ አዝሎአል ተብሎ በመለስ ዜናዊና ጥቂት ግብረአበሮቹ በመታመኑ እንደሆነ እነዚሁ ምንጮች አክለው መግለጻቸው ታውቆአል።

ወያኔ “ኢህአደግ” በማለት በሚጠራው ድርጅት ውስጥ የተንሰራፋውን የህወሃት የበላይነት የሚቀናቀኑትን በግምገማ ስም ሲመነጥር የኖረ መሆኑ ቢታወቅም፤ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች በአንዴ ማሰናበት ሊያደርስበት የሚችለውን የፖለቲካ ኪሳራ ለመቀነስ የሚያስችለውን ብልሃት አጥንቶ የሚያቀርብ ቡድን መመስረቱን ለአመራሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ተናግረዋል።

በሌላ ዜና ደግሞ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች በስርአቱ ላይ የሚያሰሙት ተቃውሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ኢሳት በትናንትናው ዜና እወጃው ዘግቦአል።

እንደ ኢሳት ዘገባ “ከያዝነው የመስከረም ወር መባቻ ጀምሮ ትግራይ ውስጥ አገዛዙን አይደግፉም፣ ለጸረ ሰላም ሀይሎች መሳሪያ ሆነዋል” የተባሉ ወጣቶች ለእስርና ለወከባ እየተዳረጉ መሆኑ ሲገለጽ፤ ለህወሃት መስመር ተገዢ አልሆናችሁም ተብሎ በአረና ፓርቲ ደጋፊነት እየተፈረጁ ከያሉበት ታድነው ለእስርና ለእንግልት ከተዳረጉት ያመለጡ በርካታ ወጣቶች ወደ በረሃ በመጓዝ የትግራይ ዲሞክራሲ ንቅናቄ በመባል የሚታወቀውንና ወያኔን በትጥቅ ትግል በመፋለም ላይ የሚገኘውን ድርጅት እንደተቀላቀሉ ተዘግቦአል።