ፌስቡክ ገፃችን ላይ የሚመጡ እና የወደድናቸውን ቪዲዮዎችን ቀለል ባለ መንገድ እንዴት አውርደን ለራሳችን መያዝ እንችላለን ?
ተወዳጅ የማህበራዊ ሚዲያ የሆነው ፌስቡክ አገልግሎቶቹን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያዘመነ እና አዳዲስ መተግበሪያዎችን እያስተዋወቀ ይገኛል።
በቅርቡ አዲስ የቪዲዮ ማጫወቻ አገልግሎት ማስታወቁም ይታወሳል።
ታዲያ ፌስቡክ ገፃችን ላይ የሚመጡ እና የወደድናቸውን ቪዲዮዎችን ቀለል ባለ መንገድ እንዴት አውርደን ለራሳችን መያዝ እንችላለን የሚለውን እንመከለታለን።
የፌስቡክ ቪዲዮዎችን ማውረድ እንደ ዩትዩብ ቀለል ላይልልን ይችላል፤ በዚህ ጊዜም ሌሎች አማራጮችን መመልከት የግድ ሊለን ይችላል።
ለዚህ ደግሞ መፍትሄው GetFbStuff.com ነው ይለናል የፎስ ባይትስ ዘገባ።
በዚህ ድረ ገጽም፦
1. ኦንላይን የፌስ ቡክ ቪዲዮዎች
2. የግለሰብ የፌስቡክ ቪዲዮዎች
3. በፌስ ቡክ ገጽ ላይ ያሉ የፎቶ አልበሞችን ማውረድ እንችላለን።
በዚህ የፌስቡክ ቪዲዩ ማውረጃ ገጽ ተጠቅመን ከማንኛውም አይነት ኮምፒውተር ወይም ሞባይል መገልገያዎች ማለትም እንደ Windows, Mac OS X እና Ubuntu ላይ በቀላሉ ለማውረድ ያስችለናል።
GetFbStuff.com ድረ ገጽን ስንከፍትም በገጹ ላይ ቪዲዮ እና ፎቶ ለማውረድ የሚያችሉን አማራጮች ይመጡልናል።
ቪዲዮዎችን ለማውረድ የሚረዱን ቅደም ተከተሎች፦
•በመጀመሪያ የቪዲዮውን አድራሻ / URL/ መለየት
ለዚህም ለማውረድ የምንፈልገው ቪዲዮ ላይ ማውዛችንን በመጠቀም የቀኝ በኩል በመጫን ቪዲዮውን አዲስ ታብ ላይ እንዲከፍት በማድረግ ከላይ የሚመጣውን አድራሻ ማለትም (https://www.facebook.com/video.php?v=921674917) መክፈት።
•በመቀጠልም የፌስቡክ ቪዲዮውን ለማውረድ የሚረዳንን ገጽ /GetFbStuff.com/ መክፈት፥ ከላይ የመጣልንን የሊንክ አድራሻ በሚመጣልን ክፍት ቦታ ላይ ኮፒ በማድረግ ዳውንሎድ የሚለውን መጫን።

• ቪዲዮው የሚወርድበትን ጥራት መምረጥ ደግሞ ሶስተኛው ደረጃ ነው
የፌስቡክ ቪዲዮን ለማውረድ ዳውንሎድ የሚለውን ስንጫን ቪዲዮን በከፍተኛ ወይም አንስተኛ ጥራት ይውረድልዎት? የሚል አማራጭ የሚመጣ ሲሆን ይሆንን በመምረጥ ማውረድ እንችላለን።
ማስታወሻ፦ የፌስቡክ ቪዲዮ በዚህ መልኩ አልወርድ ካለን የቪዲዮው ባለቤት እንዳይወርድ አድርጎ የጫነው ወይም /privacy settings/በመጠቀም የተጫነ ሊሆን ይችላል።
ምንጭ፦ fossbytes.com