የጆሮ ኢንፌክሽን (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

የጆሮ ኢንፌክሽን በባክቴሪያ ወይንም በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ ችግር ሲሆን ከ3 ወር እስከ 3 ዓመት ባሉ ሕፃናት ላይም ጎልቶ ይታያል፡፡ ነገር ግን በሁሉም የዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎች በህመሙ ሊጠቁ ይችላሉ፡፡

በአብዛኛው ከጉንፋን በኋላ የሚመጣ ችግር ሲሆን ምክንያቱም የመካከለኛው የጆሮ ክፍል ከኋለኛው የአፍንጫ ክፍል ጋር በቱቦ የተያያዘ ስለሆነ ነዉ፡፡

✔ የጆሮ የኢንፌክሽን ምልክቶች
• የጆሮ ሕመም
• የጆሮ መደፈን ስሜት
• የራስ ምታት
• ከጆሮ የሚወጣ ፈሳሽ
• ጆሮ ውስጥ የሚጮህ ስሜት
• የመስማት ብቃት መቀነስ እና ማቆም
• አዲስ የተወለዱ ሕፃናት ደግሞ በእጃቸው ወደ ጆሮ አካባቢ በተደጋጋሚ ይነካካሉ
• መቅለሽለሽ እና ማስመለስ
• ማስቀመጥ
• ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት መጠን መጨመር

✔ ከዚህም በተጨማሪ
• በጆሮ አካባቢ ያለው አጥንት ኢንፌክሽን መፈጠር
• የአንጎል ሽፋን የሆነው የመነንጂስ ኢንፌክሽንም ያስከትላል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች ከተከሰቱ ወደ ህክምና ማዕከል በመሄድ አስፈላጊዉን ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

✔ የጆሮ ኢንፌክሽንን ለመከላከል
• ጡት ማጥባት
• ጡጦ በጀርባ አስተኝቶ አለማጥባት
• ክትባቶችን ማስከተብ
• እጅን በሚገባ መታጠብ
• ልጅዎ ባለበት አካባቢ ሲጋራን አለማጤስ ናቸዉ፡፡

ጤና ይስጥልኝ
http://www.honeliat.com/ear-infection/