በኢትዮጵያ የደን መራቆት
በኢትዮጵያ ለደን መመናመን እንደምክንያት ከሚጠቀሱ ዓበይት መንስኤዎች የኅብረተሰቡ ለኃይል ምንጭነት እነሱን መጠቀሙና ለእርሻ መሬት ማስፋፋት ሲባል አላግባብ መመንጠራቸዉ ነዉ። በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለባለሀብት እየታደሉ የሚገኙ ደን ለበስ መሬቶች ጉዳይ አነጋጋሪነቱ ከፍ እያለ በመሄድ ላይ ነዉ። የእለቱ ጤናና አካባቢ መሰናዶ ለካርቦን ብክለት ቅነሳ ይረዳሉ የሚባሉትን ዛፎች ደህንነት ለማስጠበቅ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የተቀረጸዉ ፕሮጀክት በዚህ ረገድ ያለዉን ሚና ይመለከታል። ያዳምጡ