የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥፈት በየመን

እንረዳቸዋለን ወይስ እናርዳቸዋለን?

ግሩም ተክለኃይማኖት

የመን መንግሥት ይውረድ በሚሉ ተቃዋሚዎች ከተናወጠች ጀምሮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና የወያኔ መንግሥት ያላሰለሰ ጥረት የሚያደርጉት ቅጥፈታቸውን ለማስተጋባት ነው። አንዳንዴ በመጠኑ መዋሸትም ጥሩ ነው። ባለፈው ረቡዕ ዕለት በዶቼቬሌ ቃላቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቃል አቀባይ አቶ አምደሚካኤል አሳፈሩኝ። አሳፈሩን። ”ኢትዮጵያዊያኑን እንረዳቸዋለን … ከአይ.ኦ.ኤም. ጋር በመተባበር ወደ ሀገር መመለስ የሚፈልጉትን እንመልሳለን” ብለዋል።