የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው ወጣቱ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ከፓርቲው ጋር መለያየቱን አስታወቀ፡፡
ማክሰኞ ኅዳር 14 ቀን 2008 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ በፌስቡክ ገጹ ከፓርቲው ጋር መለያየቱን፣ ከአሁን በኋላ የሚወክለው የፖለቲካ ድርጅት እንደሌለና የሚወክለው ራሱን ብቻ እንደሚሆን ገልጿል፡፡
‹‹ከአሁን በኋላ ማንኛውንም የፖለቲካ ፓርቲም ሆነ ቡድን የማልወክል እንደሆነ አሳውቃለሁ፡፡ የእኔ ውክልና ለራሴ ብቻ ነው፤›› ይላል በአቶ ዮናታን ፌስቡክ ገጽ ላይ የሠፈረው ማሳሰቢያ፡፡
እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰበትን ምክንያት ያልገለጸ ሲሆን፣ ሪፖርተር ከሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችም ሆነ ከራሱ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረትም አልተሳካም፡፡
አቶ ዮናታን የቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ምሩቅና የ27 ዓመት ወጣት ሲሆን፣ ሰማያዊ ፓርቲን ከመቀላቀሉ በፊት በመምህርነት አገልግሏል፡፡ በምርጫ 2007 ወቅት ፓርቲውን ወክሎ በአዲስ አበባ ከተማ በምርጫ ክልል 17 መወዳደሩ ይታወሳል፡፡ አቶ ዮናታን ራሱን ከፓርቲ ፖለቲካ ማግለሉን ውሳኔውን ካስታወቀ በኋላ፣ በፌስቡክ ተከታዮቹ የተሰጡት አስተያየቶች የተደበላለቁ ስሜቶችን አንፀባርቀዋል፡፡

bamagemarym ebateh makameat yeshaleh naber baewnat yasazenal gen manenem atgodam farre
Yonatan malet yeEthiopia mrt yekurt ken lij mehonun bcha new yemawkew. yhe wore ewnetm yhun wshet yetgnaenm aynet wsanewn akebralew. gena bewetatnetachee lezihch Ager eyekeletu kalu jegnoch andu newna bemiyadergachew enkskasrwoch hulu Fetari kegonu yhunlet
Yshalhal mewtath?
who cares
ወያኔ ደለለው እንዴ?
yeh endemihon kedmen enawkalen
Why? Yoni
ይሄ ነፃ አስተያየቴ ነው! አንድ ሰው ከሚሰራበት ወይም ከሚሳተፍበት ቢዝነስ, ወይም ፖለቲካ ድርጅት ሲለቅ ግልፅ በሆነ መንገድ መናገር ወይም በፅሁፍም ሆነ በሌላ መልክ ማሳወቅ አለበት እላለሁ( የማድረግ መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ)። የቢዝነስ ደንበኞችም ሆኑ የፖለቲካ ተከታዮች ምክንያቱን ቢያውቁ ከብዙ መላምት መዳን ይቻላል!! ከእኔ ቀደም ያለ አስተያየት ሰጪ ወያኔ ደለለው እንዴ! የሚል አስተያየት ሰንዝሯል!! ከዚህና ከመሳሰሉት ግምቶች ለመዳን ግልፅነት ይረዳል ብዬ አምናለሁ