ከጅምሩ ኋላፊነት የጎደለው አገዛዝ ስለተጠያቂነት ሞራሉ የለውም::ከአጣብቂኝ ለመውጣት የሚደረግ ልማታዊ ሽወዳ ይቁም::(ምንሊክ ሳልሳዊ)
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ሃይለማርያም ደሳለኝ “በብሔር በአብሮ አደግነትና በተለያየ ጥቅም ተሳስረን፣ የምንከላከል ከሆነ ይሄ አይሰራም;እንደዚህ ዓይነት ነገሮች መቆራረጥ ኣለባቸው።” አለ እየተባለ ሃይለኛ ልማታዊ ወቀጣ እየተደረገ ነው::ወያኔን ለማያውቅሽ ታጠኙ በሏት;;በኢኮኖሚ በድርቅ እና በተለያዩ ጫናዎች አጣብቂኝ ውስጥ ከውስጥ እና ከውጪ ስትገባ ልማታዊ ሽወዳ ለማድረግ የምትጠቀምበት ዘዴ አንዱ ማኮላሻ አጀንዳዎችን በመፍጠር ከጀርባ ሴራዎች ላይ ማጠንጠን ነው::ታዲያ የወያኔ አዳማቂ እና አስፋፊ ልማታዊ ነን ባዮች ይህንን ይዘው የመንግስት ደጋፊን እና የመንግስትን ተቃዋሚዎችን ጭምር በኣንድ ድምጽ የሚያስማማ ንግግር እና ቆራጥነት በማለት ሃይለማርያምን እና ድርጅታቸውን አያሞጋገሱት ይገኛሉ::የሕዝቦች ነጻነት ባልተረጋገጠበት ሃገር ምን አይነት ፌዝ ነው የተያዘው?የሳምንቱ ምርጥ ቀልድ ነው የሆነብኝ::
በኢትዮጵያ ስር የሰደደው የመልካም አስተዳደር ችግር እና የተንሰራፋው ሙስና ሁሉ ያሳተፈ ስል ነቀል ለውጥ እስካልተደረገ ድረስ በዘራፊው ሕወሓት መራሽ አገዛዝ ይስተካከላል ማለት ዘበት ነው::የወያኔ ባለስልጣናት ተሰብስበው ችግሩ እኛ ጋር ነው አሉ እየተባልን ያለነው ስህተታቸውን አመኑ ብለን ሆዳችንን ለማባባት ከሆነ ሞኛቸውን ይፈልጉ::ካሁን ቀደም ከጠ/ሚ ተብዬ ቢሮ ጀምሮ በተለያዩ የሚኒስቴር መስሪያቤቶች እና አካሎቻቸይ ያልተባል ያልተማል ያልተነገር ነገር የለም ያልተሰበሰበ ያልተገመገመ ያልተወሰነ ወዘተ የለም::ሆኖም ነገሮች ሁሉ ማዘናጊያ ከጊዜ አጣብቂኝ ለመውጣት የሚጠቀሙባት ልማታዊ ሽወዳ ናት::በዘረፋ እና በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ላይ የተሰማራው ወያኔ ጭፍሮቹን እያስጨበጨበ አዲስ የግፍ ስልት ለመቀየስ ብቅ ማለቱን ያመለክታል::ላለፉት 25 አመታት የት ነበረኡ ይህ ሁሉ የወያኔ ባለስልጣን ዛሬ ስለ ሃላፊነት እና ተጠያቂነት የሚነግሩን???ሞራላቸውስ ???ለመሆኑ ብሄራቸውን እና አብሮ አደግነታቸውን መከታ በማድረግ በየመንግስት መስሪያ ቤቱ የተሰገሰጉት እነማን ናቸው?የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በየሃገሩ የሚገኙ ኤምባሲዎች በዋቢነት ማስቀመጥ ይቻላል::የሃይለማርያም ንግግርም የሚነካው ሕወሓትን ነው::ይህ ተባለ ያ ተባል ብሎ ስለ ቆራጥነት ከማላዘን መጀመሪያ እርምጃው ከሕወሓት ተጀምሮ ተግባራዊ ስራዎች ሲተገበሩ ነው ቆራጥነት የሚባለው:እውነት ከሆነ ላላዛኞቹ ብቻ::
የወያኔ ባለስልጣናት በተለይ ሕወሓት በዘረፋ እና በብሄር ተኮር መጠቃቀም ግንባር ቀደም ባለኔትዎርክ ነው::ቀሪ የወያኔ ድርጅቶችም በኔትወርክ ቢደራጁም ከሕወሓት እውቅና ውጪ አይንቀሳቀሱም::የሁሉ እኩይ ተግባር መሪ ሕወሓት ነው::ካሁን ቀደም በተለያየ ጊዜ የሙስና ኔትወርኮችን ለመበጣጠስ ተጠያቂነት እና ሃላፊነትን ለማስፈን የተደረገው ሙከራ በሌቦች ባለስልጣት ከሽፎ የመልካምነትን ጥያቄ ያነገቡ እስር ቤት ታጉረዋል ::ለዚህም ዋና ተጠቃሽ በሙስና እስር ቤት የሚገኘው መላኩ የሕወሓት ስውር እጆች አላሰራ አሉን ስላለ ብቻ ተይዞ ወደ ወህኒ ተወርውሯል::አሁን ከመላኩ እና ከገብረዋህድ በላይ ሃገሪቷን ያራቆቱ ቡድኖች ጠፍተው ነው?ይህ ደግሞ በብሄር በመንደር በአብሮ አደግነት የተሳሰረው ኔትወርክ በከፍተኛ ባለስልጣት እጅ(በሕወሓቶች) እንደሆነ በገሃድ ያሳያል::የሰው ልጆች ነጸነት ባልተረጋገጠበt ዜጎች በአሸባሪ ታርጋ እስር ቤት በሚገቡበት አገር እንዴት መልካም አስተዳደር ይረጋገጣል?መጀመሪያ ነጻነት!!!
“በብሔር፣ በኣብሮ ኣደግነት እና በተለያየ ጥቅም ተሳስረን የምንከላከል ከሆነ ይሄ ኣይሰራም!” ብሎ ሃይለማርያም የተ ናገረ ለሕወሓት ብቻ የሚሰራ ንግግር ነው::ይህ ንግግር ግን ተቃዋሚዎችን እና አገዛዙን አያግባባም::በፍጹም!!ሕወሓት የሚሰራውን በግልጽ ያስቀመጠ ነው ብንልም እንደኔ ግን ከአጣብቂኝ ለመውጣት የተደረገ የልማታዊ ሽወዳ የፖለቲካ ስልት አንዲት ቅርንጫፍ ነው::ይህ ጉዳይ ቆራጥ እርምጃ ከተወሰደበት የሕወሓት እና ጭፍሮቹ ጉሮሮ መቁረጥ ስለሆነ መተግበር ያስቸግራል አሊያም ይህን ለመተግበር ከተቃዋሚዎች ጫን ያለ የትግል ስልት ይዞ መዝለቅን ይጠብቃል::ላለፉት 25 አመታት ሃላፊነት በጎደለው መንገድ በዘረፋ እና በሃሰት ፕሮፓጋንዳ አገር እመራለሁ የሚል ቡድን በየትኛው ሞራሉ ሰላማዊ መንገድን በአንድ ጀንበር ይቀበላል::ከአጣብቂኝ ለመውጣት የሚደረግ ልማታዊ ሽወዳ ይቁም::ከጅምሩ ኋላፊነት የጎደለው አገዛዝ ስለተጠያቂነት ሞራሉ የለውም!!!
