አሁንም እደግመዋለሁ :- ዜጎችን መታደግ የማይችሉ የሃይማኖት መሪዎች ቆባቸውን ያውልቁ:: (ምንሊክ ሳልሳዊ‬)

Minilik Salsawi – በኢትዮጵያ በሃይማኖታዊ የመንፈስ ጥኡም ሰበካና ዜማ ጋር በማጣፈጥ የጨቋኞችን የበላይነት በመስበክ ሕዝብን ማስፈራራት እና ማሸማቀቅ የጳጳሳት እና የሼህዎች አብይ ተግባር ነው።ዜጎችን መታደግ የማይችሉ በአስቸኳይ ቆባቸውን አውልቀው ከተራው ሕዝብ የመቀላቀል ግዴታ አለባቸው።ቤተክርስቲያን እና መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ እጅና ጓንት ሆነው በኢትዮጵያውያን ላይ የማያባራ ጭቆና ማካሄድ ከጀመሩ ረዥም ዘመናት ተቆጥረዋል። ይብልጡኑ የመንግስቶች ጎህ ከቀደደ ጀምሮ በተለይ የተዋህዶ ሃይማኖት መሪዎች አስፈሪ እና አስደንጋጭ እንዲሁም አሳዛኝ ደግሞም አሳፋሪ ቃላቶችን በመጠቀም ስጋዊ እና ምድራዊ ስልጣኖችን ለገዢዎች ለማደላደል ይህ ነው የማይባል ግፍ በምእመናኖቻቸው እና በሌሎች አማኞች ላይ ፈጽመዋል አስፈጽመዋል፤ እየፈጸሙ ነው፤ እያስፈጸሙ ነው። ይህ የማይዋጥለት አሊያም የሚክድ ካለ እውነት የማይደላው ብቻ ነው።

የኢትዮጵያ ጨቋኝ መንግስታት የሆኑ ከጥንት እስከ ዛሬ የተንሰራፉ በህዝብ ላይ የሚያደርጉት ጭቆና እና በደል ታሪክ የማይሽረው ጠባሳ በሰው ልጆች የትውልድ ሂደት ላይ መፍጠሩ እንደተጠበቀ ሆኖ የሃይማኖቶች ሚና ግን እጅግ በሚያሳዝን መልኩ ዜጎች በግፍ በጨቋኝ መንግስቶች ሲታረዱ በመባረክ የመንግስታቱን እድሜ አስረዝመዋል አሁንም እያስረዘሙ ነው። የመንግስት እና የሃይማኖት ቁርኝት የሚፈለገው ስልጣንን አደላድሎ ለመያዝ እና ህዝብን ረግጦ ለመግዛት ካለ ምኞት እንጅ ለዜጎች ከመቆርቆር የመነጨ አይደለም። የሃይማኖት አባቶች በሃይማኖታዊ የመንፈስ ጥኡም ሰበካና ዜማ ጋር በማጣፈጥ የጨቋኞችን የበላይነት በመስበክ ማስፈራራት እና ማሸማቀቅ የጳጳሳት እና የሼህዎች አብይ ተግባር ነው።በኢትዮጵያ ውስጥ ተገዝተው አሊያም አድርባይ ሆነው በመስራት ላይ ያሉ የሁሉም ሃይማኖት መሪዎች እጅግ ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ በዜጎች ላይ የሚደርሱ ግድያዎች ድብደባዎች እስሮች እና መንገላታቶችን እንደ አንድ መንፈሳዊ የሃይማኖት መሪ እንደ ሰብአዊ ተፈጥሮ አሊያም መጽሃፋቸው እንደሚያዛቸው ለዚጎች ሲደራደሩ ሲከራከሩ ሲያወያዩ ሲሆንም አንተም ተው አንተም ተው ሲሉ ሲያስታርቁ ሲያቻችሉ አልታዩም ከዚህ በከፋ መልኩ በልማታዊ ዲሞክራሲ የፖለቲካ ፉጨት ስር ተደብቀው በመንፈሳዊ ካባ ስር በለው በሚል አብዮታዊ ዜማ ዜጎችን እያስፈጁ ይገኛሉ።

አንድ የሃይማኖት አባት የታመመ ሲጠይቅ፤ የሞተ ሲቀብር ፤የተቸገር ሲረዳ ፤የታሰረ ዞሮ በመጎብኘት ሲያጽናና እንጂ ሲፖተልክ አሊያም ሲወሸክት ማየት ያማል። በሃገራችን ምእመናንን እንምራለን የሚሉ ሕዝብን መንፈስ እንመግባለን የሚሉ የለሊት ወፍ የሆኑ የክርስትና እና እስልምና የሃይማኖት መሪዎች ዜጎችን መታደግ የማይችሉ ከሆነ በአስቸኳይ ቆባቸውን አውልቀው ከተራው ሕዝብ መቀላቀል ግዴታ አለባቸው። ይህ ጉዳይ የብዙሃኑ የዜጎች ጉዳይ ስለሆነ ክርስቲያን እስላም የሚባልበት ሳይሆን የኢትዮጵያውያን የጋራ ጉዳይ ነው።በሃገሪቱ ዜጎች በአለም ላይ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በነጻነት በመጻፋቸው የእኩልነት እና የነጻነት ጥይቄ በማንሳታቸው ብቻ አሸባሪ ተብለው እስር ቤት በታጎሩባት ኢትዮጵያ ጉዳዩን እስኪ ላስጠናው ላጥናው ያለ የሃይማኖት መሪም ይሁን የሃይማኖት ሃራጥቃ የለም። እንዲሁም በታሰሩ ሰዎች እና በአሳሪዎች መካከል እርቀ ሰላም እንዲወርድ ለወደፊቱ ስህተቶች ካሉ እንዳይደገሙ ነገሮችን ለማግባባት እና ለማቻቻል የፈቀደ አንድም የሃይማኖት መሪ የለም። ይብስኑ የሃይማኖት መሪዎቹ በየስብሰባው እና በየጭብጨባው ዜጎች የመንግስታዊ ሽብር ዱላ ሰለባ እንዲሆኑ እያበረታቱ ይገኛሉ ።

የዜጎች ሁኔታ ያሳሰባቸው የሃይማኖት መሪዎች በከፍተኛ ዛቻ እና ማስፈራራት እንዲሁም በጥቅም በማሰር እንዳይንቀሳቀሱ አሊያም በተዘዋዋሪ ባልሰሩት ወንጀል ለማጥመድ ሴራ በመጎንጎን እያስፈራሩ የህዝቦችን የሰብ አዊ መብት ጥያቄዎች እንዳያነሱ በማስደንገጥ እንዲሁም በጥቅማ ጥቅም እና በገንዘብ በመደለል አባትነታቸውን ለስጋዊ ባለስልጣናት እንዲሸጡ እና የፖለቲካ ምንዝር እንዲፍጽሙ እየተደረገ ሲገኝ ይህንን የምንዝር ጌጥ ከመለማመዳቸው የመጣ የሃይማኖት አባቶች ከጨቋኞች ብሰው በሕዝብ ላይ ከፍተኛ በደል እንዲፈጸም ከባዱን ሚና እየተጫውቱ ይገኛሉ ።

የሃይማኖት አባቶች ሰጥ ለጥ ብለው ስለልማት ብቻ እንዲሰብኩ የእስላሙንም ሆነ የክርስቲያኑን ጥያቄዎች በተገኙበት እንዳያስተጋቡ ማስጠንቀቂያ ለቄሶች እና ጳጳሳት እንዲሁም የወያኔ መንግስት በቅርቡ ለሾማቸው የእስልምና ምክር ቢት ሼሆችን ከፍተኛ የሆነ ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል። እኔ ስጨፈጭፍ እናንተ አጨብጭቡ የሚለው አሸባሪው የወያኔ መንግስት ሃይማኖቶችን በራሱ አይዲኦሎጂ በመቀረጽ ቀሚሳቸውን ያንዥረገጉ ሰላዮችን እና የሃይማኖት ነቀዞችን በመመደብ ዜጎችን በተመለከተ የሚደርሱ በደሎች እና ገፈፋዎች ጠያቂ እንዳያገኙ አስታራቂ እንዳይሹ አድርጓል።ዜጎቹን የማይታደግ የሃይማኖት መሪ ቆቡን አውልቆ ከፖለቲካው ጎላ ሊቀላቀል አሊያም ገለልተኛ ሰው ሆኖ እንዲቀመጥ ለመምከር እንፈልጋለን ። በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሃይምኖቶች ለመንግስታዊ ሽብር ተገዢ እና ታዛዥ እንዲሁም የሽብር ሰባኪ ሆነው ዜጎችን በአደባባይ እያስግደሉ ዜጎች ከሞቱ በኋላ በሃይማኖታቸው ስርአት እና ደንብ እንዳይቀበሩ ተጽእኖ በማድረግ ለምድራዊው የጨቋኝ ምደብ ተባባሪ እና አስተባባሪ በመሆን ከባድ ወንጀል እየፈጸሙ ይገኛሉ። ስለዚህ በዜጎች ላይ የሚደርሱ በደሎች የማይቆረቁራቸው የሃይማኖት አባቶች ሊወገዱ ይገባል። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.

8 Comments on “አሁንም እደግመዋለሁ :- ዜጎችን መታደግ የማይችሉ የሃይማኖት መሪዎች ቆባቸውን ያውልቁ:: (ምንሊክ ሳልሳዊ‬)”

  1. Please take the Catholic pope from the picture – he was the only one who stood up against the regime during the 1997/2005 election time. He said the truth and faced questioning by the regime. I cannot forget that and you can ask the enquirer commission about the details to learn more. Be factual and please take him of since my moral conscious does not allow to say this is correct.

  2. Yesdet mengst blo machberber yqum, na netawetnalna gzan lnlew yemifelg amrow yefelese zegemtegna mehon alebet gn tllq tebyewoch bezih mesebasebachew bem yafelal, kewoyanie ekul memetat alebachew. Enter your comment here…
    Tru tenagerk, yelbien enem masbe new yalkew seali amsalu. Enie erasie yewoyanie wedqet ke internet lemat ena lemesmat internet sfetsh ewlalehu. Yalzerut ybeql ymesl, ethiopia eyenorku, beyeqenu eyehone yalewn eyayehu ena eyesemahu, baquarach woyanie temeta, tedemesese, tewegede, wedeqe yemil ziena ke internet safenefn ewlalehu., tamr tebqie, tamr endeliele eyawku, erasien matnanatie new mesel. Enie kewst eyenorku yeliele yemaytay yatesema neger kewch ager yalut fetmewt neta wetan yemil ziena lemesmat yewoyanien yeworera zemen mulu afaralehu. Mnm teb yale neger yelem. Kaltebaberbet hulum huno band lbona dl meche ygegnal betqit arbegna.

  3. Yesdet mengst blo machberber yqum, na neta wetnalna gzan lnlew yemifelg amrow yefelese zegemtegna mehon alebet, gn tllq tebyewoch bezih mesebasebachew dem yafelal, kewoyanie ekul memetat alebachew.
    Tru tenagerk, yelbien enem masbe new yalkew seali amsalu. Enie erasie yewoyanie wedqet ke internet lemat ena lemesmat internet sfetsh ewlalehu. Yalzerut ybeql ymesl, ethiopia eyenorku, beyeqenu eyehone yalewn eyayehu ena eyesemahu, baquarach woyanie temeta, tedemesese, tewegede, wedeqe yemil ziena ke internet safenefn ewlalehu., tamr tebqie, tamr endeliele eyawku, erasien matnanatie new mesel. Enie kewst eyenorku yeliele yemaytay yatesema neger kewch ager yalut fetmewt neta wetan yemil ziena lemesmat yewoyanien yeworera zemen mulu afaralehu. Mnm teb yale neger yelem. Kaltebaberbet hulum huno band lbona dl meche ygegnal betqit arbegna.

  4. “የጨቋኞችን የበላይነት በመስበክ ሕዝብን ማስፈራራት እና ማሸማቀቅ የጳጳሳት እና የሼህዎች አብይ ተግባር ነው”

  5. Brother you say the truth. Abune Teklehaimanot and Abune Teophlose were the right popes ever seen in Ethiopia. They sacrificed for the sake of their religion and people opposing the fascist Dergue.

  6. ክብር ለቀደምት የሀይማኖት አባቶች ለዜጎቻቸው ምን ያህል ቦታ ሠጥተው መሥዋት እንደሆኑ አንረሣም አሁንም ለህዝብ እንጂ ለወረበላ ድርጅት መቆም የለባቸውም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*