ፖሊስ ቤተሰብን በወረዳ፣ በብሎክ ብሎም በቤት ደረጃ በማደራጀት እየጠረነፈ ነው::

ፖሊስ የቤተሰብ አባላትን እየጠረነፈ ነው

Negere Ethiopia's photo.

ፖሊስ ቤተሰብን በወረዳ፣ በብሎክ ብሎም በቤት ደረጃ በማደራጀት እየጠረነፈ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ ከአሁን ቀደም በየካ ከፍለ ከተማ በየግቢው የታደሉ ‹‹የቤተሰብ ተጠሪ ፎረም›› የሚሉ ቅፆችን በማስደገፍ መዘገባችን የሚታወቅ ሲሆን ሰሞኑን በሳሪስ በተመሳሳይ አደረጃጀት ቤተሰቦችን ለመጠርነፍ እየተሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ቅፁ ላይ የቤተሰብ አባላት ‹‹በመኖሪያ ቤታችን ውስጥ የሚፈጠሩ ያለ መግባባቶችን በራሳችን ለመፍታትና ብሎም የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ እንዲሁም ከፖሊስ ጎን ሆነን በማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የድርሻችን ለመወጣት›› በሚል ከቤተሰብ መካከል ለፖሊስ ተጠሪ እንዲወክሉ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ይህ የቤተሰቡ የፖሊስ ተወካይም ግቢው ውስጥ ተፈጠሩ የሚላቸውን ጉዳዮችና ሌሎችም መረጃዎች ለፖሊስ ማድረስ ይጠበቅበታል፡፡ ጥርነፋው ከቤተሰብ ተነስቶ፣ ብሎክ፣ ቀጠና እና ወረዳ እያለ እንደሚቀጥልም ለማወቅ ተችሏል፡፡

5 Comments on “ፖሊስ ቤተሰብን በወረዳ፣ በብሎክ ብሎም በቤት ደረጃ በማደራጀት እየጠረነፈ ነው::”

  1. ጥሩ ነዋ! ይሕ ምን ችግር አለው? ሰላም ለማምጣትና ችግር ፈጣሪዎችን ለመቆጣጥር ይረዳል:: በርቱ ፖሊሶች!!

  2. ጥሩ ነዋ! ይሕ ምን ችግር አለው? ሰላም ለማምጣትና ችግር ፈጣሪዎችን ለመቆጣጥር ይረዳል:: በርቱ ፖሊሶች!!

  3. ሀይ ወያኔ የ1ለ5አደረጃጀት ፖለቲካችሁ ለዉጥ አላመጣ አለ እንዴ? ካልሆነ ሙስና መድቡና ባደረጃጀት ሽፋን የግዛታቹ ፀሮችን አስለቅሙ የናንተ አደረጃጀት ከዛ አያልፍም

  4. Sew metchem be and ayenesam karat asteyayet aybeltem menta enkuwan be honest yeweyane frewoch wede hilenachehu temelesuna yendesew lemaseb mokeru kaltesakalachehu zem belu.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*