በመለስ ዜናዊ የሚመራዉ የአሸባሪዉ የወያነኔ ቡድን፤ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ የሆነዉ ብስራት አማረ በአሜሪካን አገር በስለላ ተግባር ላይ እንደሚገኝ ተጋለጠ`
ህወሀትን ከተቀላቀለበት ከ 1968 ዓመተምህረት ጀምሮ በተሰጠው የአፈናና የግድያ አስተባባሪነት ቦታ በትንሹ ከ 10 ሺህ በላይ ሰዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለውና ያስገደለው ብስራት አማረ ዛሬ ደግሞ አሜሪካ ተመድቦ ውጪ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ እየሰለለ እንደሚገኝ አቶ ገብረመድህን አርአያ አጋለጡ።
ቅጥረኛዉ ነፍሰ ገዳይ ብስራት አማረ፤ አክሱም ተወልዶና እስከ ዘጠነኛ ክፍል ድረስ እዚያው ከተማረ በሁዋላ ህወሀትን መቀላቀሉን የጠቀሱት አቶ ገብረመድህን፤ ”ህንፍሽፍሽ”ተብሎ ከሚጠራውና በአመራሩ ላይ ጥያቄ ያነሱ በርካታ የህወሀት ታጋዮች ከተገደሉበት ጊዜ አንስቶ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ከአረመኔዉ መለስ የሚወጡ የግድያ ትዕዞችን በዋነኝነት ሲፈፅምና ሲያስፈፅም የነበረ በደም የተበከለ ግለሰብ መሆኑን አለኝ የሚሉትን መረጃ በመዘርዘር አጋልጠዋል።
ህወሃት በትግራይ በረሃ ውስጥ ትግል ላይ በነበረበት ወቅት ብስራት አማረና ጓደኞቹ ፤ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን በማሰር ጉድጓድ ካስቆፈሩዋቸው በሁዋላ በአንድ ጊዜ በጥይት ደብድበው በመግደል እዚያው ባስቆፈሯቸው ጉድጓድ ውስጥ እንደቀበሯቸው በሀዘን ያስታወሱት አቶ ገብረመድህን፤በጋለ ብረት እየተተኮሱና የፈላ ውሀ እየተደፋባቸው በሚዘገንን ሁኔታ እየተሰቃዩና እየጮኹ የሞቱም ጥቂት እንዳልሆኑ አውስተዋል። የሚገደሉት ሴቶች ከሆኑ ደግሞ፤ በነ ብስራት አማረ የአስገድዶ መድፈር ድርጊት ይፈፀምባቸው እንደነበርም አቶ ገብረመድህን ጠቁመዋል።
አቶ ገብረመድህን፤ በነፍሰ ገዳዮቹ በነ ብስራት አማረ ከተገደሉት ሰዎች የተወሰኑትን በዝርዝር ያቀረቡበትን ይህን ፅሁፍ ያነበቡ ሁሉ፤- “ ጽሁፉ፣አሁን በስልጣን ላይ ያሉት የህወሀት ቁንጮዎች ገና ከመነሻው ጀምሮ ምን ዓይነት ጨካኝና ደም መጣጭ ሰዎች መሆናቸውን ያመላከተን ነው” ሲሉ አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው።
“ብስራት ዛሬ አሜሪካ መጥቶ በየፓልቶኩ የወያኔን ብፅዕና ሲሰብክና ሲመፃደቅ እየሰማነው ነው” ያሉት አቶ ገብረመድህን፤”ይሁንና ፤ እየገረፈና እየገደለ ስለገነባው ድርጅት ጥብቅና ቢቆም ባህሪያዊ ነውና መገረም የለብንም”ብለዋል። አቶ ገብረመድህን አያይዘዉም ህወሀት በትጥቅ ትግሉ ጊዜ በትግራይ ህዝብ ስም ያገኘውን በመቶ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር እርዳታ ፤ ለድርጅቱ እንዳዋለው ተጨባጭ መረጃዎችንና ፎቶግራፎችን ጭምር ዋቢ አድርገው ማጋለጣቸው ይታወሳል።
አቶ ገብረመድህን አረ አያ የህወሃት ፋይናንስ ሃላፊ ሆነው ለበርካታ አመታት ከሰሩ ቦኋላ የህወሃት አመራር እየያዘ በሄደው የጸረ ኢትዮጵያ አቋም ልዩነት ፈጥረው ከድርጅቱ እንደተለዩና በጊዜው ሥልጣን ላይ ለነበረው ደርግና ሊትዮጵያ ህዝብ እጅግ ጠቃሚ የነበሩ መረጃዎችን ምንም ሳይደብቁ ይፋ አድርገው የነበሩ አገር ወዳድ ሰው እንደሆኑ ይታወቃል። የአቶ ገብረመድህንን መረጃ በአገባቡ ያልተጠቀመው ደርግ እራሱ ወድቆ አገሪቷንም አሁን ካለችበት አደጋ ውስጥ ከቶአት እንዳለፈ ታሪክ በተደጋጋሚ ስገለጽ ኖሮአል።