ድርቁ ከ1977ቱ ያልተናነሰ ነው ሲሉ አርሶአደሮች ተናገሩ

ኢሳት ዜና :-በወሎ፣ቆቦና ዋግ ህምራ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች የዘንድሮው ድርቅ ከ1977ቱ ያልተለየ ነው በማለት ለኢሳት ተናገሩ፡፡
ተጎጂዎች በድርቁ በርካታ ሃብት ንብረታቸውን በመጨረሳቸው ባዶ እጃቸውን እንደቀሩ ይናገራሉ፡፡የገዢው መንግስት ሚዲያዎች በድርቁ የሞተ ሰው የለም በማለት ለማስተባበል ቢሞክሩም ተጎጅዎቹ ‹‹ ከሃብታችን ባሻገር ልጆቻችን እየተነጠቅን ነው፡፡ ›› በማለት በተጨባጭ ያለውን የወቅቱን ችግር ይገልጻሉ፡፡
ድርቁ ዘንድሮ በይፋ በሁሉም አካባቢ ይከሰት እንጅ ባለፉት ሶስት አመታትም በተከሰተው የዝናብ እጥረት ከብቶቻቸውን ለመቀለብ የቤታቸውን ጣሪያ ሳር በመግፈፍ ለመቀለብ እንደተጠቀሙበት ያስታውሳሉ፡፡ የሳር ሃገር የነበረው፣ ሳሩ በማረሩ መሬቱ ባዶ በመሆኑ ለጥጆች እንኳን የሚበቃ ምግብ አለመኖሩን ተጎጅዎች ይናገራሉ፡፡ በቀጣይ ወራቶች ዝናብ ካልጣለ ከብቶቻቸው እንደሚያልቁና እነርሱም ችግር ላይ እንደሚወድቁ ፍራቻቸውን ይገልጻሉ፡፡
በሌላ ዜና ደግሞ ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ብር ወጪ ተደርጎ በየከተማውና በየሴክተር መስሪያ ቤቱ በግዳጅ ለአንድ ወር ሲከናወን የቆየው የብአዴን በዓል በታሰበው መልኩ ውጤት ሳያመጣ ተጠናቋል፡፡ ብአዴን ከባህርዳር ውጭ ያሉ የገጠር ነዋሪዎች መኪና አቅርቦ በአሉን ለማድመቅ ቢሞክርም፣ አብዛናው የባህርዳር ነዋሪዎች እንደሁም የዩኒቨርስቲ መምህራን በበአሉ ላይ አልተገኙም።
በተለይ ለአማራው ህዝብ ቆሚያለሁ የሚለው ብአዴን-ህውሃት ህዳር 3/2008 ዓ.ም በብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት በተደረገው የቼክ ርክክብ ስነ ስርዓት የ30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ዕርዳታ ማድረጉን በክልሉ ሚዲያዎች የተዘገበውን የተመለከቱ የባህርዳር ነዋሪዎች ‹‹ለበዓሉ ሽርጉድ ከመደበው በ10 እጥፍ የሚያንስ ገንዘብ ለሚዲያ ፍጆታ ለማዋል ዕርዳታ ብሎ መስጠቱ አስቂኝ ነው፡፡ ›› በማለት አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡
ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር አላስፈላጊ የካኪ ልብስና ሽርጥ ለበአሉ ታዳሚዎች ለአንድ ቀን ከማልበስ ይልቅ በረሃቡ ለተጎዱ ወገኞች ዕርዳታ ሊውል ይገባ ነበር በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ከረሃቡ ዜና ሳንወጣ የሴቭ ዘ ችልድረን የኢትዮጵያ ተወካይ ጆን ግርሃም “ኢትዮጵያ እርዳታ ትፈልጋለች፣ ፊታችንን ልናዞርባት አይገባም” በሚል ርዕስ በአውስትራሊያ ታዋቂ ለሆነው ሄራልድ ሰን ላይ ጽሁፍ አቅርበዋል። ተወካዩ ኢትዮጵያ በ30 አመታት ውስጥ ያልታዬ ድርቅ አጋጥሟታል ብለዋል። አለማፍ እርዳታ ለሶሪያ፣ ኢራቅ፣ የመን፣ ኔፓልና ደቡብ ሱዳን እየተሰጠ ባለበት ወቅት የኢትዮጵያ ድርቅ መከሰቱ አሳዛኝ ቢሆንም፣ አለም ፊቱን ሊያዞር እንደማይገባ፣ አውስትራሊያ ከ4 አመታት በፊት እንደሰጠቸው ድጋፍ አሁንም ተመሳሳይ ድጋፍ እንድትሰጥ ተማጽነዋል።
የኢህአዴግ መንግስት አቋም አንዳንድ ተቋማትና ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸውን እንዳይደግፉ እያደረጋቸው ነው። ኢህአዴግ ተከታታይ እድገት ማስመዝገቡን በተደጋጋሚ መናገሩ አሁን በድፍረት ረሃብ አለ ብሎ ለመናገር አሳፍሮታል። በቅርቡ የመንግስት የኮሚኒኬሽን ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑት ጌታቸው ረዳ፣ አለማቀፍ ማህበረሰቡ እርዳታ ለማግኘት ሲባል የተረጅዎችን ቁጥር እያጋነነ ያቀርባል በማለት ተናግረዋል። በዚህም የተነሳ፣ ኢትዮጵያውያን ተሰባስበው ድጋፍ ለመስጠትና በተለይም አለማቀፉ ማህበረሰብ ፊቱን ወደ ሶሪያና ሌሎች ቦታዎች በማዞሩ ክፍተቱን ለመሙላት በአስቸኳይ እንዳይደራጅ እንዳደረገው በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያን አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።

3 Comments on “ድርቁ ከ1977ቱ ያልተናነሰ ነው ሲሉ አርሶአደሮች ተናገሩ”

  1. ከጋዘጠኛ ደምስ በለጠ የሚባለው በበኩሉ የመኢሶን ገራፊነት ታሪኩን እያነሱ ቀልቡን የሚገፉት እንዳሉ ሲታወቅ says:

    ወንዝን ቁም ብሎ መንገር ፋይዳ ቢስ ነው – የግንቦት-አርበኞች ጦር አይገታም
    August 7, 2015

    ኑረዲን በሃልቢ

    ኢትዮጵያኖች ዕድላችን ሆነና ሀገር አዳኝ ሙከራ የሚያደርጉትን ማቀፍ ሲገባን ለብቻቸው መከራን እንዲቀበሉ ትተን፤ አጋፍጠን ከተለዩን በኋላ ማልቀስ መቆጨቱ ዕጣችን ሆኗል። በአስፈላጊው ጊዜ ከአርበኞቻችን ጎን ብንቆም ኖሮ ስንቱን ስቃይና መከራ ባስወገድን ነበር ያሰኛል ። አርበኞች ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ወደ ሀገር ዘልቆ ከወያኔ መፋለም ሲጀምር እልልታ ፈንታ ወገዛና ነቀፌታ መደመጡ ማሳዘኑ አልቀረም ። ግን እነማን ናቸው ይህን አሉታዊ ኡ ኡታ የሚያሰሙት?

    ሁናቴው በትልቁ የጠቀመን ተደብቀው የነበሩትን የወያኔ ሰራተኞች ሁሉ ራሳቸውን ማጋለጥ መገደዳቸው ነው። የውቤው ልሳን፤ ከዚህ ቀደም የነጻነት ራዲዮ አባል የነበረው ኢሳያስ ደርግነቱን እንደያዘ ወያኔነቱን ደግሞ በሕዝባዊ ኃይል ላይ በነዛው የሀሰት ዘመቻ አጋልጧል። ደምስ በለጠ ከሁሉም ቀድሞ ወደ ሻዕቢያ ነጉዶ ዛሬ ተመልሶ ግን በፊት ደብቆ የነበረውን ሁሉ ሰበር ዜና ብሎ ከወያኔ ሳይቀር አድናቆትን አትርፏል። የደምስ የመደብ ጀርባ ሳይሆን የታሪክ ጀርባ የሚያሳየን ጸረ ሕዝብ የገራፊንና ባንዳዊ ሚና ነው። ዛሬም ቢሆን ያኔ የገረፋቸውን አልረሳምና ሕዝባዊ ኃይሉን ሕልውና ሲነሳው እነሱንም ወረፍ ከማድረግ አለተቆጠበም። ደምስ ወያኔ የሚያደንቀውን ተልዕኮ ሲወጣ ምነዋ ብሎ ትንሽም መጠየቅ ለምን ተሳነውስ፤ለምንስ ህሊናውን (ካለው!) መጠየቅ አቃተው? ሌላው ወያኔ የኮለኔል ልጅ ብሎ የሚያቆላምጠው ኤልያስ ክፍሌ ማንነት ለአንዴም ለሁሌም ቁልጭ ብሎ ተጋልጧል ። የፕሮፌሰር ብርሃኑን ተጋድሎ ሲያክቸለችል የራሱን ሚዛንና ሚና ግን ሊያከብድ አልቻለም ብንል ተገቢ ነው ። ኤልያስ ከኢሳያስ ጎን ተለጥፎ ሲያናፋ ያልሰማ ነበርን ? ሻዕቢያ ወይ ሞት ያለው ከሁሉም በፊት ማን ነበር ? ኤልያስ የኢትዮጵያ ብሐራዊ የሽግግር ቆንስላ ባለስልጣን ነው። ይህ ተቋም ለምን በነጻ ሊፏልል ዘንድ ፈቀደለት ። ኤልያስ በግንቦት 7 መሪዎች ይቀናል ፡፤የኢሳት በሰፊው ተቀባይነትን ማግኘትና የእሱ ሬቪው አንባቢ ማጣት ይከነክነዋል። ፕሮፌሰር ብርሃኑ ሲከበሩ ኤልያስ ግን በሄደበት ዓይንህን ላፈር መባሉ ሊዋጥለት አልቻለም፤ የስለላ/ኢንተሊጀንስ/ መረቤ ይህን ያን የተደበቀ ሀቅ ፈልቅቆ አወጣ ወዘተ እያለ አሉባልታን አንግሶ ስም ሲያጠፋ የታዘብነው ኤልያስ ሰሚ ቢያጣ ጥፋቱ የራሱ እንጂ የሌላ አይደለም። በራሱ ላይ መነሳት ሲገባው ማለትም መታረም ሲኖርበት በግንቦት 7 ላይ መዝፈኑን ነው የመረጠው። እውነትም አጥፊና ግብዝ ገልሰብ።

    አላርፍ ያለች ጣት እንዲሉ ባለ ራዲዮው አበበ በለውም መስመር ለቆ በህዝባዊ ሀይሉ ላይ ማጓራት ለማያዉቁት ሊያስገርም ይችላል። ግን ይህ ግለሰብ ከወያኔ ጎራ መሰለፍ ከጀመረ ውሎ አድሯል። የሱቅ ስርቆት ጉዳይ እያነሱ አንገት ይያስደፉታል የሚሉም አሉ። ድርጊቱንና ቅስቀሳውን በሚገባ ከመረመርነው ሚናው ግልጽ ይሆናል ። ወዳጁ ቤን ኢትዮጵያ ፈርስት በጊዜው በአዲስ አበባ ስለሰራው ቪላም አሳውቆን እያለና በጸረ ሕዝባዊ ኃይል አቅዋሙ ወያኔ እያደነቀው እያለ ወያኔ የሚፈራው አንድ ራዲዮ ካለ የእኔን አዲስ ድምጽ ነው ብሎ ባለፈው እሁድ ሲፎክር ሰማን ። ያ ገንዘብ አሳዳጅ፤የመላኩ ተፈራ ቀኝ እጅ፤ ዕቁብ ዘራፊ፤ ስም አጥፊ ለፍላፊ ምርጫው ስንሻው ደግሞ ስንቱን በየመስኩ ሲያታልል ሲዘርፍ ከርሞ አንዳንድ የዋሆች ጸረ ወያኔ የሆነ መስሏቸው ጆሮአቸውን ሰጠውት ነበር ። ለመሆኑ 4 ሰዓት ሙሉ በራዲዮ ሊለፈልፍ ማን ገንዘብ ሰጠው ብሎ ለምንስ አልተጠየቀም ። ስንቱን ድርጅት ሲያወግዝና ለከፋፋዮች መድረክ ሰጥቶ ሲያጠቃ፤ ወያኔን ከመተቸት ይልቅ በግንቦት 7 ላይ አተኩሮ በየሳምንቱ ሲጮህ በዚሁ አቅዋሙ ማንነቱን ያጋለጠ ግለሰብ ነበር፡፤ እነሆ ዛሬ ለወያኔው ስናር ለቤን/ብንያም ቃለ መጠይቅ ሰጥቶ በሕዝባዊ ኃይሉ ላይ ዘመቻ ከፍቷል ። ወያኔም በሽልማት መልክ የሁለት ሰዓት ራዲዮ መክፈት እንዲችል ገንዘብ ለግሶታል ።

    እነዚህና መሰሎቻቸው ናቸው በግንቦት 7 ና በአርበኞች ሀይል ላይ ዘመቻ የከፈቱት ፡፤ የፍርሃትን መጋረጃ ከፍተውና ቀደው ወያኔን በክላሺን ሊያነጋግሩት የተነሱትን ጀግኖች የሚያክቸለችሉት ። ባይመቱበት እንኳን ያስፈራሩበት ይላል የህገራችን ሰው ፡፤ ሕዝባዊ ኃይል ምንም ሌላ አማራጭ ብቅ ባላለበት ባለው አቅም ሊፋለምልን ተነስቶ ኑ ደግፉኝ ሲል መደገፍ እንጂ መቃወም ወያኔን መጥቀም ብቻ ነው ግቡ ። ፕሮፌሰር ሙሴና አቶ መልኬ ያላቸውን ቁርሾ እናውቃሳለንና ብዙም ትችት አይጠይቅም ። መጠየቅ ያለበት ግን ያ ጸረ ሻእቢያ ነኝ፤ዲምህት ነበርኩ ባዩ አብርሃም ያዬ አሉታዊ መለዕክትን በስልክ ማስተላላፍ ጀምሮ እያለ ምነው መሰብሰባ ማስጮህ እንዳቃታቸው ነው ። ዝንብ ቢሰባሰብ መሶብ አይከፍትም ነው ነገሩ ። ቢባልም በዝምታ ማለፉ ጉዳት አለውና ሳንታክት ጸረ ትግላችን የሆኑትን ማጋለጥና መፋለም አስፈላጊ ይሆናል ። ግባቸው ምንድነው?

    1ኛ. ሕዝብ ለግንቦት7ና አርበኞች ግንባር ምንም ድጋፍ እንዳይሰጥ መቀስቀስ፤
    2 ኛ. የተጀመረውን ጦርነት ውሸት ነው በሚል ድጋፍ ማሳጣት፤
    3 ኛ. በድፍረት የመሪነት ቦታቸውን ተረክበው ልጆችና ምጮትን ትተው ወደ ትግሉ ሜዳ ያቀኑትን ማሳጣትና ከህዝብ መነጠል
    4 ኛ. ታመነም አልታመነም ወያኔን መርዳት ።

    ስለ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ድፍረትና ተዋጊነት ከእኔ በላይ የሚያውቋቸው መስክረዋልና የምጨምረው የለኝም ። ከታጋዮች ጋር ሆኜ የመጣውን ሁሉ እቀበለላሁ ብለው ሄደዋል ። የሚያኮራ ነው ። ተራው ጽዋው፤ማነህ ባለሳምንቱ ለሕዝባዊ ኃይል ደርሷልና በቆራጥነት ግዳጁን ተቀብለውታል ። የሚያኮራንና ተስፋ የሚሰጠን ነው፤ መሆንም አለበት ። በርግጥ ለኢትዮጵያና ሕዝቧ የምንቆረቆር ከሆነ ። ፍልሚያው በወያኔና በሕዝባዊ ኃይሉ መሀል ነው ። ሕዝብ የሚቆመው ከልጆቹ እንጂ ከጠላቱ እንዳልሆነም እናምናለን ። ጠፍቶ የከረመውን የመሪ ድርጅት ቦታ ግንቦት7 ና አርበኞች ሞልተውታልና በርቱ በርቱ የሚያሰኘን ነው ። አንዳንድ ጸሃፊዎች ረጅም አረፍት ነገር ይዘረጉና በንባቡ አንባቢው ውሉ ይጠፋዋል ። ነቃፊ ሆነው ለፋፊዎቹና ጸሓፊዎቹ (ፕሮፌሰር ሙሴ ለምሳሌ) ምን ሊናገሩ እንደሚፈልጉ ማወቅ ስይሆን መገመት እስኪያቅተን ድረስ ያደርሱናል ። አይገባም ፡፡ ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም ነውና ያለው ሁኔታ በግልጽ መቅረብ አለበት ። ይህ ማለትም

    ህ/ ሕዝባዊ ኃይል ታጋዮች በኢትዮጵያ መሬት ወያኔን እየተፋለሙ ነው ።
    ለ/ የሀይሉ መሪዎች ወደ ትግሉ ሜዳ ዘልቀዋል።
    ሐ/ ሁኔታው ወያኔና ደጋፊዎቹን ብርክ አስይዟል ።
    መ/ ድያስፖራው በተለይ ለሕዝባዊ ኃይሉ ድጋፍ ሊስጥ ይገባዋል ።
    ሰ/ የወያኔ ጀሌዎች ተጋልጠዋል ።

    ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው ። ነገ ሀቁ ቁልጭ ብሎ የሚታየው በወያኔ መፍረክረክና ውድቀት ነው

  2. be Ethiopia weyane

    be USA,, ena EU ,,, ye G7 cadrewoch.. yet enedres ?

    g7 zelo MINILIK Gibe yemegaba meselew weyes Hizbun niqotal ??????

    KKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKK teregagu pls !!!

  3. የወሎ ርሃብ አትበሉ አቦ ተውን!
    የኢትዮጵያ ርሃብ ዋና ምክንያት ምንድን ነው?
    ሰው !ሰው! በሰው ተንኮል ተራብን እኔ ግን ለዚህ ችግር መፍትሔ አለኝ ፡፡
    ብህሉን ወገኑ እምነቱን የሚጠብቅ ሕዝበ ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ዛሬ እየሆነ ያለው ርሃቡ ድርቁ በሰው ሰራሽ መሆኑ የአስተዳደርበደል ግፍ ብቀከላ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ አሁንም ርሃብ ሰውን እየቀጠፈ ነው
    ወሎን የኢትዮጵያ አካል አለማድረግ የሚያስቡ ስንት ካድሬዎች ናቸው በተራበ ሕዝብ ገንዘብ የሚሰበስቡ ሰው በላ ጅቦች መሆናቸውን ያረጋገጡበት ወቅት ነው አይ ወሎ!
    በወሎ ውስጥ ያለው የተፈጥሮ ሃብት ለምሳሌ፡ ታታሪና ጠንካራ ሰራተኛ ሕዝብ ያለበት፣ወንዞች (በሽሎ፣ገራዶ፣ ቦርከና፣ሚሌ፣ኩልመሽክ፣ተከዜ፣ማዕድኖች (ወርቅ፣ኦፓል ፣ነዳጅ፣የከበሩ ድንጋዩች፣ብረታ ብረት ወዘተ)፣ሃይቆች፣የዕርሻ ቦታዎች( ጨፋ ሜዳ አላንሻ ሜዳ፣ገራዶ ሜዳ)፣ ታዳ ልብ በሉ ይህ ሁሉ ሃብት እያለን በጎጥ ተደራጅተው እየዘረፊት፣ እያዘረፉት ተራበ ይሉታል በስሙ ይለመናል ይህ ጉዳይ ስሰማ ያመኛል ይቆጨኛል አቦ ተውን
    እንዳውም ዛሬ ርሃብ የለም ይሉታል ዝም ብለህ ተራብ ነው እያሉ ያሉት ሚዛናዊ አስተሳሰብ የጎደላቸው ዘረኞች ርሃብ ተኮር ስራ እየተሰራ
    ሳተናው አሊ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*